TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ”…
“አጋቾቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ጠይቀዋል። ልጄ ‘በአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው ” - የታጋች አባት
በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ካሜራ ማን ሆኖ ሲሰራ ነበር የተባለው ወጣት አብርሃም አማረ #በሊቢያ በአጋቾች #ታግቶ በየቀኑ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ፣ አጋቾቹ ታጋቹን ወጣት ለመልቀቅ 950 ሺሕ ብር እንደጠየቁ፣ ይህን ገንዘብ ማሟላት እንዳልተቻለ የታጋች አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የታጋች አባት አቶ አማረ ዓለም ገረመው ምን አሉ ?
- “ አጋቸቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ተጠይቀዋል። ልጄ ‘ከአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው። እኛ ኑሯችን ዝቅተኛ ነው። ፈተና ላይ ነኝ። ምን አይነት ደላላ አታሎ እንደወሰደው ፈጣሪ ይወቅ። ”
- “ ሌሎችም ታጋቾች ‘ነፍስ ውጪ የፍስ ግቢ፣ ስቃይ’ ላይ እንደሆኑ ልጄ ነግሮኛል። ”
- “ በጥቅም የተሳሰረ ምን አይነተ ጊዜ ላይ እንደደረስን ፈጣሪ ይወቅ። ልጄ በዚህ ደረጃ ላይ ይጠብቀኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ”
- “ አጋቾቹ ገንዘቡን በፍጥነት አስተላልፉ እያሉ እያጣደፏን ነው። እስካሁን ወደ 450 ሺሕ ብር ቢገኝም ቀሪው 500 ሺሕ ብር ገና አልተሟላም እየታገልኩ ነው። ”
- “ ልጄ ለዚህ እገታ የተዳረገው፣ ሕይወቱን ለማሻሻል ወደ ሌላ አገር እየሄደ ሊቢያ ሲደርስ ነው። ”
- “ ከዚህ በፊት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይከታተል የነበረ ቢሆንም በኮረና ወቅት እንደተቋረጠ፣ በዚህም አጋጣሚ ካሜራ ማን ሰልጥኖ በተለያዩ ተቋማት ተቀጥሮ 1,000 ብር እየተከፈለው ይሰራ ነበር። ”
- “ ዲግሪውን በግል እንዲማር እየጎተጎትኩት ነበር። ሆኖም ግን በደላሎች ተታሎ አሁን እሱም በስቃይ፣ ቤተሰብን በጭንቀት ላይ ወድቋል። ”
- “ አጋቾቹ ቀረጻውን ይልካሉ፣ የሱን ግን ድምጹን ነው የሚያሰሙኝ። ‘ስቃይ ነው እስከ 2 ወራት ታግተው የቆዩት በየቀኑ ነው የሚገረፉት ብር አምጡ እየተባሉ’ ብሏል። ”
የታጋች አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሁንም ፦
- የዓለም ባንክ፣
- የቄራና የሌሎች አካባቢ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ እየሄዱ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ይህ ደግሞ ለወጣቶቹም ለወላጅም፣ ለአገርም ፈተና ስለሆነ ትኩረት እንዲሰጠው መክረዋል።
“ ይሄ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አልጠበኩም። ” ያሉት አባት አቶ አማረ “ ልጆቼ እንዳይርባቸው፣ እንዳይጠማቸው፣ ከቁም ነገር እንዲደርሱ ነበር የምጥረው። አቅም ያላችሁ ሁሉ እርዳታ አድርጉልኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።
+251911388792 የታጋቹ አባት አቶ አማረ ዓለም ገረመውን በዚህ ስልክ ማግኘት ይቻላል። መርዳት ለምትፈልጉ 1000030178638 አቶ አማረ ዓለም ገረመው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ከትላንትና በስቲያ #በሊቢያ ደላሎች የታገተ የሀዋሳ ከተማ ተወላጅ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ #እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋችን እናት በማነጋገር መረጃ እንደላከላችሁ ይታወሳል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia