TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ይሄ ' የአማራ አዋሳኝ ' የሚባለው ቀልድ መቆም ያለበት ነው " - አቶ ረዳዒ ኃለፎም

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳዒ ሀለፎም ሰሞኑን ስለነበረው የተኩስ ልውውጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ረዳዒ ሀለፎም ምን አሉ ?

- ግጭቱ ራያ አላማጣ ሳይሆን ጨርጨር አካባቢ ነው። ይሄ የአማራ አዋሳኝ የሚባለው #ቀልድ ደግሞ መቆም ያለበት ነው።

- የትግራይ መሬት ነው ጨርጨር። ጨርጨር ትግራይ እንጂ አማራ ሆኖ አያውቅም። አሁንም አይደለም። እዚያው የአማራ ታጣቂዎች አሉ። እነዛ የአማራ ታጣቂዎች በእኛ ሚሊሻዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት ነው። የአጭር ጊዜ ተኩስ ልውውጥ ነበር ቁሟል አሁን ግጭቱ የለም።

* ጉዳዩን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ለቀረበ ጥያቄ ፦ " በእኛ በኩል (በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርም) ከላይ ከሚመለከታቸው የፌደራሉ መንግሥትም የተወሰነ ንግግር እየተደረበት ነው " ብለዋል።

* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦

" የመጀመሪያው ነገር ሕገ መንግሥቱን ማክበር ነው። የአዋሳኝ ጉዳይ አይደለም መሀል ትግራይ ላይ ነው ችግሩ እየተፈጠረ ያለው። ወረው በኃይል ከያዙት መሬት ላይ ነው አሁን ደግሞ መልሰው ጥቃት እየፈጸሙ ያለት። ይሄ ትክክል አይደለም። ለማናችንም የሚጠቅም ነገር አይደለም።

መሆን ያለበት ጥያቄ ያለው አካልም በሕጉ መሠረት ካልሆነ በቀር የሆነ አጋጣሚ ተጠቅሞ ‘ጉልበት አለኝ፣ ይጠቅመኛል’ ብሎ ባሰበ ጊዜ የኃይል አማራጭ የሚወስድ ከሆነ፣ ቢያንስ የሕዝቦች ዘላቂ ወዳጅነትና መቀራረብ የሚያረጋግጥ አይደለም። ከዚህ መቆጠብ ነው ያለብን " ብለዋል።

- የፌደራል መንግሥት ሲቪሊያንን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ድሮም ቢሆን በውሉም በተመሳሳይ ፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖም ከመከላከያ ሰራዊት ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ውሉም ያስገድዳል። አለመውጣታቸውም ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የአማራ ታጣቂዎች ባሉበት አካባቢ ሴቶች እየተደፈሩ ናቸው። ሰብዓዊ መብቶች እየተረገጡ ናቸው። ብዙ ጥፋቶች እየተፈጸሙ ናቸው። ስለዚህ ውሉን በአግባቡ ተግባሪዊ ማድረግና በቁጥጥር ሥር መስራት ከተቻለ ብቻ ነው ወደ ሰላም ማምራት የምንችለው።

- በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ያሉት ትክክል ስላልሆኑ አደብ መያዝ ያስፈልጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 8/2016 ዓ/ም
መቐለ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ነው አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት ፣ ትዕግስት ማጣት የሚመጣ ነው " - ኢዜማ በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያለውን ግምገማ በተመለከተ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። …
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" አሁን ላይ ያሉ ችግሮች ምፍትሄ እስካላገኙ  ስለ ምርጫ ማሰብ #ቀልድ ነው " - አቶ ግርማ በቀለ

የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድረገዋል።

Q. የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ጥሰትን በተመለከተ ስለሚነሱ ጉዳዮች የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይላል ?
 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በእጅጉ ተጥሰዋል።

መንግሥት የፓለቲካ ምህዳሩን ያስፋልን ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይደረግ፣ በአገሪቱ ስለተፈጠሩት ችግሮች በጠረንጴዛ ዙሪያ እንወያይ እያልን ስንጮህ ነበር።

አሁን ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አልፎ ፦
° የፓርቲ መሪዎችን ከቤት አውጥቶ ገድሎ የመጣል፣
° የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ሕገ መንግስቱ የሰጣቸውን መብቶች ተገፈው ምን እንዳጠፉ ሳይነገር የሚታሰሩበት ከባድ ደረጃ ላይ የደረስንበት ጊዜ ነው። "

Q. ስለ ሀገሪቱ የጸጥታና ደኀንነት ሁኔታ የፓርቲያችሁ ግምገማ ምንድን ነው ? 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" ለ6 ዓመታት በብልጽግና፣ ከኢህዴግም በከፋ ሁኔታ አገራችን ያልተረጋጋችበትና በሰላም ረገድ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የወደቅንበት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።

የአገራዊ እሴቶችንና ገንቢ አስተሳሰቦችን ወደ ኋላ ጥሎ ከውጪ የሚመጣውን የወቅቱ ፓለቲካ አስተሳሰብ ይዞ፣ በዛም ተሞክሮ ላይ አግላይና ጠቅላይ የሆነ የፓለቲካ ስርዓት ነው። 

ይህ በመሆኑም አገራችን ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማኀበራዊ ምስቅልቅሎችና ከፍተኛ ችግሮች ዳርጓታል።

የተፈጠረውን ምስቅልቅል ለማስወገድ ፦
- በአገሪቱ ውስጥ አገራዊ መግባባት መፍጠር፣ 
- በሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መናቆርና ልዩነት የማራገብ ሂደት ማርገብ፣
- ብሔራዊ እርቅ የሚወርድበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለብን፤
- ሁሉም ባለድርሻ አካላት ባለቤት ሆነው የመፍትሄው አካል መሆን አለባቸው። "

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን ፈትኖታል። ፓርቲዎ ለመንግስት ያለው መልዕክት ምንድን ነው ?

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" በፓለቲካ መሪነት ሳይሆን እንደ አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ እየኖርን ያለነው በአንዳች ተዓምር እንጂ የእውነት የወር አስቤዛ ለአንድ ቀን እንኳ የማይሆንበት ደረጃ ላይ የደረስንበት ሁኔታ ነው ያለው። 

የዛሬ 20 ዓመት በአንድ ብር አንድ ሊትር ወተት ገዝቼ ነው ልጅ ያሳደኩት። አሁን ዋጋውን ሁላችንም እናውቀዋለን። ሕዝቡ ግን ይሄ ሁሉ እየሆነ በፈጣሪ እርዳታ አለ። "

Q. በቀጣዩ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመመቅረብ ምን ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" ➡️ የብሔራዊ መግባባትና የሀገራዊ እርቅ ጉዳይ ላይ ቁጭ ብለን እስካልተነጋገርን ድረስ፣

➡️ አገሪቱ ውስጥ ላሉት ፓለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ምስቅልቅሎች መፍትሄ እስካላበጀን ድረስ፤ 

➡️ ዋና ዋና የባለድርሻ አካላት ለዚች አገር ችግር መፍትሄ እስካልነደፉ ድረስ፣ እዚህ አገር ስለምርጫ ማሰብ ቀልድ ነው። "

Q. መልካም አስተዳደርን ስለመረዘው ብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ? 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" የዚህ አይነት ብልሹ አሰራር በአገራችን በታሪክ ውስጥ የገጠመን ጊዜ የለም በአጭሩ። አመሰግናለሁ ! "

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#HiberEthiopia #ሕብር

@tikvahethiopia