TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NobelPeacePrize #DrAbiyAhemed

"ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር"--- የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር

"የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት"--- የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም

የኖርዌይ የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦላቭ ጆልስታድ ጠ/ሚር አብይ ከአምስት ቀን በሁዋላ ሽልማታቸውን በሚቀበሉበት ወቅት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ፕሮግራም ላይ እንደማይገኙ ገልፀው "ይህ በጣም ችግር ነው። ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር" ብለው ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።

ዛሬ የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት በሰጡት መረጃ - "የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት። ስለዚህ ጠ/ሚሩ በተመረጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኖቤል ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር ይካፈላሉ" ብለዋል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ባሰራጨው መረጃ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት የሚድያ ፕሮግራሙ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተው እንደነበር አስውሷል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በስልጣን ላይ ስለመቆየት እና የሀገሪቱን ህዝብ ስለማገልገል ... #DrAbiyAhemed

ቪድዮ: ፋይል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ አንድ ቤተሰብ ለሌላ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ለማካፈል የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር አብይ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት መንገድም መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት ቢያደርስ በየቤቱ ምግብ ለማድረስ አቅሙም ሆነ መንገዱ ስለማይኖረው ፤ ሰዎች በምግብ እጦት እንዳይጎዱ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ሌላ ቤተሰብ ለማቅረብ ዝግጅት እንዲደረግ እና እንደቤተሰብ ምክክር እንዲደረግ አሳስበዋል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ወጣቶችም እረፍታቸውን ተጠቅመው ከዚህ ችግር እንዴት መሻገር እንደሚቻል ጥናት ፣ ምርምር እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የጥበብ ሰዎችም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ የተለያየ የስነ-ጥበብ ስራ በመስራት በሽታውን ለማሸነፍ የሚቻልበትን የተስፋ መንገድ እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrAbiyAhemed

- ኢትዮጵያ የተሻለ አቅም እንዳላቸው ሀገራት #እንዳንዘጋ የሚያደርገን ሁሉም ቤቱ ይግባ ቢባል ቤት የሌላቸው በርካታ ዜጎች አሉ።

- ቤት ያላቸውም ቢሆኑ በቀን ወጥተው የዕለት ጉርሳቸውን ካልሰሩ መንግስት ምግብ ማቅረብ የማይችል እነሱ ደግሞ ካልወጡ የማይበሉ ከሆነ በአንድ በኩል ህይወታቸውን መታደግ ቢቻልም በሌላ መንገድ ህይወታቸውን እናጣለን።

- ሌላ ሀገር ያየነውን እንዳለ እዚህ አምጥቶ መተግበር ያስቸግራል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RecepTayyipErdoğan #DrAbiyAhemed

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያ የኮቪድ-19ን ፈተናዎች እንድትቋቋም ለማገዝ ፈቃደኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሳውቀዋል።

ዶ/ር አብይ ከፕሬዘዳንቱ ጋር የተሳካው ነው ያሉትን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀው ፤ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እጅግ ተፈላጊ የሆኑትን የሕክምና መገልገያዎች በሚያቀርቡበት ሂደት ከፕሬዘዳንት ረጂብ ታይብ ኤርዶጋን ጋር እንደሚሰሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸውን ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump #DrAbiyAhemed

“ከኢትዮጵያው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ተወያይተናል ፤ ኢትዮጵያ #ቬንቲሌተሮች (የመተንፈሻ መሳሪያ) ያስፈልጓታል አሜሪካም ድጋፍ ለማድረግ በጥሩ አቋም ላይ ትገኛለች፤ ይህንንም እናደርጋለን!” - ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ
.
.
"ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኢትዮ - አሜሪካንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ አበረታች የስልክ ውይይት አድርገናል፡፡ የCOVID-19 መከላከል እና ቅነሳ ጥረቶች እንዲሁም በበረሃ አንበጣ ቁጥጥር ላይ የሚደረገውን ድጋፍ ለማድነቅ እወዳለሁ፡፡" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse #DrAbiyAhemed

በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች!

በኮሮና ቫይረስ ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ኢትዮጵያዊት ነብሰ ጡር እናት በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም በሆስፒታሉ ዛሬ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተዋል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች። "በአሁኑ ወቅትም ህጻኑና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ባለው በዚሁ ሆስፒታል ዛሬ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia