TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመወዝ ➡️ " አሁን ላይ ከኑሮ ወድነቱ ጋር ተደምሮ የደመወዝ መዘግየት እየፈተነን ይገኛል " - ሰራተኞች ➡️ " ችግሩ ይቆያል የሚል እምነት የለኝም " - የድርጅቱ አመራር ደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በበጀት ምክኒያት መፈተን ከጀመረ እንደቆየ የድርጅቱ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። በዚህም ምክኒያት " ደሞዝ እየዘገዪ ተቸግረናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በ28 ሲገባ የነበረዉ ደሞዛችን…
" ... ደመወዛችን እየዘገየ መከፈሉን ተከትሎ መስራትም መኖርም አልቻልንም " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ሰራተኞች
የቀድሞዉ ደቡብ ክልል መበተኑን ተከትሎ በአራቱ ክልልሎች ማለትም፦
- በሲዳማ
- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- በደቡብና
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጀት እንዲተዳደር ፤ በክልሎች ፈቃደኝነት እና በመንግስት አቅጣጫ ተቀምጦለት ሁሉንም ክልሎች እንዲያገለግል ተወስኖ ስራዉን የቀጠለዉ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሰራተኞቹን ደሞዝ በሰአቱ መክፈል እየቻለ እንዳልሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።
በዚህ ወርም እንዳለፈዉ ወር የሰራተኛዉ ደሞዝ ዘግይቶ ከ12 ቀናት በኃላ ነው የተከፈለው።
የሰራተኞች ደመወዝ ዛሬ ከሰዓት ነው ያገባው።
ደመወዝ እየዘገየ በመከፈሉ የድርጅቱ ሰራተኞች አደጋ ላይ መውደቃቸዉንና ህይወታቸዉ እየተመሰቃቀለ መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" አሁን ላይ ድርጅቱ የሰራተኛዉን ደሞዝ እያዘገየ ከመክፈሉ በተጨማሪ የስርጭት መቆራረጥና የሎጅስቲክስ ችግሮች እየተመለከትን ነው ፤ " የሚሉት የድርጅቱ ሰራተኞች " አመራሩ ስለችግሩ ሊያወያየን ይገባ ነበር " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተከሰተዉ የደሞዝ መቋረጥ ፣ የስራ ማስኬጃ ጉድለትና የስርጭት መቆራረጥ ያመጣው የገንዘብ ችግር ምክንያቱ ክልሎች የፈቀዱትን በጀት በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች ምክንያት መልቀቅ ባለመቻላቸዉ ነው።
ችግሩን ለመቅረፍ ድርጅቱ ከክልል አመራሮች ጋር ንግግር እያደረገ " ተስፋ የሚጣልበት መግባባት " ላይ መድረሱ ታውቋል።
ይሁንና ከሌሎች ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የተፈቀደዉ በጀት በአግባቡ እንደሚለቀቅ ቢገለጽም በሲዳማ በኩል አሁንም ምላሽ አልተገኘም።
የሲዳማ ክልል የድርጅቱ መቀመጫ እና መስራች ሆኖ ሳለ ስለምን ዝምታን መረጠ ? በማለት ለክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ተጠሪ አቶ አብርሀም ማርሻሎም ሆነ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ የሆኑትን ዶክተር አራርሶን ገረመዉን ለማናገር የተደረገዉ ጥረት ሊሳካ አልቻለም።
#TikvahFamilyHawassa
@tikvahethiopia

#AmharaRegion ° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ ° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች…
" ... በታሪኬ እንዲህ ያለ የስቃይ ጊዜ ገጥሞኝ አያውቅም !! " - ነዋሪ
ባለፉት 5 ዓመታት በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች " ግጭት ተፈጠረ፣ ጥቃት ተፈፀመ፣ ሰው ሞተ፣ ንብረት ወደመ ፣ ህዝብ ከገዛ ቄየው ተፈናቀለ " ሲባል መስማት የተለመደ ነው።
በሰሞነኛው ግጭት በርካቶች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ቄያቸውን ለቀው ሸሽተዋል።
አንድ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዬጵያ የሰጡ የአጣዬ ነዋሪ ፤ " እኛ ያልገባን ሰው እርስ በእርሱ ተላልቆ ምድሪቱን ባዶ ማድረግ ነው ወይ የተፈለገው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
መንግሥት ይህ ሁሉ ሲሆን ዘላቂ መፍትሄ ሊሰጥ አልቻለም ሲሉ በሀዘን የገለጹት ነዋሪው " የአንድ መንግሥት ዋና ስራው የህዝብን ደህነት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ሁሌም እንዲህ ያለ መከራ ሲወርድብን መኖራችን እጅግ ያሳዝናል " ብለዋል።
ሌላኛው በእድሜ የገፉ ነዋሪ በሰጡን ቃል ፤ " እኔ እዚሁ ተወልጄ ነው ህይወቴን የኖርኩት ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በታሪኬ እንዲህ ያለ የስቃይ ጊዜ ገጥሞኝ አያውቅም " ብለዋል።
" ሰዎች ይሞታሉ፣ ንብረት ይወድማል፣ የሚጠየቅ የሚቀጣ የለም። አንድ ጊዜ ተወርቶ ያልፋል። እኔስ አርጅቻለሁ ልጆቼ ግን እንዲህ ባለው ሁኔታ እንደሚኖሩ ሳስብ ልቤ ይሰበራል " ሲሉ አልቅሰው ተናግረዋል።
ሌላኛው ነዋሪ እርስ በእርስ መወነጃጀሉ እንደማይበጅ መንግሥት ግን መንግሥት ነኝ የሚል ከሆነ የፈለገውን አይነት መንገድ ተጠቅሞ ሰላም ማስፈን እንዳለበት ፣ በደህንነት ምክንያት ለሚጠፋው የሰው ህይወት ሁሉ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባው ገልጸዋል።
ካለፈው 9 ቀናት ጀምሮ በአጎራባች አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የንፁሃን ሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ቤቶች ተቃጥለዋል። ከብቶችም ተዘርፈዋል።
የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በአካባቢው ደህንነት መጥፋት የፋኖ ታጣቂዎችን ሲከስ ፤ የሰሜን ሸዋ ዞን ደግሞ በሽብርተኝነት የተፈረጀውን እና ታጥቆ የሚንቀሳቀሰውን " ሸኔን " ይፈርጃል።
ነዋሪዎች ደግሞ " ሸኔ " የሚባል ነገር እዚህ የለም፤ ያለው ገበሬ ነው ባይ ናቸው።
እስካሁን መንግሥት ያለው ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " ህዝቡ ' አለቅን ፣ ሰው ተጫረሰ፣ ንብረት ወደመ፣ ቤትም ተቃጠለ እያለን ነው ' እባካችሁ በዚህ ጉዳይ ምልስ ስጡን " በማለት ለአማራ ክልል ኃላፊዎች ስልክ ቢደውልም ፣ መልዕክት ቢያስቀምጥም እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

#Update " ቅዳሜ የመጨረሻው ገንዘቡን የመመለሻ ቀን ነው " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል። ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነውም ብሏል። በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ…
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ምን አለ ?
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር መጋቢት 6 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን የሲስተም ችግር ተገን በማድረግ #ተመዝብሯል ያለውን " የህዝብ ገንዘብ " አስመልክቶ መግለጫ አወጣ።
ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ላይ ችግር በተፈጠረበት ቅፅበት የነበረውን ክፍተት እንዴት እንዳገኙ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ መረጃ የደረሳቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሌሊቱን በሙሉ በመደዋወል ከአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች (ATM) ገንዘብ በመውሰድና ልዩ ልዩ ገንዘብ መክፈያና ማስተላለፊያ ማዕቀፎችን በመጠቀም የራሳቸው ያልሆነውንና በሂሳባቸው ውስጥ ያልነበረን ገንዘብ " ዘርፈዋል " ብሏል።
ከዚህ ባለፈ ደግሞ ፤ " የተፈጸመውን #ምዝበራ እንደ በጎ ተግባር ሁሉ በሁሉም የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በጀብድ መልክ ሲዘዋወር መመልከታችን ከፍተኛ ኃዘን አሳድሮብናል " ሲል ገልጿል።
የባንኮች ማህበሩ ፤ " ከማኅበረሰቡ በተሰበሰበ አንጡራ ገንዘብ በመንግሥት ከፍተኛ ወጪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ወደ ከፍተኛ ተቋማት /ዩኒቨርስቲ/ የተላኩ አፍላ #ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ከሆነው ነባር ዕምነት እና ባህል ባፈነገጠ ሥነምግባር ላይ ወድቀው መገኘታቸው ልብ የሚሰብርና አገራችን ካለባት ጊዜያዊ ችግሮች በላይ የሚያሳስብ አሳዛኝ ድርጊት ሁኖ አግኝተነዋል " ብሏል።
ድርጊቱንና የድርጊቱን ፈጻሚ እና ተባባሪ የሆኑትን አካላት ሁሉ ማኅበሩ በጽኑ #እንደሚያወግዝው ገልጾ ፤ እነዚህን መሠል ወጣቶች በተመሳሳይ ውድቀት ውስጥ እንዳይገኙ ለመከላከል ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርቧል።
በንግድ ባንክ ላይ የተፈጠረው ችግር እና ችግሩን ተገን አድርገው በባንኩ፣ በባንኩ ደንበኞችና በኅብረተሰቡ ላይ ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ እየተደረገ ባለው ሕጋዊ ማጣራት እና በቀጣይነት ወደ ህግ በማቅረብ በቂ ተመጣጣኝና አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ረገድ ፤ ሁሉም አባል ባንኮች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ጠቁሟል።
ሁሉ አቀፍ ትብብር ለህግና ጉዳዩ ለሚመለከታው ተባባሪ አካላት ለመስጥትም ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
#TikvahFamilyAddisAbaba

#ኢትዮጵያ
ከተፈጥሯዊ መንገድ ውጭ የሰው ልጅ በአንድም በሌላ መልኩ ሲገደል ሲገዳደል ፣ ሲሰቃይ ሲያሰቃይ ፣ ሲሰደድ እንዲሰደድ ምክንያት ሲሆን፣ በዚህች ኢኮኖሚያዋ ደካማ በሆነ ሀገር ለፍቶ ያፈራው ጥሪት በአንድ ሌሊት ዶግ አመድ ሲሆን ቀጣይ የሚፈጠረው ፦
- ቂም
- በቀል
- እርስ በእርስ ጥላቻ
- መጠፋፋት ብቻና ብቻ ነው። በሰዎች ውስጥ የሚያድረውን ይህንን አይነት አመለካከት መቀየር ደግሞ እጅግ ረጅም ጊዜ ይወስዳል።
አንድ ሰው በምንም አይነት መንገድ ይሁን ሲገደል ልጆች ፣ ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ፣ ዘመድ ፣ ጓደኞች እንዳሉት መረዳት ይገባል፤ እኚ ሁሉ የሚወዱትን ሲነጠቁ ምን አይነት ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል ? ብሎ መጠየቅ ይገባል።
እነዚህ አካላት ሁሉ ተደምረው ነው ማህበረሰብ የሚፈጠረው።
እርግጥ ነው የሰዎች ሞት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአንድ ቀን ወሬ ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ለወለደች እናት፣ ላሳደገ ቤተሰብ፣ ለጓደኛ ለማህበረሰብ፣ ህመሙ መቼም ሊጠፋ አይችልም። በየአጋጣሚው ሁሉ ይህን የሚወዱትን ሰው እና አሟሟቱን ሲያስታውሱት ሲናገሩት ይኖራሉ።
በየትኛውም አካል የሰው ነፍስ ሲጠፋ ያንን ሰው የተነጠቁ ወላጆች፣ ቤተሰብ ማህበረሰብ በዛ ነፍስን ባጠፋው አካል ላይ ጥላቻቸው እየጨመረ ይመጣል። ይህ ነገ ሌላ ችግር መውለዱ ግልጽ ነው።
ልጃቸውን ለተነጠቁ አካላት በማንም ምንም ነገር ቢደረግላቸው፤ ቃል ቢገባላቸው የተነጠቁትን ነፍስ አይመልሰውምና በጎ እሳቤያቸው ይቆማል። ነገር ሁሉ ይበላሻል።
ተጎጂዎችን ሊያፅናና ሊክስ የሚችለው ብቸኛው መንገድ ነገ ሌላውም ወገን በግፍ እንዳይገደል ፣ እንዳይሰቃይ ማድረግ እና ፍትህን ማስፈን፣ ወንጀለኛን መቅጣት ብቻ ነው።
የሚወዱትን ተነጥቀው ፣ ተሰደው ፣ ከሞቀው ቄያቸው በግፍ ተፈናቅለው ሜዳ የወደቁ ፍትህ ያልተሰጣቸው የተጎዱ ሰዎች እንዴት በጎ ነገር ሊያስቡ ፤ በጎ ነገር ተደረገላችሁ ሲባሉ ሊያወድሱ ይችላሉ ? መጠበቅም ነውር ነው።
ሰዎች በአንድ ለሊት ከመሬት ተነስተው ለሆነ ነገር / ለሆነ ጉዳይ ጥላቻ በውስጣቸው ሊያድር አይችልም። በጊዜ ሂደት የሚያዩት የሚሰሙት ነገር ሁሉ አመለካከታቸው ላይ ትልቅ ተፅእኖ አለው።
ስለዚህም ፤ ባለፉት ዓመታት ደግመን ደጋግመን ስንል እንደነበረው የሰው ልጅ ክቡር ነውና እንዳይጎዳ እንዳይሰቃይ ለሀዘን እንዳይዳረግ ከልብ መስራት ይገባል።
ሰው በሞተ ቁጥር ደስታ ሳይሆን ሀዘን ፣ ቂም ፣ ጥላቻ እየተወለደ ይሄዳል። ይህ ደግሞ ነገ ሌላ ችግር እየወለደ የአዙሪት ህይወትን እንድንመራ ያደርጋል።
ቢያንስ የሞቱትን መመለስ ባይቻል ሌላ ሰው ህይወቱ እንዳይጠፋ፣ እንዳይጎዳ፣ እንዳይሰቃይ፣ እንዳያዝን ማድረግ ፤ ተበዳይን ፍትህ በመስጠት መካስ ይገባል።
ከዚህ በላይ ሁሉን አቀፍ ፍፁም እውነተኛ ዘላቂ እርቅ መፈለግም የግድ ነው።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት
2016 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ከተፈጥሯዊ መንገድ ውጭ የሰው ልጅ በአንድም በሌላ መልኩ ሲገደል ሲገዳደል ፣ ሲሰቃይ ሲያሰቃይ ፣ ሲሰደድ እንዲሰደድ ምክንያት ሲሆን፣ በዚህች ኢኮኖሚያዋ ደካማ በሆነ ሀገር ለፍቶ ያፈራው ጥሪት በአንድ ሌሊት ዶግ አመድ ሲሆን ቀጣይ የሚፈጠረው ፦
- ቂም
- በቀል
- እርስ በእርስ ጥላቻ
- መጠፋፋት ብቻና ብቻ ነው። በሰዎች ውስጥ የሚያድረውን ይህንን አይነት አመለካከት መቀየር ደግሞ እጅግ ረጅም ጊዜ ይወስዳል።
አንድ ሰው በምንም አይነት መንገድ ይሁን ሲገደል ልጆች ፣ ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ፣ ዘመድ ፣ ጓደኞች እንዳሉት መረዳት ይገባል፤ እኚ ሁሉ የሚወዱትን ሲነጠቁ ምን አይነት ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል ? ብሎ መጠየቅ ይገባል።
እነዚህ አካላት ሁሉ ተደምረው ነው ማህበረሰብ የሚፈጠረው።
እርግጥ ነው የሰዎች ሞት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአንድ ቀን ወሬ ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ለወለደች እናት፣ ላሳደገ ቤተሰብ፣ ለጓደኛ ለማህበረሰብ፣ ህመሙ መቼም ሊጠፋ አይችልም። በየአጋጣሚው ሁሉ ይህን የሚወዱትን ሰው እና አሟሟቱን ሲያስታውሱት ሲናገሩት ይኖራሉ።
በየትኛውም አካል የሰው ነፍስ ሲጠፋ ያንን ሰው የተነጠቁ ወላጆች፣ ቤተሰብ ማህበረሰብ በዛ ነፍስን ባጠፋው አካል ላይ ጥላቻቸው እየጨመረ ይመጣል። ይህ ነገ ሌላ ችግር መውለዱ ግልጽ ነው።
ልጃቸውን ለተነጠቁ አካላት በማንም ምንም ነገር ቢደረግላቸው፤ ቃል ቢገባላቸው የተነጠቁትን ነፍስ አይመልሰውምና በጎ እሳቤያቸው ይቆማል። ነገር ሁሉ ይበላሻል።
ተጎጂዎችን ሊያፅናና ሊክስ የሚችለው ብቸኛው መንገድ ነገ ሌላውም ወገን በግፍ እንዳይገደል ፣ እንዳይሰቃይ ማድረግ እና ፍትህን ማስፈን፣ ወንጀለኛን መቅጣት ብቻ ነው።
የሚወዱትን ተነጥቀው ፣ ተሰደው ፣ ከሞቀው ቄያቸው በግፍ ተፈናቅለው ሜዳ የወደቁ ፍትህ ያልተሰጣቸው የተጎዱ ሰዎች እንዴት በጎ ነገር ሊያስቡ ፤ በጎ ነገር ተደረገላችሁ ሲባሉ ሊያወድሱ ይችላሉ ? መጠበቅም ነውር ነው።
ሰዎች በአንድ ለሊት ከመሬት ተነስተው ለሆነ ነገር / ለሆነ ጉዳይ ጥላቻ በውስጣቸው ሊያድር አይችልም። በጊዜ ሂደት የሚያዩት የሚሰሙት ነገር ሁሉ አመለካከታቸው ላይ ትልቅ ተፅእኖ አለው።
ስለዚህም ፤ ባለፉት ዓመታት ደግመን ደጋግመን ስንል እንደነበረው የሰው ልጅ ክቡር ነውና እንዳይጎዳ እንዳይሰቃይ ለሀዘን እንዳይዳረግ ከልብ መስራት ይገባል።
ሰው በሞተ ቁጥር ደስታ ሳይሆን ሀዘን ፣ ቂም ፣ ጥላቻ እየተወለደ ይሄዳል። ይህ ደግሞ ነገ ሌላ ችግር እየወለደ የአዙሪት ህይወትን እንድንመራ ያደርጋል።
ቢያንስ የሞቱትን መመለስ ባይቻል ሌላ ሰው ህይወቱ እንዳይጠፋ፣ እንዳይጎዳ፣ እንዳይሰቃይ፣ እንዳያዝን ማድረግ ፤ ተበዳይን ፍትህ በመስጠት መካስ ይገባል።
ከዚህ በላይ ሁሉን አቀፍ ፍፁም እውነተኛ ዘላቂ እርቅ መፈለግም የግድ ነው።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት
2016 ዓ/ም
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ቅዳሜ የመጨረሻው ገንዘቡን የመመለሻ ቀን ነው " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል። ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነውም ብሏል። በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ…
#Update
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባንኩ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱ ግለሰቦች በዲጂታል የክፍያ አማራጭ መመመለስ ይችላሉ አለ።
ባንኩ ፤ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ እና ያዘዋወሩ ሰዎች እስክ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
ዛሬ ምሽት ባወጣው መልዕክት ደግሞ ፤ " ያለ አግባብ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም በቀጥታ ቀድሞ ገንዘቡ አለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንካችን የሚገኝ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፍ (#transfer) እና ገቢ ማድረግ ይችላሉ " ብሏል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 የማይመልሱ ግለሰቦችን ደረጃ በደረጃ በህግ አግባብ እንደሚጠይቅ ስማቸውንና ፎቶግራፋቸውንም በሚዲያ እንደሚያሰራጭ አስጠንቅቋል።
አርብ መጋቢት 6 ለሊት ከባንኩ ሲወጣ ያደረው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም ባንኩ በተደጋጋሚ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ያወጡ ሰዎች ገንዘቡን እንዲመልሱ እያሳሰበ ይገኛል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥርዎን መጠቀም ይችላሉ።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ የ9% ወለድ፣ አነስተኛ ብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ያግኙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#ቤቲንግ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ነገ ከጥዋቱ 2:30 ላይ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች ጋር ሊመክሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል። ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጀሁት ባለው የምክክር መድረክ ላይ ፤ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ጥዋት 2:30 ላይ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል የስብሰባ…
#ቤቲንግ
➡️ " ቤቲንግ ቤቶች ዳግም #እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡ አሳስቦናል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
➡️ " ሁሉንም ቤቶች በጅምላ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ህጉን ተከትለው የሚሰሩና ብዙ ሰራተኛ ያላቸው ቤቲንግ ቤቶች አሉ " - የቤቲንግ ቤት ባለቤቶች
በአዲስ አበባ ከተማ በቤቲንግ ቤቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ ሲካሄድ በነበረ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ተሰምቷል።
ውይይቱ የተደረገው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተቋቋመው ግብረሃይል አማካይነት ባለፈው ጊዜ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ የተገኙ የቤቲንግ ቤቶች በጥናት ተመስርቶ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን ገልጿል።
በዚህም፦
1ኛ. አብዛኛው ቤቲንግ ቤቶች በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ላይ በመሆናቸው፣
2ኛ. የብሔራዊ ሎቶሪ ባወጣውን ደንብ መሠረት ዕድሜያቸው ከ21ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ገብተው ሲጫወቱ በመገኘታቸው፣
3ኛ. በቤቶቹ ውስጥ አዋኪ ድርጊቶች ማለትም፦ ጫት መቃም፣ አልኮል መጠጦች መጠጣት...ወዘተ ሲፈፀምባቸው በመገኘታቸው፣
4ኛ. ያለንግድ ፈቃድ ሲሰሩ በመገኘታቸው፣
5ኛ. የቡድን ፀብ የተከሰተባቸው መገኘታቸው ለመዘጋታቸው ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።
ቢሮው፤ " ሕብረተሰቡም በቤቲንግ ቤቶች ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድተናል " ብሏል።
ቢሮው ፤ ከዘርፉ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ አመዝኖ እንደሚታይ ፤ ቤቲንግ ቤቶች ዳግም እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡም አሳስቦናል ሲል አሳውቋል።
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች የታሸጉ የቤቲንግ ቤቶች ፦
1ኛ. ለቤቲንግ ቤት ያከራዩ የቤት ባለቤቶች የንግድ ዘርፉን ቀይረው ከመጡ፣
2ኛ. " አገልግሎቱን አንፈልግም ካሁን ቀደም ሳናውቅ ስለገባንበት ከዚህ በኋላ አንሠራም " ብለው ማረጋገጫ ለሚሠጡና ቤቶቹ ተከፍተው ለሌላ አገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል ሲል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
በሌላ በኩል፤ በአዲስ አበባ ስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ በመንግስት ከታሸገ 3 ወር ሆኖታል የሚሉ በዘርፉ ላይ ያሉ አካላት ፤ ትክክለኛ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነና በየ ወረዳው የሚነገራቸው የተለያየ ሃሳብ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
" ዘርፍ ቀይሩ ወይንም ዕቃ አውጡ እየተባልን ነው ፤ ብሄራዊ ሎተሪ እንደሚከፍትልን እና ዝግጅት እንድናደርግ ብሎም እድሳት አድርጎ ፍቃዳችንን ከሰጠ በኋላ ነው እንዲ የተጉላላነው " ብለዋል።
" በስራችን ብዙ ሰራተኞችን የያዝን እና ከፍተኛ ግብር ለሀገራችን የምናስገባን ድርጅቶች ማንገላታት አግባብ አይደለም " የሚሉት የዘርፉ ባለቤቶች " ስራ በሌለበት ወቅት ብዙ ስራ አጦች በከተማችን ባሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ስራ አጦች እንድንሆን እየተደረግን ነው " በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።
" ቤቲንግ መስራት ሲገባቸው አለአግባብ ከህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ካሉ በህግ መጠየቅ እንጂ ሁሉንም በአንድ መፈረጅ አይገባም " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቤቲንግ ቤቶች እስከ ወዲያኛው እንዲዘጉ ጫና እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
የዘርፉ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " በአጠቃላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጎ ከእምነት ተቋማት ፣ ከትምህርት ቤት መራቅ ያለበትን ርቀት ተከትሎ እድሜ ከ21 አመት በላይ ብቻ እንዲጠቀም ተደርጎ ቢቀጥል ለሀገርም ለህዝብም ጥቅም ይኖረዋል " ብለዋል።

#AmharaRegion #Gojjam ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል። የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272…
#Update
" 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ
ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል ቀጣሪው ድርጅት ገለጸ።
የቀጣሪው ድርጅት ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ ላለፉት 24 ቀናት ታግተው የሚገኙትን 272 #የቀን_ሰራተኞች ጉዳት ሳያገኛቸው ለማስለቀቅ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ/ም 4 ሚሊዮን ብር በተለያዩ 3 ሰዎች አማካኝነት ክፍያ ፈፅመናል ብለዋል።
አቶ ሙልጌታ ፤ " ገንዘቡን #ተቀበሉን ከዛም ለቀቋቸው ከለቀቋቸው በኃላ እንደገና ጎዛመን የሚባል ቦታ ላይ ለዋናው አስፓልት 5 ኪ/ሜ ሲቀር እንደገና ሌላ ኃይል መልሶ ያዛቸው። ... የውሸት የውሸት ፖለቲካ የእውነት አምላክ ይፍረድልን ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድልን " ሲሉ ተናግረዋል።
" 4,000,000 ብር (4 ሚሊዮን) ነው #የከፈልናቸው " ያሉት አቶ ሙልጌታ ፤ " የከፈልኩበት ሰነድ በእጄ አለ ፤ በ3 ሰው ስም ነው የገባው። ' አስገባ ' ተባልኩኝ አስገባሁ ተለቀቁ እንደገና ከተለቀቁ በኃላ ሌላ ቡድን ያዛቸውና ለእያንዳንዱ መኪና አሁን 1,500,000 ብር ተጠይቋል ፤ ልጆቹን ለቀይ መስቀል ነው አሳልፈን የምንሰጠው ብለውን እየጠበቅን ነው " ብለዋል።
መጋቢት 1 ተለቀው እና ድጋሚ ተይዘው ከሆነ ከቀናት በፊት ቃለ ምልልስ በሰጡበት ወቅት ይህን ገንዘብ ለአጋቾቹ #መክፈላቸውንና ተለቀው መያዛቸውን ለምን እንዳልተናገሩ ተጠየቀው ፤ " አንደኛ የነበርኩት እዛው አካባቢ ነው ለደህንነቴ አስቸጋሪ ነበር። ሁለተኛ ደግሞ ልጆቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረኩ ነበር በዛ የተነሳ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
ስራ አስኪያጁ ፤ ሰራተኞቹ #ከእገታው_ተለቀው መሄድ ከጀመሩ በኃላ በድጋሚ በቡድኑ ሌላ ክንፍ የተያዙት እዛው በምስራቅ ጎጃም ፣ ማቻከል ወረዳ አማኑኤል አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።
ሲጓዙበት የነበረ 4 ተሽከርካሪ ቁልፍም በታጣቂዎች መወሰዱን ገልጸዋል።
6 ሚሊዮን ብር ማስለቀቂያ መጠየቁን አመልክተዋል።
' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ' እንደሆኑ የገለጹት ፋኖ ማርሸት ፀሀይ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ጥያቄ አላቀረብንም ፤ ገንዘብም አልተቀበልንም ፣ ድርጅቱ ስም ማጥፋት ነው የያዘው ብለዋል።
ፋኖ ማርሸት " ይሄ ኒኮቲካ የሚባለው የኮንስትራክሽን ድርጅት የፋኖን ስም በዓላማ እያጠፋ ያለ ተቋም ነው። ምርኮኞች የተያዙት በ4ኛው ክ/ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና ነው። ክፍለ ጦራችን #አማኑኤል / ማቸከል፣ ጎዛመን እስከ ደ/ማርቆስ እና ልጆቹ አሁን ያሉበትን በረሃ ያጠቃልላል። ስለዚህ በዚህ ቀጠና እስካሉ የኛ ሙርከኞች ናቸው " ብለዋል።
" #ገንዘብ_የጠየቀ_አካል_የለም። ተጭነውባቸው ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የመጡባቸው የአውቶብሶቹ ባለቤቶች (4 አውቶብሶች) ' አውቶብሶቻችን ስጡን ' ሲሉ አንሰጥም የሚል መልስ ሲሰጣቸው ' ለፋኖ ገንዘብ እንስጥና ድጋፍ አድርገን አውቶብሶቻችን ይመለሱ ' አሉ እኛ የገንዘብ ችግር የለብንም ፤ ገንዘብ አንጠይቅም አውቶብሶቹ ግን ቀይ መስቀል መጥቶ ልጆቹን ሲረከብ ተጭነው የሚሄዱባቸው ናቸው ብለን አቆይተናል " ብለዋል።
ልጆቹ ከነበሩበትም #እንዳልተንቀሳቀሱ ፣ ኒኮቲካም ሊቀበል እንዳልመጣ ገልጸው ድርጅቱ " የፋኖን ስም እያጠፋነው " ሲሉ ከሰዋል።
" እነዚህ ልጆች ታጋቾች ሳይሆኑ #ምርኮኞች ናቸው። ምርኮኞቹን ደግሞ ለቀይ መስቀል የምናስተላልፍበት ምክንያት ፦
1. እኛ ተንቀሳቃሽ ኃይል ስለሆንን፣
2. ለነሱ የምንመግበውን ምግብ ለወታደራችን ማዋል ስላለብን ፣
3. ዓለም አቀፍ የጦርነት ህግን አክብረን የምንዋጋ የነፃነት ታዋጊዎች / ኃይሎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው " ብለዋል።
እስካሁን ቀይ መስቀል እንዳልመጣ በአካል ከመጡ እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።
የተያዙት ደግሞ ድርጅቱ እንዳለው " 272 " ሳይሆኑን 246 ብቻ ናቸው ብለዋል።
ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን አሁን ጉዳዩ ከእኛ ከአቅማችን በላይ ነው ሲል አሳውቋል።
አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ " ለሚመለከተው ሁሉ ስራውን ለሚያሰራን ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በፅሁፍ አሳውቀናል ምንም መፍትሄ የለም #የድሃ_ልጅ ነው እየተሰቃየ የሚገኘው " ሲሉ ተናግረዋል።
" የአማራ ህዝብ እውነቱን ብቻ አይቶ ይዳኘን ፣ እነዚህ ወንድም ህዝቦች ናቸው የመጡት ለስራ ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰራተኞቹን ጉዳይ እንደሚያውቅ ፣ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ጋር በመሆን እየሰራበት እንደሆነ ገልጾ ለጊዜው ለታጋቾች ደህንነት ሲባል ከዚህ በላይ አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ ሬድዮ /ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ ማግኘቱን ያሳውቃል።

" ' ሳር ቤት አካባቢ በአውቶብስ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ' እየተባለ በቲክቶክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።
ፖሊስ ፤ የከተማው ሰላም መሆን እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስጋት ላይ ለመጣል በቻሉት መጠን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
እነዚህ አካላት ህዝቡ ደህንነት እንዳይሰማውና ከተማውም ሰላም አንደሌለው ለማሳየት ብዙ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው የፈጠራ ሀሰተኛ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ይዘው መጥተዋል ሲል ገልጿል።
ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ #ቦንብ_ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።
" ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ ነው " ያለው ፖሊው ሁሉም የከተማው ነዋሪ ይህን ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።
ፖሊስ ፤ የከተማዋን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሌት ተቀን ህልማቸውን " ቲክ ቶክ /#TikTok " በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየገለፁ ናቸው ብሎ " በአዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ አሳስቧል።
ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይም በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።

በውጭ አገር ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመድዎ በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር አለም አቀፍ ሃዋላ የተላከልዎትን ገንዘብ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የቴሌብር ወኪል ሲቀበሉ የ 10% ስጦታ እንሸልምዎታለን !
ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3ArwoEO
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ " በግል ምክንያት " በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።
ኮሚሽኑ የአምባሳደር ተሾመን ከኃላፊነር መልቀቅ በተመለከተ ፤ " በግል ጉዳያቸዉ ምክንያት በኮሚሽነርነት ላለመቀጠል ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ከመጋቢት 3/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለቀዋል " ብሏል።
በኮሚሽነሩ ምትክ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የውጭ ፖሊስ አማካሪ አቶ ተመስገን ጥላሁን መተካታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተሾሙት ባለፈው ዓመት ጥር 2015 ዓ.ም. ነበር። ያለፈውን 1 ዓመት የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከለጋሽ አካላት ለማሰባሰብ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
በኢህአዴግ ዘመን ጉምቱ ከሚባሉት ባለስልጣን አንዱ የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፤ ከ1997 እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፤ ከዚህ ባለፈ የወጣቶች፣ ባህል እና ስፖርት እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ፣ በኃላም በዲፕሎማትነት ሰርተዋል።