TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

➡️ ፈረንሳይ ፣ ጣልያን እና ስፔን 85 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ዲፕሎማቶቹ ሀገራቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ተከሰው ሲሆን፤ ሩስያ ክሱ ሀሰት ነው ብላለች፤ የዩክሬን ጦርነት ከጀምረ ጊዜ አንስቶ 300 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከተለያዩ ሀገራት ተባረዋል።

➡️ ሩስያ ዛሬ የስፔን እና የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባረረች። እስካሁን 27 የስፔን፣ 34 የፈረንሳይ ያባረረች ሲሆን 24 የጣልያን ዲፕሎማቶችን ልታባርር እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የNATO አባላት ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ህብረቱ አባልነት እንዳይገቡ ያደረባትን ስጋት እንዲያከብሩ ጠየቀዋል። ኤርዶጋን ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ሀገር እንዲሆኑ ሀገራቸው ድጋፏን እንደማትሰጥ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

➡️ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ቆሟል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድሩ መደናቀፍ አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ነው።

➡️ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የፊንላንድ እና ስዊድን ለNATO አባልነት ያቀረሹትን ታሪካዊ ያሉትን ማመልከቻ ባደስታ እንደሚቀበሉትና አጥብቀው እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ባወጡት ተግለጫ ከUS ኮንግረስ እና ከNATO አጋሮች ጋር በመሆን በፍጥነት ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ጠንካራው የመከላከያ ህብረት (NATO) ለማምጣት እሰራለሁ ብለዋል።

➡️ ፊንላንድ NATO ለመቀላቀል ባሳለፈችው ውሳኔ ላይ የሩሲያ ምላሽ ድንገተኛ ቢሆንም እርምጃዎቹ ግን ወታደራዊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

#አልጀዚራ #ኤኤፍፒ #ዘኪየቭ_ኢንዲፔንደንት #አልአይን

@tikvahethiopia
#እስራኤል

ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸው ተነገረ።

በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተፈጥሮ ነበር።

ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ አክለውም ሁሉም #አፍሪካዊያን ስደተኞች ከእስራኤል እንዲወጡ ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸውንም ገልጸዋል።

ትላንት ቅዳሜ የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደርን በሚቃወሙ እና በሚደግፉ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት ተነስቷል።

ተቃውሞውና ግጭቱ በእስራኤል ኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው የተካሄደው። የእስራኤል የአደጋ አገልግሎት ተቋም 114 ሰዎች በግጭቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።

የእስራኤል ፖሊሶች የግጭቱን ተሳታፊዎች ለመበተን የፕላስቲክ ቦምቦችን የተጠቀሙ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ በፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹ ላይ እሳት መርጨቱን የዘገበ ሲሆን በአጸፋው 27 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አስታውቋል።

በተያያዘ ሮይተርስ እጃቸው እና ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች ሲደበቁ መመልከቱን ዘግቧል።

በእስራኤል 20,000 ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው የመጡ ናቸው።

#ቪኦኤ #ኤኤፍፒ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#G20 አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት…
" አፍሪካ ሕብረት እንዲገኝ ጥሪ አልደረሰንም " - ኤባ ካሎንዶ

አዲሱ የቡድን 20 የበለጸጉ ሀገራት ዓባል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘ ገልጿል።

ነገ ዓርብ እና ቅዳሜ በኒው ደሊ የሚካሄደውን ጉባኤ ያዘጋጀችው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ አፍሪካዊው ድርጅት ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገው ነበር።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ቃል አቀባይ የሆኑት ኤባ ካሎንዶ፣ ኅብረቱ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ጥሪ እንዳልደረሰው ትናንት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

19 ሀገራትን እና የአውሮፓ ኅብረትን በዓባልነት ያቀፈው ስብስብ፣ 85 በመቶ የዓለምን የሀገር ውስጥ ምርት እና ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሶስተኛውን ይይዛል።

ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ብቸኛዋ የቡድኑ ዓባል ነች፡፡

“የአፍሪካ ኅብረትን የጋበዝነው ወደፊት ቋሚ ዓባል እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ነው” ሲሉ ሞዲ ከ 10 ቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

“የአፍሪካ ኅብረትን በቋሚ ዓባልነት ሞቅ አድርገን ለመቀበል እንጠብቃለን” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው ታህሳስ ተናግረው ነበር፡፡

የቡድን 20 አባላት እነማን ናቸው ?

🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት ናቸው።

#ኤኤፍፒ #ቪኦኤ

@tikvahethiopia