TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update

" ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው።

በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

ጉምሩክ ፤ " የሠነድ ምዝገባ እና ማጣራት ሂደቱን በአግባቡ እየሠራ ይገኛል " ብለዋል።

" የብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " ሲሉ አረጋግጠው " የቀረቡ ሠነዶች ያልተሟሉ እና ቀሪ ጉዳዮች ኖረው ተቀባይነት ያላገኙ ሠነዶች የሚስተናገዱት በዕለቱ የምንዛሪ ተመን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ " ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ " ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛ #የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#EthiopianCustomsCommission #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው። በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው…
#ጉምሩክ🚨

" አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! " - ጉምሩክ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦

" መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።

በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ  ይደረጋል።

ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ  መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። "

#EthiopianCustomsCommission

@tikvahethiopia