TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ABH ምላሽ ሰጠ!

“ኤጀንሲው ሕግን መሰረት ሳያደርግ ለፈጸመው ስህተት #ይቅርታ ይጠይቀን”–ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ/የኤቢኤች ዋና ሥራ አስፈጻሚ
.
.
ሰኞ ነሐሴ 13/2011 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው የጅማ የኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ካምፓስ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኤቢኤች ፓርትነርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ እንደተናገሩት “እኛ ሕግን ተከትለን እየሰራን ነው፤ ኤጀንሲውም በአዋጅ የተሰጠንን ስልጣን በፌስቡክ አይሽርም፤“ ብለዋል፡፡ “በመገናኛ ብዙሃን የተገለፀው ጉዳይም፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ስም የሚያጎድፍና የተሳሳተ እንደሆነም” ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲን እንደገና ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ አዋጅ 240/2003 አንቀጽ ሶስትን ጠቅሰው የተናገሩት ዶ/ር ማርቆስ፣ “የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ጅማ ሆኖ በሌሎች ቦታዎች ላይ የትምህርት ክፍሎችና የምርምርና የሕብረተሰብ አገልግሎት ሊያቋቁም እንደሚችል” አብራርተዋል፡፡

Via #MollaMultimedia

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ABH-08-19
አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት #ዋና_አፈ_ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት #ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።

የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛውም መመዘኛ #ትክክል አይደለም ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ በቀጣይ ተመሳሳይ #ስህተት እንደማይደገም በምክር ቤቱ ፊት ቃል እገባለሁ ብለዋል። በእርግጥ እንደምክንያት ማቅረብ ባይቻልም ምክር ቤቱ ማድረግ የነበረበትን መደበኛ ጉባኤዎች ሳያካሂድ የቀረው ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ የተነሳ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዓመት #አራት መደበኛ ጉባኤዎችን ማድረግ የሚገባው ቢሆንም ባለፈው የጥቅምት ወር የመጀመሪያውን ስብስባ ካደረገ ወዲህ ዳግም ሳይሰበሰብ ነው የበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው። በዚህም ምክንያት የክልሉ ዓመታዊ በጀት እስከአሁን ባለመፅደቁ የአስፈጻሚ ቢሮዎች ከሀምሌ 1 2012 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስራዎቻቸውን በምክር ቤት ባልጸደቀ በጀት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 329 ታራሚዎች #ይቅርታ ተደርጓል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው በወረቀት እንዲሰጥ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ታብሌቶች ወደ ሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየት በይፋ #ይቅርታ መጠየቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ይቅርታ

" ባቀድነው ልክ ውጤታማ ባለመሆናችን የ ኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ " - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ ዋንጫው ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያን የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ቆይታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን " ባቀድነው ልክ ውጤታማ ባለመሆናችን የ ኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ብለዋል።

አክለውም ፥ " የአሰልጣኙን ኮንትራት እናከብራለን ፣ እስከ ኮንትራቱ መጨረሻ አብሮን ይቀጥላል ብለን እናምናለን " ሲሉ ተናግረዋል ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በበኩላቸው ፥ " ስንሄድም ስንመጣም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው አልተደበቅንም ፣ ብሄራዊ ቡድኑ ኩራት ነው ፣ በ ማህበራዊ ገፆች እንደተመለከትነው ድንጋይ ይዞ የተቀበለን ሰው የለም " ብለዋል።

" እስከ መስከረም 30/2015 ከ ፌዴሬሽኑ ጋር ኮንትራት አለኝ " ያሉት አሰልጣኙ እስከዛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ነኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ከ8 ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ቢመለስም ምድቡን ማለፍ ሳይችል በመቅረቱ የመጀመሪያ ተሰናባች ሆኖ ከቀናት በፊት ወደ ሀገሩ መመለሱ ይታወቃል።

More : @tikvahethsport
ኢትዮ ቴሌኮም ምን አጋጠመው ?

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት እክል አጋጥሞት እንደነበር አስታወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም በአንደኛው ዋና ጣቢያው (core site) ላይ ባጋጠመው የውስጥ የኃይል አቅርቦት ቴክኒካል ችግር ምክንያት በከፊል ደንበኞቹ ላይ የአገልግሎት መቆራረጥ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ለተፈጠረው ችግር #ይቅርታ የጠየቀው ኢትዮ ቴሌኮም ችግሩ የተፈታ መሆኑን አሳውቋል።

ዛሬ በከሰዓት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቴሌኮም አገልግሎት የሚያገኙ የድርጅቱ የተለያዩ ደንበኞች ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ አለመስራት፣ ስልክ ለመደወል አለመቻል ፣ SMS ለመላክ አለመቻልን ጨምሮ ሙሉ የአገልግሎት እክል አጋጥሟቸው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ለመረዳት ችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ስምምነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመውን ፈተና ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ፦

1. በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፤ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር። ለዚህም ከዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

2. በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናት ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮችና በአገልግሎት እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከበፊቱ በበለጠ ተገቢው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

3. በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚያገለግሉ ቋንቋውን የሚያውቁ አገልጋዮችን የሚያሠለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ፣ የተከፈቱትም እንዲጠናከሩ እንዲደረግ።

4. ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በቂ የሆነ የኦሮምኛ ቋንቋን የሚያውቁና በቋንቋው የሚያገለግሉ ኤጲስቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾሙ፡፡

5. ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሀገረ ስብክታቸውና የክነት ማዕረጋቸው እንዲመለሱ።

6. በሦስቱ አባቶች የተሾሙት አባቶች ቀድሞ ወደነበሩበት የክነት ማዕረግ ይመለሳሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት እንደገና በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሾሙ ይደረጋል።

7. በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት የወንጌል አገልግሎትን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።

8. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከርና ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖረን ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን፡፡

9. ጥላቻን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፋ፣ ጥላቻን ከሚያበዛና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲቆጠቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትንም እናወግዛለን።

10. የገጠመን ፈተና ይበልጥ ውስጣችንን ለመፈተሽ፤ አንድነታችንን ለማጠናከር፤ ወንጌልን የበለጠ ለመስበክና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስፋፋት ለበጎ እንጠቀምበታለን።

በመጨረሻም #ፍቅር#ይቅርታ እና #አንድነት እንዲመጣ የደከማችሁትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም እናመስግናለን። ዋጋችሁንም እግዚአብሔር እንዲከፍላችሁ እንጸልያለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፈተናው በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ። ይህን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ11ዱ…
#Update

" ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች

" ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።

ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ ከዋሉ በኃላ " ፈተናው ቀርቷል " መባላቸውን ገልጸዋል።

ሰራተኛው ይሰጣል የተባለውን ፈተና ሲጠባበቅ ከዋለ በኃላ አንድም ግልፅ ምክንያት ሳይነገር አመሻሽ ላይ " ቀርቷል " መባሉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

" ለተፈጠረው መጉላላትና የስነልቦና ጉዳት ማነው ተጠያቂው ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

ፈተናው ለምን እንደቀረ በይፋ የተሰጣቸው ማብራሪያ እንደሌለ ሰራተኞቹ አክለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለ " ካፒታል ጋዜጣ " ቃላቸው የሰጡ የመንግሥት ሰራተኞች በመፈተኛ ቦታቸዉ ተገኝተው ሳይፈተኑ ለረዥም ሰዓታት በፌዴራል ፖሊስ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ 4 እና 5 ኪሎ ለመፈተን ወደ ተቋሙ ከ6:30 ጀምሮ በተመደቡበት መፈተኛ ክፍል ቢደርሱም እስከ ቀን 11:30 ድረስ ከፌዴራል ፖሊስ በስተቀር ማንም ፈታኝ ባለመምጣቱ ከረዥም ሰዓታት እንግልት በኃላ እንዲበተኑ ተደርገዋል።

በቅርቡ ለሚተገበረዉ የሰራተኞች ድልድል ሲባል ከ14 ሺህ በላይ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ለፈተና እንደሚቀመጡ መነገሩ ይታወቃል።

- የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር፣ 
- ቤቶች ልማት እና አስተዳደር፣
- ትራንስፖርት፣
- ፐብሊክ ሰርቨሲ እና ሰው ሀብት ልማት፣ 
- ፕላን እና ልማት፣ 
- ሥራ እና ክህሎት፣
- ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች
- ቤቶች ኮርፖሬሽን ጨምሮ አጠቃላይ ከ13 ሺህ በላይ ሰራተኞች ፈተናዉን አልወሰዱም።

በወቅቱ ረዥም ሰዓታት ፈተናዉን በመጠባበቃቸዉ ምክንያት የጩኸት ድምፅ ያሰሙ ሰራተኞች ለእስር መዳረጋቸውን እና የተለያዩ እንግልቶች እንደደረሰባቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል።

በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ፈተናው ወደሌላ ቀን መራዘሙን እንደሰሙ ሰራተኞቹ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ መነገሩ ይታወሳል።

ተጨማሪ . . .

የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናውን እንደሚያዘጋጁ ከተገለፁት ሁለት ተቋማት አንደኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው #መሰረዙን በደብዳቤ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦
* ለአመራሮች፣
* ባለሙያዎች
* ሰራተኞች ፈተና እንዲሰጥ ኃላፊነት እንደተሰጠ አስታውሷል።

ሆኖም በተከሰተ " የፈተና ቴክኒካዊ ችግር " ምክንያት በ12/04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ፈተና መሥጠት እንዳልተቻለ ከይቅርታ ጋር ገልጿል።

የተዘጋጀው ፈተና ደህንነት ችግር ያላጋጠመው መሆኑን ግን አመልክቷል።

በማንኛውም በጋራ በመስማማት ቀን ይሄንኑ ፈተና ለመሥጠት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባገኘው መረጃ አስተዳደሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቅርብ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች " ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ…
#AddisAbaba #ፈተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦

" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦
* ለአመራሮች ፣
* ለባለሙያዎች
* ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት ሰጥቷል።

ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ #ይቅርታ ጠይቋል።

ቀጣይ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ #በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ " ኢቲ106 " የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " ችግር እንዳጋጠመው ይታወቃል።

ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

- የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።

- ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።

- ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።

- ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።

- ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።

Video Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጡን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው አሳውቋል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በርብርብ እየተሰራ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

ለተፈጠረው መጉላላትም #ይቅርታ ጠይቋል።

ከአንድ ወር ገደማ በፊት በፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ሁሉም አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደነበር እና በሰዓታት ውስጥ ችግሩ መፈታቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ወይም አልፎ አልፎ ለተወሰኑ ሰዓታት #እየተቋረጠ እንደሚገኝ አመልክቷል።

" የመስመር ማዛወር ሥራዎቹ በጥንቃቄና በፍጥነት ለማከናወንና አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው " ያለ ሲሆን ነዋሪዎች ይህን ተረድተው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ለአገልግሎት መስተጓጎሎችም #ይቅርታ ጠይቋል።

በሌላ በኩል፥ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

በዚህም፦
ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

@tikvahethiopia