TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.8K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወጣትነት በዘህራህ ልዩ ከወለድ ነጻ የሴቶች ቁጠባ ሒሳብ ሲታገዝ፣ የስኬት ጉዞ ከመቼውም ይልቅ ይፋጠናል!

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#Ethiopia #Turkiye

ከቱርኪዬ የመጡ የሀኪሞች ቡድን በቅዱስ ጳዉሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት 3 የኩላሊት ንቅለ ተከላ በተሳካ ሁኔታ እንዳካሄዱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን የተመራ ልኡካን ቡድን የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለማቋቋም የሚስችል ፕሮጀክት ላይ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ተወያይተው ነበር።

የህክምና ባለሙያዎቹ ቡድን ላደረጉት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል።

#MoH

@tikvahethiopia
#Ethiopia❤️

ኢትዮጵያ 🇪🇹 ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን አጠናቀቀች !

በቻይና ናንጂንግ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያ አምስት ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ አጠናቀቀች።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ ፦

  ሁለት የወርቅ እና
ሶስት የብር ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ለተከታታይ አራት አመታት የወርቅ ሜዳልያውን ማሸነፍ ችላለች።

ኢትዮጵያ በውድድሩ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ 1️⃣ኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ ከአለም 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሜዳልያ ያስገኙ አትሌቶች እነማን ናቸው ?

🥇 ጉዳፍ ፀጋይ ( 1500 )

🥇 ፍሬወይኒ ኃይሉ ( 3000 )

🥈 በሪሁ አረጋዊ ( 3000 )

🥈 ንግሥት ጌታቸው ( 800 )

🥈 ድርቤ ወልተጂ ( 1500 )

Via
@Tikvahethsport  
#አቢሲንያ_ባንክ
በረቀቀ ቴክኖሎጅ የተዘጋጀውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ
- በ5 የቋንቋ አማራጭ
- ከአቢሲንያ ወደ አቢሲንያ አካውንት ያለምንም ክፍያ እና ያለገደብ ገንዘብ ለማስተላለፍ
- ኪውአር ስካን አገልግሎት
ለማግኘት ዛሬውኑ ወደ አቅራቢያዎ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን ያግኙ #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ

ገደቡም ክፍያውም ተነስቷል!

ውድ ደንበኛችን! የባንካችንን አዲሱን የሞባይል መተግበሪያ ተጠቅመዉ ከሂሳብዎ ወደ ሌላ የባንካችን ሂሳብ ገንዘብ ያለ ገደብ እንዲሁም ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይችላሉ። #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Ethiopia #Kenya

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል።

በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው።

በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ነው።

ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል።

ይህ ስምምነት የንግድ ዋጋ ጣሪያዎችን፣ የጉዞ ድግግሞሽን እና የድንበር ንግድ ዞኖችን የመሳሰሉ ጉዳዮችን በመዳሰስ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር የተገኘ ውጤት ነው ተብሏል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
በረቀቀ ቴክኖሎጅ የተዘጋጀውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ
- በ5 የቋንቋ አማራጭ
- ከአቢሲንያ ወደ አቢሲንያ አካውንት ያለምንም ክፍያ እና ያለገደብ ገንዘብ ለማስተላለፍ
- ኪውአር ስካን አገልግሎት
ለማግኘት ዛሬውኑ ወደ አቅራቢያዎ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን ያግኙ #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#አቢሲንያ_ባንክ
የሁሉም ምርጫ !


ሸሪዓውን መሠረት አድርገውና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አካተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሰከረለት የአይማል ኮር ባንኪንግ ሲስተም እየታገዙ ዳጐስ ያሉ ጥቅሞችን ለአስቀማጮች የሚያስገኙትን፤ የሴቶች (ዘህራህ)፣ የወጣቶች (ፊትያህ)፣ የባለውለታዎች (ሙስኒን)፣ የሃጅ እና ዑምራ፣ የዕድር (ጀሚአህ)፣ የዕቁብ (ሱንዱቅ) እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሙዷረባህ ትርፍ አጋሪ ሂሳቦችን በመክፈት፤ ከባንካችን ጋር ኢንቨስት አድርገው በተሻለ ትርፍና በከፍተኛ ጥቅም የወደፊት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Ethiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ነው።

ምክር ቤቱ " ይህ የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር መዘርጋቱ ፦
- የውጭ ካፒታል በሀገራችን ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት፣
- የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣
- የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ
- ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል " ብሏል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ሌላ ከወሳናቸው ጉዳዮች አንዱ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳን ለማስፈፀም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።

" ስምምነቱ በአባል ሀገራት መካከል ንግድ እንዲስፋፋ፣ የገበያ ትስስሩ እንዲጠናከር፣ የእሴት ሠንሰለቱ እንዲጎለብት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማበረታታት የሚያስችል ነው " ብሏል።

" በአባል ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በታሪፍ ምክንያት ሳይደናቀፉ የእቃዎች ፍሰት የተሳለጠ እንዲሆን ከአባል አገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን በመወያዬት ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን " ሲል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

(ተጫማሪ ምክር ቤቱ የወሰናቸውን ውሳኔዎች ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia