TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ‹‹የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ህዝብ እየሞተበት ያለ ጥያቄ እንደመሆኑ #በቀላሉ የሚታይ አይደለም›› ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ዶክተር #አምባቸው_መኮንን አስታወቁ፡፡ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትነት መታጨታቸውን ህዝቡ ባለመፈለጉ በፖለቲካ ተሳትፏቸው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል፡፡ አማካሪ ሚኒስትሩ ዶክተር አምባቸው መኮንን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በወልቃይትና በራያ አካባቢ የሚታየው ችግር በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፣ ለአገሪቱም የሰላም #መናጋት ምክንያት እየሆነ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ካልተፈታ ሁለቱ ክልሎችም ሆኑ አገሪቱ ሰላም አያገኙም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹ለፖለቲካዊ ለውጡ ቀጣይነት›› በሚል ርዕስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ ዶር. #አምባቸው_መኮንን፣ ፕሮፌሰር #መረራ_ጉዲና#ክርስቲያን_ታደለና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዶክተር አምባቸው በአንኳር ንግግራቸው ምሁራን ወቅቱ ባመጣው ለውጥ በፖለቲካው ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታታቸው በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሃሳብ ፍጭቶች የሚካሄዱባቸው መድረኮችን ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይቆያል፡፡ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በሌሎች ምሁራን አማካኝነት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወረታ🔝

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት 8ኛ የደረቅ ወደብ መደረሻውን ለመገንባት ዛሬ በወረታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል። የመሠረት ድንጋዩ በተቀመጠበት ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #አምባቸው_መኮንን፣ ጠትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መከናወኑን የዘገበው አብመድ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia