TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደሴ

ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ከህፃናት ልጆቻቸው ጤና የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ላሉበት ቦታ የሚመጥናቸውን ካሳ ካገኙ ቦታውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደሴ ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።…
#ደሴ

“ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ” - ደሴ ሆስፒታል

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፣ በሆስፒታሉ በኩል የሚቃጠለው ቆሻሻ ወደ ቤታቸው እየገባ እንደተቸገሩ ፣ መጀመሪያ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ሲቃጠል እንደነበር ፣ ዘመናዊ ማስወገጃ ከተሰራ በኋላ ግን ሙሉ ወደ ግቢዎች ውስጥ እንደሚገባ ፣ በተደጋጋሚ ለችግሩ መፍትሄ ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

መንደሮቹ በተለይም ህፃናት ልጆች ያሉባቸው እንደሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፣ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከመኖር ለቤታቸው የሚመጥን ካሳ ከተከፈላቸው ቦታውን ለቀው መሄድም እንደሚሻላቸው ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት #ቪዲዮም በቃጠሎው ወቅት ቆሻሻው ወደ ቤት እንደሚገባ ያስገነዝባል።

ነዋሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው  የሆስፒታሉ ባለስልጣን ፤ “ አሁን ያ ሁሉ አልፎ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ፣ ሕጋዊ ማስወገጃ ተሰርቶለት፣ ድሮ ከነበረው ችግር የወጣበት ቀን ነው ” ብለው፣ “ ከነበረው ችግር ወጣ ነው እንጂ ችግሩ ብሶ ቀጥሏል አልልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በእርግጥ #ከሕዝብ_መኖሪያ ሊወጣ ተቋሙ ግድ ነው። አሁን ግን ያለው የቆሻሻ አወጋገድ በአዎሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ መንግሥት ተደግፎ Almost ሰባት ወሩ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ዘመናዊ የሆነ፣ ስታንዳርዱን የጠበቀ ማቃጠያ ተሰርቶለታል ” ነው ያሉት።

እኚሁ ባለስልጣን አክለውም ፣ “ ግን ከሰው መሀል ነው። ያ በሕጋዊ መንገድ ሲቃጠል እንደድሮው እንኳ ብናኝ እንኳ አያርፍባቸውም። ጭሱ ግን ሊሸት ይችላል ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ዘመናዊ ማቀጠያ ቢሰራም ቆሻሻው እየገባ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ባቀረቡት መሠረት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለባለስልጣኗ ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፤ “ ጭሱ ታካሚንም ይረብሻል፣ ከሕዝብ መሀል መሆናችን ነውና ዋናው ትልቁ ችግር። ጭሱማ እንዴት ይቀራል ? ተኔሬተር ነውኮ ግን የሚጨሰው ” ነው ያሉት።

“ እነዚህ አሁን የሚጨስባቸው ጠቅላላ በካዳስከርና በከተማ ማስተር ፕላን የሆስፒታሉ ቦታዎች ናቸው ” ብለው ፣ “ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ፣ እንጂ አሁን ላይ እጅግ የተሻለ ነገር ነው ያለው ” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፣ “ ለምን ብትል በጣም ብዙ ተሰቃይተው አልፈዋል፣ ከዚህ አሁን ካለው በላይ። ግን ከጎኑ ያለው ሰው አይሸተውም አልልህም። ግን ከፍታው ከአራት ሜትር በላይ ሆኖ፣ ከአምስት፣ ከስድስት ሜትር በላይ ከፍ ብሎ የሚጨስ የተሰራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ” ብለዋል። 

“ አሁን ላይ ራሱ ሞዲፋይ አለው ተነሬተሩ። የተሰራው ማቃጠያ #ሞዲፋይ አድርገው አሁንም እዛው ላይ የሰሩት ከፍታውን ካለው ጨምረው ሊሰሩት እያሰቡ ነው። በቅርብ ቀንም ይሰራል። ሁለተኛ ደግሞ ከውጪ ያልገባ ጭስ አልባ ማቃጠያ ማሽን አለን። በቅርብ ጊዜ (ከወር በኋላ) ይደርሳል። ብዙ ነገሮችን የሚቀንስልን ” ሲሉም ተናግረዋል።

ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ግን ፤ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ በየዕለቱ ስቃያቸውን እያዩ እንደሆነ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የትንንሽ ልጆቻቸው ጤና አደጋ ላይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
" የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለቅቄያለሁ " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በስሩ የነበሩ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን በምህረት መልቃቁ አስታወቀ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዛሬ አመሻሽ ባሰራጨው መግለጫ ፤ " በያዝነው ወር የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የደረሰበት ደረጃ ለመገምገም በአዲስ አበባ መቀመጡ ተከትሎ በተደረሰው ስምምነትና በተቀመጠው የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በትግራዩ ጦርነት ተማርከው እስከ አሁን በእስር የቆዩት 112 የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በምህረት ተለቀዋል " ብሏል። 

እነዚህ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔ መሰረት የተለቀቁት መልካም አርአያ የነበራቸው እንዲሁም የፌደራል መንግስት በእስር የቆዩ የትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት በምህረት ለመልቀቅ የጀመረው እርምጃ እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው ብሏል።

በቅርቡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ተሳታፊዎች የትግራይ ተወላጅ እስረኞች / የሰራዊት አባላት እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር።

በዚህም ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እሳቸው በሚያውቁት አንድም የታሰረ ሰው እንደሌለ ተናግረው ፤ ስራ እንዲያቆሙ የተደረጉትም ወደ ስራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረው ነበር።

መንግሥት እስረኞችን ፣ የስራ አስፈፃሚዎችን ሳይቀር መፍታቱን በመናገር " ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው " ብለው ነበር።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
                                                 
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል " -  የዕድሜ ባለፀጋ

በአጣዬ ከተማ እና በሰንበቴ ዙሪያ የታጠቁ ኃይሎች ሰሞኑን ከፈተቱት በተባለ ተኩስ ንጹሐን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ፤  “እኔ የማውቃቸው ብቻ 6 ሰዎች ተገድለዋል። ወደ ደብረ ብርሃን የተላከ ቁስለኛም አለ ” ብለዋል።

ይህ መረጃ የአንድ አካባቢ ብቻ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት።

“ ካራ ለጉማ አዲስ አበባ መርካቶን ነው የሚመስለው ከአጣዬ በመጡ ተፈናቃዮች። ከዛፍ ስር፣ ት/ቤት ነው የተጠለሉት ” ብለዋል።

" አጣዬ 01 ቀበሌ ዘረፋ ነበር ፤ ሰንበቴም በተመሳሳይ ፤ አጣዬ ከተማ በጣም ወድሟል” ሲሉ አስረድተዋል።

ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አንድ የሰንበቴ ነዋሪ በበኩላቸው ሰሞኑን የተኩስ ጥቃት እንደነበር ተናግረው  “ የኦሮሞ ተወላጆችም በ ' ፋኖ ' ታጣቂዎች ተገድለዋል። በእኛ አካባቢ ከ5 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ” ሲሉ ተናገረዋል።

“ በተለይ ከሳምንታት ጀምሮ ግድያ፣ ቃጠሎ ነው የሚስተዋለው። በርካታ ንጹሐን ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ " ህዝቡ አለቀ፣ ወደ ማን አቤት እንበል ? " ሲሉ  ጠይቀዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ " ሰውም አልቋል፣ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለው ለጥቃቱ " ሸኔ" ን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ ለጥቃቱ " ፋኖ " ን ተጠያቂ ሲያደርግ ተስተውሏል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መካሻው፣ ስልክ ባያነሱም “ ስብሰባ ላይ ሆኘ ነው ” ያሉ ሲሆን፣ የሚመቻቸውን ወቅት ስንጠይቃቸው “ አሚኮ  ላይ መግለጫ ስለሰጠን ከዛ ማግኘት ይችላሉ ” ከማለት ውጪ በድጋሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጎራባች ስፍራዎች በሚገኙ የአማራና የኦሮሚያ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፣ “ ስብሰባ ላይ ነኝ ” ብለዋል።

የኢፌደሪ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ፣ የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታና ኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች በተመሳሳይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በማንኛውም ሰዓት ማብራሪያ ከተገኘ ይቀርባል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።

የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።

ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት  መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።

ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።

@tikvahethiopia
#ሞስኮ

ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሩስያ ፣ ሞስኮ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ።

አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።

ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል።

የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።

የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።

በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል።

ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።

የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል።

እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።

ቪድዮ ፦ ከሩስያ የማህበራዊ ሚዲያዎች

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ | ለኢንስታግራም ተከታዮቻችን

የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ 3 ኢንስታግራም ተከታዮቻችን የ300 ብር የካርድ ስጦታ እናበረክታለን፡፡

🫵🏽 የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ኢንስታግራም https://bit.ly/3NiRHOn ገፅን መወዳጀት ይኖርብዎታል፡፡

🧵 ተሸላሚዎችን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #questionandanswer
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ➡️ " የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል " - የዶክተር በሀይሉ ቤተሰብ  ➡️ " ይቅርታ መረጃው የለኝም " - የአዲስ አበባ ፓሊስ እውቁና እጅግ የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር በኃይሉ ኃይሉ መገደላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ዶ/ር በኃይሉ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ለጥዋት ሩጫ በሚል በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው የተገለጸው። ለቲክቫህ…
#AddisAbaba

በኢትዮጵያ እውቁ እና የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሃኪም ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ባለፈው ሳምንት እሁድ መጋቢት 8 ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባሰራጨው መረጃው የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ " ማሞ ድልድይ " ስር ወድቆ መገኘቱን ገልጿል።

በወቅቱ አስከሬኑ ተነስቶ የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ  ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓልም ብሏል።

ፖሊስ ፤ ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን ምርመራ ውጤት ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን ይገልጻል ብሏል።

" ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል " ሲል ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራ መቀጠሉን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።

ከቀናት በፊት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ቤተሰቦች ፤ ጥዋት ለሩጫ በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተው መገኘታቸውን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለው ነበር።

ዶክተር በሀይሉ ቤታቸው ቦሌ ሚካኤል እንደነበር የገለጹት እኚሁ የቅርብ ቤተሰብ " ሞተ ያሉት ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው ነበር።

@tikvahethiopia
" ከእገታ ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር ክፈሉ ተብለን ብንከፍልም ልጃችን አልተለቀቀም፣ ያለበትንም ሁኔታ አናውቅም ፤ የድርጊቱ አቀናባሪ ሀገር ለቆ ሊወጣ እንደሆነ ሰምተናል " - አባት

ከወራት በፊት ማለትም ነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ/ም በታጣቂዎች የታገተ ልጃቸዉን ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር በሰው በሰዉ የከፈሉት ቤተሰቦች ትእዛዙን ቢፈጹሙም ታጋቹ ግን ዛሬም ሊለቀቅ አልቻለም ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪነታቸው በሀዋሳ የሆነው አቶ ፍቅሬ አበራ የተባሉ አባት ፤ በወቅቱ በመተሀራ ከተማ የሆቴል ማናጀር የነበረዉ ልጃቸዉ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ በሆቴሉ ይሰራ የነበረዉን ልጅ ስህተት መስራቱን ተከትሎ የገንዘብ  ቅጣት መቅጣቱን ተከትሎ ልጃቸው መተሀራ ከሚገኘዉ የስራ ቦታዉ ውስጥ ካለ ማረፊያ እንዲታፈን መድረጉን አመልክተዋል።

ከዛም 300 ሺህ ብር ለማስለቀቂያ እንዲከፍል መደረጉን ገልጸዋል።

አባት ፤ " በግል የስራ ጸብ ምክኒያት ባልደረባውን ለኦነግ ሸኔ አሳልፎ የሰጠዉ ግለሰብ ብሩን ብንልክም ልጃችን እንዳይወጣ አድርጎ ' ሰራሁለት ' ሲል መደመጡን " የሚገልጹት አባት ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ በእጄ ላይ አለ ብለዋል።

ነገር ግን አቤቱታቸውን ሰምቶ መረጃቸውንም መርምሮ ወንጀለኛዉን አካል የሚይዝላቸው የህግ አካል እንዳጡ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ ልጄን ለታጣቂዎች አሳልፎ የሰጠው ግለሰብ ከሀገር ለመዉጣት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ ሰምተናል " ያሉት አባት " የሚመለከተዉ አካል እጄ ላይ ያለዉን መረጃ ተጠቅሞ ፍትህ ያወርድልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ " ሲሉ ተማጽነዋል።

አሁን ላይ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋናው ቢሮ ለማሳወቅ እንደተዘጋጁ ገልጸው የልጃቸውን አሁናዊ ሁኔታ ካለማወቃችን በላይ " ለዚህ ሁሉ ሀዘን የዳረገን አካል አለመያዙም አሳምሞናል  " ብለዋል።

መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።

ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።

በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።

ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑ ቸርነትን እናድርግ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል። ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል። ገቢ…
#Update

" ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የመግቢያ ትኬቶች በ100 ብር እየተሸጡ ሲሆን ትኬቶቹን ፦
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ነገ በመግቢያ በር ላይም ትኬት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች / ምዕመናን ነገ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲሄዱ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ እና የአቅማቸውን ያህል እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia