TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት " - የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት…
" ዜጎች ምን ያህል እንደሚንገላቱ የአይን ምስክር ነኝ !! " - የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር)

ዛሬ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #የፓስፖርት_አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በተካሄደው የ2015/2016 የክዋኔ እና ኦዲት ሪፖርት ስብሰባ ላይ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል ስለ ሰራተኞች ስነምግባር ፤ ስለ ዜጎች እንግልት ተነስቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) መ/ቤቱን " ሁላችንም የምንረግጠው በር ነው ያላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ነገር ግን ሁላችንም ተጠቂ / Victim የሆንበት ጉዳይ ነው እውነቱን ለመናገር " ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ያሉት ስለ ሰራተኞች ስነምግባር እና ስለ ተገልጋይ እንግልት ባነሱት ሃሳብ ነው።

በጉዳዩ ላይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ኃላፊዎች ለምክር ቤቱ " አጃቢዎቻቸው ፣ በቋንቋ ፣ ቦታ ባለማወቅ ... በተለያዩ ምክንያቶች አጅበዋቸው የሚመጡት እንጂ አገልግሎት ፈላጊዎቻችን አይደለም የሚንገላቱት " ብለዋል።

የምክር ቤት አባልና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ግን " እኔ ምስክር ነኝ እኔ ተንገላትቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔ ተንገላትቻለሁ ፤ እኔ ተገፍቼ ወጥቻለሁ ያውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መታወቂያ እያሳየሁ ፤ ተጎትቼ ወጥቻለሁ ይህንን ከማንም አይን እማኝ አይደለም እኔ ላይ የደረሰ ነው። እኔ ይሄንን የምለው እኔ ተበድያለሁና እኔ ለምን ተበደልኩ ብዬ አይደለም " ብለዋል።

" እኔ ይህን ሃሳብ እያቀረብኩ ያለሁት ከኃላዬ ያለው ዜጋ ምን ያህል እንደሚንገላታ የአይን ምስክር ነኝ ለማለት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን ፈትሹት ፤ ሩቅ አይደለም የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም እየናገርኳችሁ ያለሁት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ያለ ነው " ብለዋል።

" አገልግሎት ፈላጊው ወረቀት ይዞ ፣ የሞላውን ፕሪንት አድርጎ ይዞ በጣም እየተንገላታ ፤ እየተገፋ ያለበት ሰዓት ነው ያ መሆን የለበትም " ሲሉም አሳስበዋል።

አክለው " ለዜጎቻችን መስጠት የምንችለውን አቅማችን የፈቀደውን አገልግሎት በአግባቡና በስርዓት ልንሰጥ ይገባል እንጂ ከዛም አልፎ መንገላታትን ልንጨምርበት አይገባም " ብለዋል።

መ/ቤቱ ያሉትን ቅርንጫፎች አቅም እንዲያጠናክር እና ዜጎችን ከሚያንገላታ አሰራር እንዲታረም በጥብቅ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopia
#Passport

@tikvahethiopia