TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ይነበብ ! #ይሰራጭ !

• አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ?

• የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ?


(ይህ መረጃ ከፋና የምርመራ ዘገባ የተወሰደና አዘጋጁ መርማሪ ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንባቢያን ያሳውቃል)

(ፅሁፍ ዝግጅት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ)

ጉዳዩ እንዲህ ነው...

ታህሳስ 7 /2015 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘው አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በተጓደሉ የህክምና ባለሞያዎች ምትክ የሰው ኃይል ለማሟላት የቅጥር ማስታወቂያ ያወጣል።

በዚህም ማስታወቂያ መሰረት 286 ጠቅላላ ሃኪም፣ 67 የላብራቶሪ ባለሞያዎች፣ 117 የመድሃኒት ቤት ባለሞያዎች ፈተናውን ለመውሰድ ይመዘገባሉ።

ተወዳዳሪዎች በግልፅና በይፋ በወጣ የፅሁፍ ፈተና ማስታወቂያ ጥሪ መሰረት ጥር 3/2015 ዓ/ም ላይ ፈተና ወስደዋል። የፅሁፍ ፈተናውን በአብላጫ ውጤት ያለፉት ተወዳዳሪዎች ውጤቱን አይተው የቃል ፈተና ወስደዋል። ያሉ ተወዳዳሪዎችም በግልፅ ተለጠፈ።

ሆስፒታሉ ከተመዘገቡት ውስጥ ብቁ ናቸው ያላቸውን በአጠቃላይ 16 የጤና ባለሙያዎች፦
👉 8 ጠቅላላ ሀኪም
👉 5 ፋርማሲስት
👉 3 የላብራቶሪ ባለሞያዎች ይፋዊ ጥሪ አቅርቦ ቅጥር ፈፀመላቸው።

ከዚህ ለኃላ ባለሞያዎቹ የወር ደመወዝ ተከፏለቸው፣ እስከ መጋቢት 13 ጥዋት ድረስ በስራ ላይ ከቆዩ በኃላ ስብሰባ አዳራሽ ትፈላጋላችሁ ተብለው ይጠራሉ።

ባለሞያዎቹ ኑ ሲባሉ የመሰላቸው የ " እንኳን ደህና መጣችሁ " ስነስርዓት ነበር ነገር ግን ያልጠበቁት ዱብእዳ ተናገራቸው። ይህም የቅጥር ሂደቱ ላይ የህገወጥነት ጥርጣሬ ስላለ ምርመራ እስኪደረግ መታገዳቸው ተገለፀላቸው። እግዱን የሚመለከት ደብዳቤም ተሰጣቸው።

የእግድ ደብዳቤው መጋቢት 13 በሆስፒታሉ የበላይ ኃላፊ የተፃፈ ነው። ጥርጣሬ አለኝ ሂደቱ መረምራለሁ ያለው የሲደማ ፐብሊክ ሰትቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ነው።

ቢሮው ምንድነው የሚለው ?

- ከቅጥሩ ህጋዊነት ጋር በተያየዘ ጥቆማ ደረሰን እሱን አጣራን።
- የማጣራት ስራው የተሰራው በአጣሪ ቡድን ተቋዉሞ ነው። ቡድኑ ሁለት ሰዎች ነው ያሉት።
- የማጣራት ስራው የፈጀው ሁለት ቀን ነው።

ይኸው አጣሪ ቡድን ከሁለት ቀን የመረጃ ማሰባሰብ ስራ በኃላ የቅጥር ሂደቱ " ህገወጥ ነው " በሚል የህክምና ባለሞያዎቹ ቅጥር መሰረዝ አለበት የሚል ምክረ ሃሳብ ለቢሮው አቅርበዋል።

በዚህ ጥናት መነሻ ቢሮው " የተፈፀመው የስራ ቅጥር ተሰርዟል ፤ በምትካቸው አዲስ ማስታወቂያ ይውጣና የሰው ኃይል ይቀጠር " የሚል ውሳኔ አሳለፈ።

የቢሮው አጥኚ ቡድን ጥናት በተደረገበት ወቅት ሆስፒታሉ ምንም መረጃ ሳይደብቅ ሰጥቶታናል በሚል ምስጋና አቅርቧል። እውነት ሆስፒታሉ የደበቀው ነገር የለም ?

ጥናቱ ሲፈተሽ...

ለምን ቅጥሩ እንዲሰረዝ ተወሰነ ?


ይኸው 2 አባላት ያሉት አጥኚ ቡድን ወደ ሆስፒታሉ ሄጄ ከ " ሰው ሃብት አ/ደ/የሥ/ሂደት " አገኘሁ እና አሰባሰብኩ ባለው መረጃ መሰረት ለቅጥሩ መሰረዝ ምክንያቶች ናቸው ያላቸው፦

1. የአዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል የቅጥር ኮሚቴ ሕጉን ጠብቆ ቢቋቋምም የህክምና ባለሞያዎቹ ቅጥር ሲፈፀም ከኮሚቴው ሰብሰቢ አቶ በረከት አመሎ በስተቀር ሌሎች አባላት አልተሳተፉም የሚል ነው።

#ይህ_ሲጣራይህ የጥናቱ ውጤት የተሳሳተ ሲሆን ባለሞያዎቹ ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት የቅጥር ኮሚቴ አባላት ተሰብስበው በፈተናው አሰጣጥ ሂደት ላይ የተወያዩበትና የምልመላ መስፈርቶችን በተመለከተ ውሳኔ ያሳለፉበት ቃለ ጉባኤ ሰነድ ተገኝቷል። በዚህም የኮሚቴው ሰብሰቢ እና ፀሀፊ ጨምሮ 9 አባላት ውሳኔውን በፊርማቸው አፅድቀዋል።

2. ሁለት (2) የ ' ጠቅላላ ሃኪም ' የስራ መደብ ላይ የተቀመጡና አንድ (1) የላብራቶሪ ቴክኒሻን መደብ ላይ የተቀጠረ የህክምና ባለሞያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመመሪቂያ ውጤት CGPA ሳይኖራቸው በቀጥታ የፁሁፍ ፈተና ወስደው የተቀጠሩ ናቸው የሚል ነው። አቶ ታደሰ ዩኤ የተባሉ የጥናት ቡድኑ አባል ሄዳቹ በዶክመት ውስጥ CGPA አላገኛችሁም ተብለው ሲጠየቁ " አላገኘንም፤ ፋይላቸው ውስጥ የለም " ብለዋል።

#ይህ_ሲጣራ፦ ሆስፒታሉ በቀን 07/04/2015 የቅጥር ማስታወቂያ ካወጣ በኃላ ከቀረቡ በርከታ ቁጥር ካላቸው እጩዎች መካከል በCGPA ውጤታቸው መሰረት ለፅሁፍ ፈተና ተወዳዳሪዎችን ሲጠራ CGPA የላቸውም የተባሉት ባለሞያዎች ውጤታቸው ተገልጾ ነጥብም ተሰጥቷቸው ለፅሁፍ ፈተና መጠራታቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤትም በማስታወቂያ ቦርድ ለህዝብ ተገልጿል። ሆስፒታሉ ቀርቦልኛል የሚለውና በህክምና ባለሞያዎቹ እጅ ላይ ያለው ውጤት ልዩነት የለውም።

3. የላብራቶሪና የፋርማሲ ባለሞያዎች ፈተና ያወጣው የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲሆን ነገር ግን ፈተናውን እንዲያዘጋጅ እና እንዲፈትን ኮሌጁ በደብዳቤ መጠየቁን የሚያሳይ ሰነድ አላየንም የሚል ነው። አቶ ታደሰ የተባሉት የአጣሪ ቡድኑ አባል ወደ አዳሬ በሄድንበት ወቅት " መረጃ ክፍል ውስጥ ደብዳቤ አላገኘንም፤ አልሰጡንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ እዚህ ጋር ሌላኛዋ የጥናት ቡድን አባል ወ/ሮ አይናለም አረጋ፤ ከጥናት ውጤቱ ጋር ፍፁም የማይገናኝና የሌለ " ተወዳዳሪዎቹ ጭራሽ ፈተና አልተፈተኑም " ብለዋል። በዚህም ንግግራቸው ከራሳቸው የጥናት ውጤት ጋር የሚጋጭ ሀሳብ ሰንዝረዋል።

#ይህ_ሲጣራ ፦ " የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና እንዲያዘጋጅ ከአዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል በደብዳቤ አልተጠየቀም እንዲሁም የህክምና ባለሞያዎቹ ፈተና ሳይወስዱ በቀጥታ የተቀጠሩ ናቸው " የሚለው የጥናቱ ውጤት ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አሳውቋል።

ኮሌጁ የተላከለት ደብዳቤ በፋይል ውስጥ አለ፣ በደብዳቤው መሰረትም ኮሌጁ ፈተና ፈትኖ ውጤቱን ከሆስፒታሉ ጋር ተፈራርሞ ማስረከቡን ገልጿል። ፈተናውን ያወጡና የፈተኑ አካላትም ከአዳሬ ሆስፒታል አበል ተከፍሏቸዋል።

በምርመራ ስራ ወቅት ተወዳዳሪዎቹ ፈተና ሲፈተኑ የሚያሳዩ ፎቶዎች የተገኙ ሲሆን ፎቶዎቹ ከሌሎች ሰነዶች ጋር ከሆስፒታሉ ማህደር ውስጥ ሆን ብለው እንዲጠፉ ተደርገዋል።

4. ሌላው የጥናቱ ግኝት የሆስፒታሉ ሲኒየር ሃኪሞች ሆኑ የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና ሲያወጡ " በፈተናው ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ምንም አይነት እንከኖች ቢኖሩ ተጠያቂነት እንደሚኖር አውቀው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አልተፃፈላቸውም " የሚል ነው።

#ይህ_ሲጣራ፦ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ እንዲህ አይነት ደብዳቤ መፃፍ እንደማያስፈልግ ይህ የሚታወቅ መሆኑን ገልጿል። ከዛ በኃላም ለኮሌጁ አዳሬ ለፈተና ጥያቄ እና ማስፈተን የትብብር ደብዳቤ የፃፈ ሲሆን ይህን መሰል ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዳላከ ኮሌጁ አስረግጦ ተናግሯል።

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል...

ይህ የምርመራ ስራ ሲሰራ የሆስፒታሉ የስራ ኃላፊ ወይም የሰው ሃብት ልማት ኃላፊው በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ፣ በስልክ ቢጠየቁም ምላሽ ሊሰጡ አልፈለጉም። ሰዎቹ ስልክም አያነሱም።

ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ምርመራው ሲሰራ በስራ ገበታቸው ላይ ጭራሽ ሊገኙ አልቻሉም።

ሲፈለጉ የጠፉት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ማራዶና ዘለቀ እና የሰው ሃብት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ተፈራ ናቸው።

የአዳሬ የስራ ኃላፊዎች ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም።

ያንብቡ : telegra.ph/TikvahEthiopia-08-15

በፋና ቴሌቪዥን የዩትዩብ ሊንክ ይመልከቱ ፦ youtu.be/n4CvuCIDuxc