TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BahirDar

ዛሬ በባህርዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለከተማ በህገወጥ መልኩ የተከዘነ በርበሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

በርበሬው ተከማችቶ የተገኘው በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአዲስ አለም ቀበሌ መስኪዱ አካባቢ ነው::

በቁጥጥር ስር የዋለው በርበሬ በኩንታል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሲሆን በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ሊያዝ የተቻለው::

ባለሃብቱም ከንብረቱ ጋር በቁጥጥር የዋለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

በባህር ዳር ከተማ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ስግብግብ ነጋዴዎች የኑሮ ውድነቱን እንዲባባስ መንስኤ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የዚህ አይነት ተግባራትን ሲያገኝ ለፖሊስና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል::

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara : " 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተዳርጓል" የአማራ ክልል መንግስት 750 ኪሎ ሜትር በሚያካልል አካባቢ 5 ዞኖች በህወሓት ወረራ እንደተፈፀመበት ሪፖርት አደረገ። ክልሉ ይህን ያሳወቀው ዛሬ በባህር ዳር ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ተወካዮች ጋር በመከረበት ወቅት ነው። የዛሬው ውይይት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ የሰብዓዊ…
#BahirDar

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር ሕወሓት በተቆጣጠራቸው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰሜን ወሎና በተወሰኑ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ሰዎች በመድሀኒት እጥረትና በርሀብ እየሞቱ ነው ሲሉ ተናገሩ።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ይህንን ያሉት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ከዓለም አቀፍ የእርዳታ ለጋሽ ድርጅት ተወካዮች ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤ በደቡብ ጎንደር እና በደቡብ ወሎ ህወሓት ወረራ ፈፅሞ በወጣባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የህዝብ መጎሳቆል መፈጠሩን የተናገሩ ሲሆን ዓለም አቀፉ ረጂ ድርጅቶች በፍጥነት ሕወሓት ተቆጣጥሮ ባለባቸው አካባቢዎች "በርሀብና በህመም ላሉ 4 ሚሊዮን ዜጎች እንዲደርስላቸው" ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የUNHCR የኢትዮጵያ ኃላፊ ዶክተር ካትሪን ሶዚ ችግሩን መረዳታቸውን ገልጸው የመገናኛ ዘዴዎችና የደህንነት ሁኔታው ከተመቻቸ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

የWFP) ተወካይ የእርዳታ ማድረሻ ተሸከርካሪዎች 19 ብቻ መሆናቸውን ጠቁመው "በነዚህ ተሸከርካሪዎች 4 ሚሊዮን ህዝብ እደርሳለሁ ማለት አይታሰብም" ብለዋል፤ ያለውን ክፍተት ከሞላልን እርዳታ እናደርሳለን ሲሉ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : በባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እንዲሁም የብሬን፣ የክላሸና የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋለ።

በባህር ዳር ከተማ ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምንሊክ ክፍለ ከተማ ማርዘነብ ቀበሌ በተባለው ስፍራ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ፦
- 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣
- 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣
- 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

የባህር ዳር ፖሊስ ፥ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ገልጿል።

የባህር ዳር ፖሊስ 9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ንብረቱ ሞት ፥ ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊት እንዲቆጠብ ያሳሰቡ ሲሆን "ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በምናውልበት ጊዜ ህዝቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ ጥሪ አስተላፈዋል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።

መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።

መስከረም 7/2014 ዓ/ም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትምህርት መምሪያው መረጃ አደራጅተው እንዲያሳውቁ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቱ ዕድሉን እንዳልተጠቀሙበት ትምህርት መምሪያው በደብዳቤው ላይ ገልጿል።

አሁን ላይ ወላጆች የት/ቤት ክፍያ እንደተጨመረባቸው ይህ የተጨመረው ጭማሪም ወላጆች ያላመኑበት መሆን ለመምሪያው ቅሬታ እያቀረቡ እንደሚኙ ገልጿል።

ትምህርት መምሪያው ፥ ትምህርት ቤቶች የጨመሩት ክፍያ ከተማሪ ወላጆች ስምምነት ውጭና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ከመስከረም 2014 ጀምሮ የተከፈለ ክፍያ ለቀጣይ ወራት ታሳቢ ተደርጎ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲያስከፍሉ የነበረውን ክፍያ እንዲያስከፍሉ አሳስቧል።

ት/ቤቶቹ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀጣይ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነሳ ፤ ከ2ኛ ሴሚኒስተር በኃላ ምንም አይነት ተማሪ በተቋማቸው የማይማርና ተቋማቱም እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።

መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሚመራ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።

የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።

የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ ነው።

መረጃው የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#BahirDar : በባሕር ዳር በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ፥ በግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ጥቆማው የደረሰው ከማኅበረሰቡ መሆኑን
አመልክቷል።

በጥቆማው መሰረት ተጠርጣሪው ቤት ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ፍተሻ በማካሄድ በግለሰቡ መኖሪያ ውስጥ 2 ክላሽ ፣ ከ3 ሺህ በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣ አንድ ኤፍዋን ቦንብ እና አንድ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿጻ።

የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በአግባቡ በማጣራት አድራሻቸውን ለፖሊስ እንዲያሳውቁም ጥሪ ቀርቧል።

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ጀመሩ። በፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአመራሮች ቡድን ዛሬ ወደ አፋር ክልል ገብተዋል። ቡድኑ በአፋር የዛሬ ውሎው…
#BahirDar

በፕሬዜዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ቡድን ዛሬ ከሰዓት ወደ አማራ ክልል መዲና ባህር ዳር መግባቱን ፓርቲው አሳውቋል።

ቡድኑ ባህር ዳር ሲደርስ በከተማዋ ወጣቶችና የፋኖ አባላት አቀባበል እየተደረገለት ፓርቲው ገልጿል።

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመሩት የባልደራስ ፓርቲ አመራሮች ቡድን ትላንት አፋር ክልል በመግባት በዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን መጠየቁ እንዲሁም በአዋሽ ወንዝ ላይ እየለማ ያለውን የስንዴ ምርት መጎብኘቱ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የምግብ ዘይት የለም ይሉናል፤ አለ የሚባልባት ደግሞ በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚሸጠው " በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የምግብ ዘይት አለመኖር ቢኖርም ደግሞ ዋጋው የሚቀመስ እንዳልሆነ ገልፀዋል። ለአብነት ከአዲስ አበባ ቲክቫህ አባላት በመጣው መልዕክት በተለያዩ አካባቢዎች ባለ5 ሊትር የምግብ ዘይት ካለ እንኳን ከ850-950 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ጠቁመዋል። ባለ አንድ ሊትር…
#BahirDar📍

በባህር ዳር የምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ የምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ከነገ ከ28/06/2014 ዓ.ም ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምረው ፓልም ዘይት መግዣና መሸጫ ዋጋ መረጃ ይህንን ይመስላል ፦

ቸርቻሪዎች / ሸማቾች ህ/ስ/ማ ከአለ በጅምላ የሚገዙበት የጅምላ ዋጋ ፦

1. ባለ 20 ሊትር 👉 1575.6 ብር ፣
2. ባለ 5 ሊትር 👉 408.6 ብር፣
3. ባለ 3 ሊትር 👉 251.10 ብር ሲሆን፣

ቸርቻሪዎች / ሸማቾች ህ/ስ/ማ #ለተጠቃሚው_ማህበረሰብ የሚያሰራጩበት ዋጋ ደግሞ ፦

1. ባለ 20 ሊትር 👉 1641.80 ብር ፣
2. ባለ 5 ሊትር 👉 425.80 ብር፣
3. ባለ 3 ሊትር 👉 261.70 ብር መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
#BahirDar

በባሕር ዳር የባጃጆች ሰዓት ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ከተማ የባጃጅ ወይም የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ እንዲሆን ገደብ ተጣለ።

የባሕር ዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ምክር ቤቱ በአደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስጠብቁ ያላቸውን ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል።

በዚህም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ትዕዛዝ ተላልፏል።

ምክር ቤቱ አሁን ካለው ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለከተማው ሰላምና ደኅንነት ሲባል ውሳኔው መተላለፉን አሳውቋል።

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውም የባጃጅ ወይም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የተባለ ሲሆን ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰድበት ማንኛውም ቅጣትና እርምጃ ኀላፊነቱን ባለቤቱ ወይም አሽከርካሪው ይወስዳል ሲል ምክር ቤቱ አሳስቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Harari #SafaricomEthiopia በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል። በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል። ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች…
#ADAMA #BAHIRDAR

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል።

የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

📍ባህር ዳር

አራት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ቀበሌ 14 - የተባበሩት ፊትለፊት፣ ቀበሌ 16 - ኖክ ፊትለፊት፣ ቀበሌ 11 - አባይ ማዶ፣ ቀበሌ 12 - ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ካምፓስ ፊትለፊት) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

📍አዳማ

ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ፍራንኮ እና ፖስታ ቤት አካባቢ) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

በባሕር ዳር እና አዳማ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

የሳፋሪኮም የጥሪ ማእከል 700 ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን በዚሁ ማግኝት ይቻላል። በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia
#Amhara #Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባሕር ዳር ክልከላ ተጣለ።

ክልከላው የተጣለው በከተማው የጸጥታ ምክር ቤት ነው።

ከክልከላዎቹ ምንድናቸው ?

-  የቤት መኪና ፣ ታክሲ ፣ የመንግሥት መኪና ፣ ማንኛውም የጭነት መኪና ተሽከርካሪ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ተጥሏል። ከተፈቀደው ሰዓት እላፊ ሲያሽከረክሩ መገኘት በሕግ ያስቀጣል።

- ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ ማንኛውም የሰው እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

- ማንኛውም ተሽከርካሪ ታርጋ ሳይኖረው ወይም ሳያስር መንቀሣቀሥ አይችልም።

- ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች ውጭ ስቲከር መለጠፍ ተከልክሏል።

-  ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ባጃጅ መጋረጃ እና የግራ ጎን ሸራን ሳያነሱ ማሽከርከር ተከልክሏል።

- የባጃጅ ተሽከርካሪ ማኀበራት ከተሰጣችው የሥምሪት ቦታ ውጭ ማሽከርከር አይችሉም።

- በማኀበራት ተደራጅተው ስምሪት ከተሰጣቸው ባጃጆች ውጭ ማሽከርከር ተከልክሏል።

- የባጃጅ ተሸከርካሪዎች የባሕር ዳር አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት በአዲስ የሚሰጠውን መለያ ወይም ባር ኮድ ግልጽ እና በሚታይ መንገድ የመለጠፍ ግዴታ አለባችው።

- የባጃጅ ባለ ንብረቶች ለቀን ገቢ ወይም ለተለያዩ የጊዜ ገደብ ለሚያከራዮቸው ግለሰቦች የውል ስምምነት በመያዝ ለፓሊስ እና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ማሳወቅ አለባቸው።

- ባጃጆች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ማሽከርከር ተከልክሏል።

- ባለ 2 እግር ሞተር ተሽከርካሪ ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር ተከልክሏል።

ክልከላው የማይመለከታቸው እነማንን ነው ?

ክልከላ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች ፦
° በጸጥታ ሥምሪት ላይ የሚገኙ፣
° አንቡላሶች፣
° የእሳት አደጋ መኪናዎች ናቸው። ነገር ግን በማንኛውም ሰዓት በአንቡላንስም ኾነ በሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ፍተሻ ይደረጋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ከጸጥታ መዋቅሩ አባላት እና ለጸጥታ ሥራ ተሰማርተው የመንቀሣቀሻ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰዎች ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሣቀሥ ተከልክሏል።

ማንኛውም የጸጥታ አባል ከተሰጠው ስምሪት ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ሲቪል ለብሶ የጦር መሣሪያ ይዞ መንሳቀስ እንዳይችል ክልከላ ተጥሏል።

#AmharaRegion

@tikvahethiopia