TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የአሜሪካ መንግስት ዋሽቶናል፣ በምሥጢራዊ ሂደት መብታችንን ቀምቶናል " - የሟች ቤተሰቦች

በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ በተከሰከሱት ሁለት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች በአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት እና በቦይንግ መካከል በተደረሰው ስምምነት ላይ ቅሬታቸውን እንዳሰሙ ሮይተርስ ዘግቧል።

ተጎጂ ቤተሰቦቹ እአአ በ2021 የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር የደረሰውን ስምምነት በመቃወም ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ነው የጠየቁት።

ቤተሰቦቻቸውን በሁለቱ አደጋዎች ያጡት ሰዎች በመሥሪያ ቤቱ እና በቦይንግ መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ አውሮፕላን አምራች ኩባንያው "የወንጀል ክስ ሳይመሠረትበት እንዲያመልጥ"  በማድረጉ ማብራሪያ መጠየቃቸውን የሮይተስ ዘገባ ይጠቁማል።

ባለፈው ወር አሜሪካዊው ዳኛ ሪድ ኦኮነር ቴክሳስ ውስጥ ባሳለፉት ውሳኔ በሁለቱ የ737 ማክስ አውሮፕላን ደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን "#የወንጀል_ሰለባ" ናቸው ብለዋል። ምን ዓይነት ማካካሻ መሰጠት እንዳለበት እንደሚወስኑም ዳኛው ተናግረዋል።

እንደሮይተርስ ዘገባ ባለፈው ዓርብ ዕለት የሟቾች ቤተሰቦች እና ጠበቆቻቸው  ከመንግሥት ጠበቆች ጋር መገናኘታቸውንና በቦታው ያልነበሩ ሰዎች ደግሞ በበይነ መረብ ስብሰባውን ተካፍለዋል።

የሟቾቹ ቤተሰቦች የአሜሪካ መንግሥት "ዋሽቶናል፣ በምሥጢራዊ ሂደት መብታችንን ቀምቶናል" ሲሉ ለዳኛ ሪድ ኦኮነር ተናግረዋል።

እአአ በ2021 ቦይንግ አውሮፕላኑ ላይ ስላሉ ግድፈቶች ይፋ ካለማድረጉ እንዲሁም ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ከተደረገ በኋላ የተሰጠው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳና ተጠያቂ እንዲደረግ አሳስበዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reuters-11-19 /ቢቢሲ

@tikvahethiopia