TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጠ/ሚ ፅ/ቤት🔝

የአስተዳደር #ወሰን እና #የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንና የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት ፀድቋል የአባላት ዝርዝር ከላይ ባለው ምስል ተገልጿል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጭልጋና አካባቢዋ የተፈጠረው ግጭት ዛሬም ሙሉ በሙሉ አልቆመም!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋና አካባቢዋ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወቃል፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የተከሰተው ግጭት ዛሬም ሙሉ በሙሉ አለመቆሙን ተሰምቷል፡፡ ግጭቱ ከቅማት #የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ እየተነሳ መሆኑም ይገለጸል፡፡

የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ የቅማንት የማንነት ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ምላሽ አግኝቷል፣ የአስተዳደር ጥያቄውንም ለመመለስ በክልሉ መንግሥት እየተሠራ ነው ያለው›› ብሏል። ቢሮው ግጭቱ በአማራና ቅማንት ሕዝቦች መካከል አይደለም ሲልም ተደምጧል፡፡ ይልቁንም ችግሩ ሠላም የማይፈልጉ አካላት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር የፈጠሩት አለመግባባት ነው›› ብሏል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የቅማንት #የማንነት እና #የራስ_አስተዳደር ጥያቄ አልተመለሰም" የሚሉ አካላት ትክክል አይድሉም ጥያቄዉ እንደተመለሰላቸዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቀብሎ አጽድቋል፤ ‘ሌሎች ተጨማሪ ሦስት ቀበሌዎች ወደ ቅማንት ይካለሉ’ የሚሉ ጥያቄዎችም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የጥናት ቡድን ልኮ ቀበሌዎቹ ኩታ-ገጠም አለመሆናቸዉን አረጋግጧል፤ ስለዚህ ጥያቄያቸው ተገቢ አይደለም ተብሏል” አቶ ወርቁ አዳሙ በፌዴሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ

@tsegabwolde @tikvahethiopia