TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትኩረት

#ከዳሎቻ ወደ #ወራቤ ያለው መንገድ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

ከላይ በምስሉ ላይ የምትታየው እናት ምጥ ይዟት ከዳሎቻ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ብትላክም በመንገዱ ብልሽት ምክንያት አንቡላንሷ በጭቃ ተይዛ እናትም በጭቃ መሃል እንድትወልድ ተገዳለች።

ከዚህ ባለፈ ከዳሎቻ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ሪፈር የተፃፈላት ህፃን በመንገዱ ብልሽት ምክንያት አንቡላንሱ መሃል መንገድ ደርሶ ማለፍ ባለመቻሉ የህፃኗ ህይወት ልያልፍ ችሏል።

መንገዱ ከዳሎቻ ከተማ ጫፍ እስከ ወራቤ ከተማ ጫፍ ቡታጅራ መውጫ የተዘረጋና ርቀቱም ከአስር ኪሎ ሜትር ያነሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁናቴ ተበላሽቶ ይገኛል። 

በተጨማሪም መንገዱ እጅግ በጣም ጠባብ ፣ በየቦታው የተቆፋፈረ፣ በክረምት ወራት ከባድ ጭቃ፣ በበጋ ጊዜያት አስቸጋሪ አቧራ ያሚበዛበት ሲሆን በተደጋጋሚ የሚጠቀሙት መንገደኞች ላይ ከፍተኛ የጤና መታወክም ሲያደርስ ቆይቷል።

ይህም መንገድ በክልል ገጠር መንገድ በኩል በጠጠር መንገድ ደረጃ ተሰርቶ እያገለገለ ቆይቶ  በየ ጊዜው የተወሰነ ጥገና እየተደረገለት እስካሁን ቢደርስም አሁን ላይ የጉዳቱ መጠን እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ መድረሱ ከክረምቱ ወቅት ዝናብ ጋር ተዳምሮ የመስመሩን ጉዞ እጅግ ፈታኝ አድርጎታል።

ስለሆነም የሚመለከተው አካል የመንገዱን አሁናዊ ሁኔታ ተመልክቶ አፈጠኝ ምለሽ ሊሰጠን  ይገባል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

(ሰይፈዲን ሉንጫ ከወራቤ)

@tikvahethiopia