TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሶማሌለንድ

የራስ ገዟ ሶሌላንድ ሲቪል አቬዬሽንና ኤርፖርቶች ባለስልጣን እንዲሁም የሶማሌላንድ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ መረጃ አሰራጭተዋል።

ይኸውም " የኢትዮጵያ አውሮፕላን በሱማሌላንድ አየር እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል " የሚል ነው።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ባሰራጨው በዚህ መረጃ " በ37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል " ብሏል።

" ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ #ተቆጣጣሪዎች በተሰጠ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ ተርፈዋል " ሲል ገልጿል።

የካቲት ወር ላይ በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸውን የሶማሌላንድ የሲቪል አቬሽንና ኤርፖርቶች ድርጅት ገልጾ ነበር።

የአሁኑ ክስተት የተፈጠረው እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው ተብሏል።

በዕለቱ በ37000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ #የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን በረራ ቁጥር UAE722 እና በተመሳሳይ በ37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39,000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር ተደርጓል ተብሏል።

ለተፈጠረዉ ለዚህ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ወቅሷል።

" መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን ዓለም ይወቅ "ም ብሏል።

ሁኔታው የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶበታል።

በዚህ ጉዳይ እስካሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ አየር መንገድ የተባለ ነገር የለም።

መረጃውን የሶማሌላንድ የሲቪል አቬዬሽን እና ኤርፖርቶች ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ያጋራን ካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
😱708150😡107🙏83😭73👏34🤔27😢26🕊26
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia ° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ #ሮይተርስ ዘግቧል። ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ…
#Update

የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል።

አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች።

የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

በተጨማሪም ከሶማሊያ ነጻ አገርነቷን ባወጀችው ሶማሊላንድ እና በከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኙት ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በ7 ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ መወሰኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በተመሳሳይም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን “ ለአጠቃላይ ምክክር ” ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተገልጿል።

የሶማሊያ እርምጃ ኢትዮጵያ #ሶማሌለንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ማድረጓን ተከትሎ " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብታለች " በሚል ምክንያት ነው።

ሮይተርስ ከሰዓት በፊት የሶማሊያ ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብሎ የነበረ ሲሆን አሁን የሶማሊያ መንግሥት በይፋ አምባሳደሩ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አሳውቋል።

የሶማሊያን መንግሥትን ውሳኔን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በዚህ ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ እና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
👏715😡154111🕊59😱43🤔31🥰27😭26😢20🙏11