ስለአዲሱ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ (ኦሚክሮን) ምን ያህል እናውቃለን ?
አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተ ሲሆን በመላው ዓለም በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።
ሳይንቲስቶች ይህ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ለምን ? ከተባለ ቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ ዐይነቱን እየቀያየረ በመሆኑ በፍጥነት እየተዛመተ በመሆኑ ነው ተብሏል።
በደቡብ አፍሪካ የተገኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የተሰጠው ስያሜ “ #ኦሚክሮን ” የሚል ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት “ኦሚክሮን” በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳየው የስርጭት ባህሪ ተንተርሶ አደገኛ መሆኑን አስታውቋል፤ ቫይረሱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ባህሪውን የሚቀያይርና በርካታ ሰዎችን እያጠቃ ይገኛልም ብሏል።
ኦሚክሮን ለከፍተኛ ስጋትን እንደደቀነ ያሳወቀው የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም ለዚህ መዘጋጀት አለበት ብሏል።
በአዲሱ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በርካታ ሀገራት በደቡባዊ አፍሪካ እና አካባቢው ሀገራት ላይ የጉዞ ገደብ እየጣሉ ሲሆን አውሮፓ ህብረት፣ ብሪታኒያ ፣ አሜሪካ ፣ ጃፓን ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ ተጠቃሽ ናቸው።
@tikvahethiopia

" ዴልታ እና ኦሚክሮን አደገኛ ማዕበል እያመጡ ነው " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የኮሮና ቫይረስ #ዴልታ እና #ኦሚክሮን ልውጥ ዝርያዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን በማበራከት አደገኛ ማዕበል እያመጣ ነው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።
ዶ/ር ቴድሮስ፥ ይህንን ያሉት በአሜሪካና በመላው አውሮፓ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ መሆኑን እየተገለፀ ባለበት በአሁን ሰዓት ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ ለወረርሽኙ መበራከት የሁለቱ ዝርያዎች " ጥምር " ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
አክለውም ሁኔታው " በተዳከሙ የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር እና የጤና ስርአቶችን ሊያናጋው ይችላል" ብለዋል።
ከክትባት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሃብታም ሀገራት 3ኛውን ዙር ክትባት ወይም ማጠናከሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የበለፀጉ አገራት መጠነ ሰፊ የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎች " ወረርሽኙን እንዲራዘም " ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።
ለዚህ ምክንያትም የክትባት አቅርቦቶችን ከድሃ ሀገራት በማዘዋወሩ ቫይረሱ " እንዲሰራጭ እና አዳዲስ ዝርያ እንዲፈጥር የበለጠ እድል ይሰጠዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. በ2022 አጋማሽ 70 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ህዝብ ክትባት እንዲያገኝ የተጀመረው ዘመቻ እንዲሳካ ሁሉም ሰው መከተብን የአዲስ አመት ዕቅድ እንዲያደርገው ዶ/ር ቴድሮስ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።