TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#RecepTayyipErdoğan #DrAbiyAhemed

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያ የኮቪድ-19ን ፈተናዎች እንድትቋቋም ለማገዝ ፈቃደኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሳውቀዋል።

ዶ/ር አብይ ከፕሬዘዳንቱ ጋር የተሳካው ነው ያሉትን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀው ፤ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እጅግ ተፈላጊ የሆኑትን የሕክምና መገልገያዎች በሚያቀርቡበት ሂደት ከፕሬዘዳንት ረጂብ ታይብ ኤርዶጋን ጋር እንደሚሰሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸውን ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RecepTayyipErdoğan
#AmbassadorAdemMohammed

በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን በአንካራ ቤተመንግሥት ለቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን በስነስርዓቱ ላይ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ በመካከላቸው ያለውን ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ባህላዊና ዲፕሎማሲያዊ ዕድሎች መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አምባሳደር አደም መሃመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመጥቀስ በሀገራቱ መካከል ያለውን የላቀ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መረጃው በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey : ቱርክ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 አገራት አምባሳደሮች አገሯን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የቱርክ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ባስተላለፉት ውሳኔ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች አንካራን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል። አምባሳደሮቹ እንዲባረሩ የተወሰነው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት ከተካሄደው እና ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀርባ እጁ…
#RecepTayyipErdoğan

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ የሰጡባቸው የ10 ሀገራት አምባሳደሮች ፦

🇩🇪 ጀርመን
🇺🇸 አሜሪካ
🇸🇪 ስውዲን
🇳🇴 ኖርዌይ
🇳🇱 ኔዘርላንድስ
🇩🇰 ዴንማርክ
🇳🇿 ኒው ዚላንድ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇨🇦 ካናዳ
🇫🇮 ፊላንድ ናቸው።

ትላንት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ኤስኪሴሃይር በተባለ ስፍራ ለተሰበሰቡ ሰዎች ባደረጉት ንግግር ላይ እንዲህ አሉ ፦

" አምባሳደሮቹ ወደ ቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሄድ ትዕዛዝ ለመስጠት ሊደፍሩ አይገባም። ምን መደረግ እንዳለበት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራችን አስፈላጊውን ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ።

እነዚህ 10 አምባሳደሮች በአንድ ላይ በአገሪቱ ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸው /ፐርሶና ነን ግራታ/ ሊባሉ ይገባል።

በአስቸኳይም መፍትሄ ይደረግለታል"

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ። ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። @tikvahethiopia
#RecepTayyipErdoğan

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የደስታ መግለጫ ላኩ።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ መሾማቸው ይታወሳል።

ሹመቱን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መግለጫ ሲልኩ እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ጥቅምት 16/2014 ዓ/ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ ፤ የቱርኩ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዴጋን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ ልከዋል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በቀጣይ ከጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት ቱርክ 🇹🇷 እና ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከላቸው ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia