TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNICEF

የተመድ ህፃናት መርጃ ድርጅት ( ዩኒሴፍ ) በትግራይ 33 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት በሞት አደጋ ላይ መሆናቸውን አስታወቀ።

ዩኒሴፍ እርዳታ የሌላቸው አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒሴፍ ቃለ አቀባይ የሆኑት ጄምስ ኤልደር ፤ "በአሁኑ ወቅት የዳሰሳ ጥናት ከተደረገባቸው 20 በመቶው ሕዝብ መካከል 350 ሺህ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ላይ መሆናቸውን ማሳየቱ ይፋዊ በሆነ መልኩ ረሃብ (ፋሚን) አለ ብሎ ለማወጅ ከተቀመጠው በታች ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሰዎች እየሞቱ በቃላት ባንጫወት ጥሩ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

33 ሺህ የሚሆኑ ህፃናትና ጨቅላዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት በህመም አፋፍ ላይ ናቸው። በሞት አደጋም ላይ ናቸው በማለት ዩኒሴፍ አስጠንቅቋል።

ከሰሞኑን ተመድ ባወጣው ሪፖርት ከ350 ሺህ በላይ የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ በሚባል ችግር ውስጥ ናቸው ብሎ ነበር።

የክልሉን ሁኔታ የገመገመው የተመድ ሪፖርት በክልሉ ያለው የምግብ ሁኔታን "ካታስሮፊ" በሚል ጉዳትን እንደሚያስከትል ፈርጆታል።

በዚህ ትርጉም መሰረት በአሁኑ ወቅት ቸነፈር (ረሃብ) እና ሞት እየተከሰተ ያለ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ሊዛመት እንደሚችል የሚገልፅ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 7 የUN ሰራተኞችን ሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ስር በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚሰሩ 7 የውጭ አገር ዜጎች በ72 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የመንግሥታቱ ድርጅት ባልደረቦች…
#UNICEF

በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት  የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር መሀመድ ኤም. ማሊክ ፎል ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹 መጥተው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ጋር ተወያይተዋል።

ዳይሬክተሩ መሃመድ ኤም. ማሊክ ፎል የUNICEF ሰራተኞች የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የአገሪቱን ህግ አክብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በመንግስት ከአገር እንዲወጡ በተደረጉት የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ምትክ ሌላ ለመላክ እንዲቻል ከመንግሥት ጋር ምክክር ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚስተር መሀመድ ኤም. ማሊክ ፎል ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በማህበራዊ ልማት ዘርፎች የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በተለይ በህፃናትና ታዳጊ ልጃገርዶች እና ሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፤ የድርጅቱ ሰራተኞች (UNICEF) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እሴቶችን እና የሀገሪቱን ህግ በማክበር ተግባራቸውን መፈፀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የተመድ ባለልዩ መብት ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ቁርኝት ያላትና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት የተለየ ትኩረት የምትሰጥ መሆኑ አውስተው፣ መንግስት ከድርጅቱ ጋር በቅርበት እና በትብብር ጋር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

አምባሳደሯ UNICEF የመንግስትን ጥረት በመደገፍ በጤና፣ በትምህርት፣ በንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት፣ በሌሎች የማህበራዊ ልማት ተግባራት የሚያከናዉነዉን ስራ አድንቀዋል።

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገቡ የUNICEF ተወካይ ጨምሮ 7 የተመድ ተወካዮች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#UNICEF

UNICEF በደብረ ብርሃን ከተማ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ለአዳዲስ ተፈናቃዮች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ህይወት አድን የሆነ የተመጣጠነ ምግብና ውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ UNICEF አሳውቋል።

UNICEF የህጻናት ህይወት፣ ጤና፣ ደህንነት እና የወደፊት ህይወት ንፁህ ውሃ እና ንፅህና ሳያገኙ ሲቀሩ አደጋ ላይ ይወድቃል ብሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከ850 ሺህ በላይ የኩፍኝ መከላከያ ክትባቶች ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባቱን ዩኒሴፍ ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒሴፍ ክትባቱ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መከተባቸውን ለማረጋገጥ በጣም ወሳኝ እርምጃ ነው ብሏል።

የኩፍኝ በሽታ በጣም ተላላፊ ነገር ግን በክትባት በቀላሉ መከላከል ይቻላል።

#UNICEF

@tikvahethiopia
#UNICEF #ETHIOPIA

ትላንት ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆኑትን ካትሪን ራስል በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በአገራችን በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ በርካታ ሕጻናትን ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ለማየትና ለመርዳት የሚያስችላቸውን የዓለም አቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ ለማስገኘት ነው ተብሏል።

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመስክ ሥራ ልምድ ያለው ሲሆን ግንኙነቱን በማሻሻልና በመጠናከር መሠራት እንዳለበት ፕሬዚደንቷ ገልጸዋል።

ካትሪን ራስል ከሶስት ወር በፊት ነው የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆነው የተሾሙት።

ምንጭ፦ የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#Ethiopia #UNICEF

ስለምስራቅ አፍሪካ ድርቅ እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ስላሳደረው ተፅእኖ ምን ያህል እናውቃለን ?

(የተመድ የህጻናት ተራድኦ ድርጅት - UNICEF)

➤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ምስራቅ አፍሪቃን የመታው ድርቅ ከ10 ሚሊየን በላይ #ህጻናት ለአስከፊ የምግብ እጥረት ዳርጓል። እስካሁን በርሃም አደጋው የሞተ ሰው አላጋጠመም።

➤ በኢትዮጵያ ባጋጠመው 3 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች የዝናብ እጥረት በዓመታት አስከፊ የድርቅ ሁኔታ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፤ አስከፊው ድርቅ ለበርካታ እንስሳት ሞት ፣ የውኃ ምንጮችም ተሟጠው እንዲደርቁ መንስኤ ሆኗል።

➤ በ4 ክልሎች (ሶማሊ፣ ኦሮሚያ ፣ አፋር፣ ደቡብ ) ድርቅ በሰፊው የተከሰተባት ኢትዮጵያ ከችግሩ ለመላቀቅ ቢያንስ 5 ዓመታት ያስፈልጓታል።

➤ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ) ድርቁ 10 ሚሊየን ህዝብ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አሳርፏል። ከዚህ ውስጥ 1.5 ያህሉ ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናት ናቸው፡፡ 

➤ በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ 1.75 ሚሊየን ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቋል።

➤ በሶማሊ ክልል ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 220 ሺ ህጻናት ገደማ የተመጣጠነ ምግብ እጦት አለባቸው፡፡ ከ150 ሺህ በላይ አጥቢና እርጉዝ እናቶች በቂ ምግብ የማያገኙ ናቸው።

➤ ባለፈው ዓመት በችግሩ ሳቢያ ከ400 ሺ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተቆራርጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ ያለዕድሜ ጋብቻን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ምስቅልቅሎችን አሳርፏል።

➤ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ የናረው የስንዴና ሌሎች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ የድርቅ ተፅእኖውን ምላሽ የመስጠት ጥረቶችን አዳጋች አድርጎታል።

#UNICEF #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#Ethiopia #EU #UNICEF

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የተደረገው ድጋፍ የህፃናትና ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና በግጭቱ ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ለማድረግ ነው።

@tikvahethiopia