TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን⬇️

የኬንያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማህበር የኢትዮጵያ አየር ክልል ደህንነትን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ በፍጹም እውነት #እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ የአየር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች የስራ አድማ በመምታታቸው በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ #ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት ባለመፈጠሩ ማህበሩ ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ በመሆኑ ባለስልጣኑ በምንም መልኩ እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡

ሰራተኞቹ አድማ ቢመቱም አሁንም በበቂ ሁኔታ ስለጠና በወሰዱ፤ በሙያው ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ባከበቱ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቁ ሰራተኞች ስራቸውን እያከናወኑ በመሆኑ ምንም ዓይነት ስጋት አይፈርም ብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር ክልል የተጠበቀ መሆኑን ለአየር መንገዶች፤ ለሃገራት ሲቭ አቪዬሽ ባለስልጣናት፤ ለዓለም አቀፍና ቀጠናዊ አካላትም እንደሚያረጋግጥ ገልጿል፡፡

📌የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስከረም 4ቱ ሰልፍ ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ አይደለም!

መስከረም 4 ይደረጋል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ #እንዳልሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች አስታውቀዋል። ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን ገልፀዋል።

Via #ETHIOFM

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FakePage ይህ ከ260,000 በላይ ተከታይ ያለውና በገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስም ታየተከፈተ የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። እጅግ በሚገርም ሁኔታ በገፁ የሚሰራጩት መልእክቶችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይክ እና ሼር ያደርጉታል። ፖስት የሚደረጉት ፎቶዎችም ከኢንስታግራም ገጿን የሚወሰዱ ናቸው። Meron Getnet @tsegabwolde @tikvahethiopia
Meron Ghetnet

"የፌስቡክ ገፁን ልሽጥልሽ ጭምር ሲለኝ ነበር"--አርቲስት ሜሮን ጌትነት በስሟ ተከፍቶ 260,000 ተከታይ ስላፈራው የሀሰት የፌስቡክ ገፅ ከተናገረችው!

ሰሞኑን መነጋገርያ በነበረው በገጣሚ እና ተዋናይዋ ስም ስለተከፈተው ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ዙርያ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከሜሮን ጌትነት ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።

ሜሮን ጌትነት ስለጉዳዩ ይህን ብላለች፦

"የሚገርመው ዘመድ እና ጓደኞቼ ጭምር ይህ ገፅ የኔ ይመስላቸው ነበር። እኔ ግን ለበርካታ ግዜያት የኔ ትክክለኛ ገፅ #እንዳልሆነ በኢንስታግራም አካውንቴ ስገልፅ ነበር። ሌላው የሚገርመው የዚህ 260,000 ተከታይ ያለው ገፅ ባለቤት ገፁን ልሽጥልሽ ስለዚህ እንደራደር ሲለኝ ነበር። ዝም ስለው ቆይቶም አብረን አድሚን ሆነን ስራ እንስራበት ሲለኝ ነበር። የዚህ ሁሉ ንግግር ስክሪንሾት አለኝ። ለማንኛውም አሁን ለፌስቡክ ሪፖርት አድርጌው እንዲዘጋ አደርገዋለሁ። ትክክለኛው አካውንቴ ይህ ነው: https://www.facebook.com/meron.ghetnet"

Via Elias Meseret/AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia