TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፀጥታ ሁኔታው አስተማማኝ ነው~ጅግጅጋ!
.
.
ስምንተኛውን የከተሞች ፎረም #በጅግጅጋ ለማካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁንና ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናገሩ።

ዝግጅቱን አስመልክቶ በጅግጅጋ መግለጫ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው ጅጅጋ ላይ የፀጥታ ሁኔታው አስተማማኝ ነው"፤ የክልሉ ፖሊስ ከፌዴራል የፀጥታ አካላት ጋርም በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።

በከተማዋ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ተሳታፊ ከተሞች ወደጅግጅጋ ገብተው ዝግጅታቸውን ጀምረዋል ብለዋል።

ዝግጅቶችን በተመለከተ ከነገ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ከሚኖሩ ዝግጅቶች መካከል በጅግጅጋ ስቴዲየም የመክፈቻ ስነስርዐት፣ በከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት፣ በመሬት ልማት ማኔጅመንት፣ በዘርፉ አጀንዳዎች ማለትም በከተማ ልማት፣ አረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ፣ በቤቶችና ኮንስትራክሽን እንዲሁም ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ።

አቶ ካሳሁን ከተሞች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት ኤግዚቢሽን የሚካሄድ ሲሆን ከዚህ በፊት በተደረጉ ፎረሞች የተስተዋለው የድምፅ ብክለት በዚህ አመት እንዳይኖር ከከተሞች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

ሀሙስ በሚኖረው የማጠቃለያ ስርዓት ለሞዴል ኢንተርፕራይዞች፣ ለሴት ስራ ፈጣሪዎች፣ በሁሉም ክልሎች ካሉ የሴክተር ተቋማት በአፈፃፀም ብልጫ ላገኙ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ስራ ፈጣሪዎች እውቅናና ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።

በተመሳሳይ የዘጠነኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አዘጋጅ በእለቱ ይፋ ይደረጋል፤ የዋንጫ ርክክብም ይኖራል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።

ስምንተኛውን የከተሞች ፎረም የተለየ ለማድረግ ከማሌዥያ አለምአቀፍ የከተሞች ፎረም ልምድ ተወስዷል ያሉት አቶ ካሳሁን ፎረሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በታዳጊ ክልል መካሄዱም ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የሱማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር #አብዱልፈታህ_ሸክቢሂ በበኩላቸው ክልሉ ፎረሙን ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል፤ ተሳታፊ ከተሞችም ወደ ጅግጅጋ እየገቡ ነው ብለዋል።

ቢሮ ሀላፊው በጥቂት ግለሰቦች ከወራት በፊት ተከስቶ የነበረው ችግር ገፅታችንን አበላሽቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ምንም የፀጥታም ይሁን የደህንነት ችግር የለም ብለዋል።

ዶ/ር አብዱልፈታህ ስምንተኛው የከተሞች ፎረም የክልላችንን ብሎም የከተማችንን አስተማማኝ ሰላም የምናረጋግጥበትና በተግባርም የምናሳይበት እንዲሆን ሰፊ ስራ ሰርተናል ውጤቱንም እያየን ነው ብለዋል።

ስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ከየካቲት 9-14/2011 ''መደመር ለኢትዮጵያ ከተሞች ብልፅግና'' በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia