TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ‼️

ዛሬን ጨምሮ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፦

"ምንድነው የምትንዘባዘበው መረጃ ከሌለህ ትርኪ ምርኪ ነገር ለምን ትፖስታለህ?"

"ትንንሽ ጉዳዮችን ለምን ትፅፋለህ?"

"አንተ የመንግስት አጨብጫቢ ነህ?"

"አንተ ከዚህ ብሄር ነህ #መሰለኝ ለዚህኛው ታደላለህ..." እና ሌሎችም።

እንዲሁም አስተያየት መሰል ብዙ ስድቦች ይደርሱኛል።
.
.
በመሰረቱ ይህን ቻናል ለህዝብ ጥቅም እና ለመረጃ ልውውጥ የከፈትኩት ነው። ከየትኛውም ወገን ንፁህ ነው። እኔም ከየትኛውም ወገንተኝነት 1000000% ንፁህ ነኝ። እኔ ራሴን የሁሉም ሰው አድርጌ ነው የምቆጥረው። ለሁሉም የሰው ፍጡር እጅግ በጣም ትልቅ ክብር ነው ያለኝ! የኔ መስፈርት ሰው መሆን ላይ ነው። በመሆኑም መረጃዎች ሲላኩልኝ መጀመሪያም መጨረሻም የማየው ከየትኛው ወገን፣ ከየትኛው ብሄር፣ ከየትኛው ሀይማኖት ተከታይ ሰዎች ተላከልኝ ሳይሆን ይህን መረጃ ባሰራጨው ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል? የሚል ጥያቄ ነው የማነሳው።

በፍፁም ያለአንዳች ግብ እዚህ ገፅ ላይ የሚለጠፈው ፅሁፍ የለም። በተለይ ቻናሉ ለሰላም የሚሰራ ነው። ይህ ማለት ችግር ሲፈጠር ይደብቃል ማለት አይደለም። መረጃዎቹ ሁሉ እንዲመቱልኝ የምፈልገው ግብ አለ። የአያንዳንዱን ከተማ እንቅስቃሴ ሰላም መሆኑን ሰው በሰላም እየተንቀሳቀሰ እለታዊ ተግባሩን መፈፀሙን የሚገልፁ ፅሁፎችን የምለጥፈው መቀለ ሆኖ ስለ ወለጋ፤ ባህር ዳር ሆኖ ስለ ሀዋሳ፤ ሞያሌ ሆኖ ስለ ቤንሻንጉል ጉዳይ መሰማት ስላለበት ነው። ለኛ ስናነባቸው ትንሽ እና ተራ የሚመስሉን ነገሮች ብዙ ሺዎችን በእንቅስቃሴያቸው እንዳገዛቸው በቂ ማረጋገጫ አለኝ።

ይሆነ ቦታ ወጣቶች የሚሰሩትን ጥሩ ስራ ሳቀርብ ሌላውም በነጋታው አስቦት ያድራል። እዚህ ከተማ እንዲህ አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተከናወነ፣ ተከበረ የምለውም በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ስላለው ነው።

ከዚህ ቀደም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓል እንዲሁም የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓላት በየከተማው በየቀበሌው #በሰላም ስለመከበሩ የማበስረው የዚህን ቻናል ግብ ለማሳካት ነው። 😁ብችል የእያንዳንዱን ሰው ሰላማዊ ውሎ ብዘግብ ደስ ይለኛል።

እና ወዳጆቼ በሰላም ተከበረ በሰላም አለቀ የሚሉ ቃላቶች ማደጋገማቸውን እንደትንሽነት እና እንዳላዋቂነት አትቁጠሩት ትልቅ ትልቅ ጥቅም አላቸው።

ሌላው ከናተ የሚመጡት መረጃዎች እውነት ስለመሆናቸው ፈጣሪ ታማኞች አድርጎ ስለፈጠራችሁ አያሳስበኝም።

መረጃዎች #እንደወረዱ የሚቀርቡት በፍፁም የኔ እጅ እንዳይገባበት ነው። መረጃ ስትልኩልኝ ነጥብ አላስተካክልም። የላካችሁትን አቅርባለሁ። ይህ እኔ ምፈነጭበት እና እራሴን ማስተዋውቅበት መድረክ አይደለም። ይሄ የናተ ገፅ ነው! የፃፋችኋትን #ምንም ኢዲት ሳላደርግ ቃል በቃል አቀርባለሁ። ወደፊትም በዚሁ ቀጥላለሁ።

ማጠቃለያው፦ እዚህ ቤት #ትንሽ ጉዳይ የለም! ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት ምድር ምንም የማልፈው ነገር የለም። ይህ አቋሜ ነው። ደረጃ እና ጥራት እያሉ መመፃደቅ አይሰራም። ከእናተ ቤት ተነስተን እንስከ ሀገር ድረስ መረጃዎችን እንዳስሳለን። ለማቅራራት እና ዝነኛ ወይም ገንዘብና ስልጣን ባላቸው ሰዎች ለመወደድ አይደለም የምሰራው! እኔም ሆንኩ ቻናሉ ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ info እንሰጣለን። ይህን ማድረግ ትንሽነት እና አለማወቅ ከሆነ ትንሽ እና አላዋቂ ሆኜ ልሙት!
.
.
አዎን የተላከ ሁሉ አይቀርብም! መረጃ ሲላክ ለአካባቢው እና ለሌላ ቦታ ይህ ነገር ይጠቅማል?? የሚለውን ጠይቄ ነው። ሌላው በውስጥ በኩል መረጃ የምሰጣቸው አሉ።
.
.
TIKVAH-ETH ለዝና የሚንቀሳቀስ አይደለም! ለሰላም፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ነው የሚሰራው።

እዚህ የሰበሰበን ሰውነት ነው፤ ከዛም ኢትዮጵያዊነት! ነፁ ኢትዮጵያዊ ደግሞ እራሱን የሚያውቅ ሁሉንም የሰው ፍጡር እንደራሱ የሚያይና #የሚያከብር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዕምሮ የሌለው ሕዝብ #ሥርዓት የለውም፤ ሥርዓት የሌለው ሕዝብ የደለደለ ሃይል የለውም፤ የሃይል ምንጭ ሥርዓት እንጂ የሠራዊት ብዛት አይደለም፤ ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግሥት ይልቅ በሕግ የምትኖር #ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች።"

▪️ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፦

ለሁሉም ነገር መሰራት ያለበት ከአዕምሯችን ነው። መልካም እና ገንቢ ሀሳብ ካልተዘራብን አፍራሽና ጠባብ አስተሳሰብ ይዘን የትም መራመድ አንችልም። የያዝነው ክፉ ሀሳብ ከኛ አልፎ ለሌሎችም እንቅፋት ነውና ነቅለን ጥለን በፍቅር፥በተስፋ እንዲሁም በእምነት ለዚህች ሀገር የግላችንን አበርክቶት እናኑር። ከራስ ቅላችን በላይ እናስብ። ተስፋዬ ፈለቀ @UoG GONDAR"
.
.
ከእኔነት እሳቤ መላቀቅ! አያቶቻችን ለሠሩት ስህተት(ምናልባት ከሰሩ) ይሄን ትውልድ እዳ ከፋይ አለማድረግ። እኛ ብሎ ማሰብ መጀመር ያስፈልገናል። ከሁሉ በፊት ሰው መሆናችንን ማመን። ሕገ መንግስቱን ማሻሻል። ፓርቲዎች ክርክራቸውን ከሕገመንግሥቱ ይልቅ ፖሊሲዎች ላይ ቢያደርጉ መልካም ነው።
.
.
የተሰራን ነገር ማፍረስ እንደመገንባት አይከብድም..ጦርነት ቀላል የሰላም መንገድ ረጅም ነው፡፡... ሁላችንም እንደ መንጋ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ቆም ብለን ነገአችንን ማሰብ ካልቻልን ዘመናችንን በሙሉ ከድህነታችን ጋር ተጣብቀን ስንኗፏቀቅ መጃጀታችን ነው..ስለ ጭለማ ማውራት ብርሃን አያመጣም የልዩነት ሃሳቦችን ትተን አንድ የሚያረጉን ነገሮች ላይ ትኩረት ብናረግ ጥሩ ቀን ይመጣል ብዬ አስባለሁ ገና ብዙ የቤት ስራ ያለብን ህዝቦች ነን፡፡ፈጣሪ ሃገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን! ዳዊት ነኝ ከሰላሌ ፍቼ
.
.
አሁን በሀገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለቀጣዩ ትውልድም የሚተርፍ መዘዝ ያለው በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው። ብዙ ግዜ እንደተባለው ይህች ሀገር ከቀጣዩ ትውልድ የተዋስናት እንጂ እኛ ብቻ ኖረን ምናልፍባት አይደለችም። ታድያ ዛሬ ፍቅር እና መቻቻልን ያላስተማርናቸው ልጆቻችን እና በእድሜ ታናሾቻችን ነገ ከየት አምጥተው ይኖሩታል? ከሁሉ በላይ ሰውነትን እናስቀድም። ጩኸታችን እና ስብከታችን ሁሉ ስለ ፍቅር ይሁን። ለምን? ምክኒያቱም የነገ ሀገር ተረካቢዎች ከኛ ይማራሉ። መጥፎም ሆነ መልካም ከታላላቆቻቸው ይማራሉ። ጥላቻን አውርሰን ሰላም የሌለው ህይወት እንዲኖሩ አንፍረድባቸው! ልዩ ከሻሽመኔ
.
.
እኔ በበኩሌ ሁሉም ሰው የየራሱን ስራ ቢሰራና ሀላፊነቱን ቢወጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አስባለው። ምክንያቱም ምንም ነገር ከግለሰብ ነው ሚጀምረው። ሁላችንም እሱ ምን አደረገ፤ እነሱ ምን አደረጉ ሳንል እኔ ምን አደረኩኝ ምን ማድረግ አለብኝ ብለን ብናስብና ለስራ ብንነሳ ከኛ ለውጥ ይጀምራል። ስለዚህ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ ለስራም እንነሳ። ሔኖክ ነኝ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
.
.
እንደ ሚመስለኝ የአይማኖት አባቶች ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል እራሳቸውን ከፖለቲካ አንጃ አውጥተው ስለ ሰላም መስበክ አለባቸው የትኛውም እምነት ግደሉ በድሉ ዝረፉ አይልም ።
የተረሳ ሆኗል ስለሰላም መስበክ ስለ አንድነት ማውራት ችላ ተብሏል ። ወጣቱ የበለጠ ሊሰማ የሚችለው የእምነት አባቶችን ነውና በዚላይ ቢሰራ ባይ ነኝ። ሳብር
.
.
ለዚህ ተጠያቂ ሁላችንም ሁነን ሳለን ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ለችግሩ ሌላ ባለቤት ፈልገን እጃችን ለመቀሰሰር መጣራችን ይበልጥ አባብሶታል። ሰውን አርክሰን ለሌሎች ነገር የተሻለ ዋጋ ሰጥተናል። ሁላችንም ጥፋቶቻችን እንመን ከዛ ይቅር እንባባል በመቀጠል ተባብረን እንስራ!
.
.
ወንድሞቼ ያነሱት ሀሳብ እንዳለ ሆኖ
በየአካባቢው የምኖር ሰዎች ችግር ወይም ግጭት ሳይባባስ ቶሎ ብለው ወዴ መፍትሄ መሄድ አለበት ላሳስብ እወዳለሁ። ምሳሌ ብንወስድ
በድሮ ጊዜ ነው አንድ ፎቅ ባለ አራት ደረጃ ከላይ በአራተኛው እሳት ይነሳና ይቃጠላል ሥስተኛ እኔ ምን አገባኝ ይላል ከዛን ወደ ሥስተኛው መጣ ይቃጠላል ሁለተኛ ምን አገባኝ ይላል እሱ ጋ እንደዚህው ተቃጣለ አንደኛ ላይ እኔ ምን አገባኝ እያለ ላለው እሱ ጋ መጣ #ምሳሌው እኔ ምን አገባኝ የምንለው ነገር ነገ የከፋ ነገር ያመጣብናል ስለዚህ #ትንሽ #ትልቅ #ተማሪ #ነጋዴ #ሹፈሩ ወዘተ በሀገራችን መስራት አለብን
አመሰግናለሁ :#ፀግሽ
.
.
የመጀመሪያው ጥፋተኛ እኔ ነኝ። ለምን ተጠራጣሪና ስግብግብ ስለሆንኩ። ለምን የምኖረውና የማስበው በተከለልኩበት የማንነት አጥር ውስጥ ስላለው። እስኪ ትጋትን ሲሆን እኔ ድክመትን ሲሆን እነ ሱ ከሚለው ቆልማማ አመለካከት እንላቀቅና" እኛ" በሚለው ተያይዘን እንጒዝ። የሸበበን ብሄር ያነቀን ጎስ ይስቀመጠንን ጎጠኝነት ትተን ከአጥሩ ባሻገር ያለው ሰፊውን የፍቅር ሜዳን እንመልከት። ክፉዎች ሊለያዩን ያጠሩብንን ግንብ ድልድይ እንገንባና ዳግም እንተያይ...የእውነት መሰረቱ መፋቀር ብቻ ነው..ሰውን ለማገልገል እንጂ ለምን ክብርን እሻለው...ትግላችንና ግዴታችን ፍቅር ይኑርበት... ሁሉን ማስተካከል የሚቻለው እርስ በእርስ በመዋደድ ብቻ ነው። ጌታነህ ከመቂ!
.
.
እሺ ወንድሜ፡ ዋናው የአሁኑ ለደረስንበት ውጥቅጥ መጀመሪያ የነበረው ከሁንም ያለው ራስ ወዳድነታችን ነው ፡ የምር እኛ በቀደድነው ቀዳዳ ሌቡች ይገባሉ ሀገርን ለማቃወስ እኛ አሁን ወላሂ መንቃት አለብን የድርጅት ደጋፊ ብቻ መሆን መዘዙ ይህ ነው አሁን ያለንበት ሁኔታ እውነትን እፈልግ ሀሳብ ያሸንፍ ለሀሳብ እድል እንስጠው ፡ አገሬ ኢትዮጲያ ለዘላለም በልጆችሽ ኮርተሽ ትኖራለሽ ፡ በርግጠኝነት እናሳካዋለን ፡ እኔ ባለሁበት ለዚህም ቁርጠኛ መሆኔን እገልፃለሁ፡ ሰላም ፍቅር ለኢትዮጵያ ህዝብ ቸው ፡ ዩኑስ ነኝ ከቡታጅራ
.
.
የሚጋፋ ሃሳብ ወይም የሌላዉን ወገን ህልዉና የሚነካ ንግግሮች እና ዘለፋዎች ከስነ-ስርዓት አልበኝነት የሚመጣ ሲሆን እያንዳንዳችን ሌላዉ ላይ ጣታችንን መቀሰር ትተን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ መክረን መመለስ ባንችል እንኳን ክፉ ከመናገር በመቆጠብ ታላቁን ሰላም እንጋራ፡፡ ኤልያስ፡ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር
.
.
እኔ እንደማስበዉ ከሆነ ለዚሁሉ ችግር ዋንኛው ተጠያቂ ት/ቤቶቻችን ናቸዉ፡ጥላቻን እንድናውቅ እያደረጉን ነው.ከዚ ቀደም የደርግን ስርአት እየተቸ ነበር ያስተማረን ደርግ ምንም ጥሩ ነገር እንዳልሰራ፡አሁንም ቢሆን ያለፈው ስርአት አንተች በጣም ብዙ ጥሩ ነገር አንደሰራም እንወቅ ባይ ነኝ፡ስለዚህ የትምህርት ስርአቱ ላይ መሠራት አለበት።
.
.
ህብረተሰብ የሚለውን ቃል ብንመረምር ህብረት እና ሰብ የሚሉት ቃላት ዉህድ ነው። "ሰብ" የሚለውም መጨረሻው እና ማሰሪያው ነው። ህብረታችን ቁምነገሩ ሰውነታችን ላይ ነው። ስለሆነም የህብረታችን ማሰሪያ የሆነውን "ሰውነት" ወደ ዉስጥ መመልከት ስንችል የምናስተውለው የአፈጣጠራችንን ረቂቅ ጥበብ፣ ሃሳብ ነው። ዘር፣ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ እዚያ ዉስጥ አንዳቸውም ቦታ የላቸውም። ይህንን ስንገነዘብ የሰውን ልጅ ቅድሚያ በሰውነቱ ሲቀጥል በሃሳቡ እናየው ዘንድ እንችላለን።
.
.
ሰላም ሰላም የሀገሬ ህዝቦች ዘር ሳልቆጥር ቀለም ሳለይ ውውድድድ ነውው የማረጋቹ የማይረሳ የአድዋን ድል አስገኝታቹልናልና እና እኔ ምለው ሰላም ለማምጣት እርስ በእርስ ህዝብ ለህዝብ መደማመጥ እና ዘረኝነት አስወግዶ ሁሉንም አንድ የሚያረግ አስተሳሰብ በህዝብ ዘንድ መምጣት አለበት ይህ እንዲመጣ ደሞ የmedia ሺፋን ትልቁን ቦታ ይወስዳል እደዚሁም social midia ዎችም የራሳቸውን አስተዋፅሆ ያደርጋሉ በሰላም ላይ እንደማመጥ እንከባበር ሁሌም ሰላም ከኛ ጋር ናት ድል ሰላም ወዳድ ለሆነው የሀገሬ ህዝብ አቤል ነኝ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የፈተና ውጤት ይፋ እንደማይሆን ተገለፀ!

ከቀናት በፊት በተለያዩ የመንግስት ሀላፊዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሀሴ 5 እንደሚለቀቅ ሲገለፅ ነበር። የፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፁት፦ "ውጤቱን ለማውጣት #ትንሽ ተጨማሪ ስራ መስራት አስፈልጎናል። ዛሬ ሳይሆን ከሁለት ቀን በሁዋላ አካባቢ ይለቀቃል። ይህ መራዘም ያስፈለገው ከዛሬው በአል ጋር በተገናኘ ሳይሆን ትንሽ ሌላ የምንሰራው ስራ ስላጋጠመን ነው" ብለዋል።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሄር የተናገሯቸው፦

√ ማክሰኞ ዕለት በኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በቀጥታ በስልክ ገብተው ከአርብ በፊት ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

√ ሀሙስ ዕለት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አቶ #አርዓያን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ ደግሞ ሀሙስ ወይም አርብ ከሰዓት ይፋ እንደሚሆን ነበር።

√ ሀሙስ አመሻሹን ኤጀንሲው በህጋዊና ትክክለኛ ገፁ ፈተናው ውጤት ነሃሴ 5 ነው የሚወጣው አለ። ተማሪውም ውጤቱን እንዴት መመልከት እንዳለበት ተገለፀ።

√ ዛሬ ነሃሴ 5 ነው ተማሪው ውጤቱን ለማየት ሲጠባበቅ አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሄር "ውጤቱን ለማውጣት #ትንሽ ተጨማሪ ስራ መስራት አስፈልጎናል። ዛሬ ሳይሆን #ከሁለት ቀን በሁዋላ አካባቢ ይለቀቃል። ይህ መራዘም ያስፈለገው ከዛሬው በአል ጋር በተገናኘ ሳይሆን ትንሽ ሌላ የምንሰራው ስራ ስላጋጠመን ነው" አሉ።

እኛ እንደTIKVAH-ETH ይቅርታ እንጠይቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia