የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር " ታይተዋል " ስለተባሉ #ዩፎዎች ምንነት ባወጣው ሪፖርት ምን አለ ?
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር /ፔንታጎን/ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (#ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱ ፦
➡ በአውሮፓውያኑ የ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ #የስለላ_አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው።
➡ የአሜሪካ መንግሥት ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ ምንም ዓይነት ” ማስረጃ የለውም።
➡ ዩፎ ተብለው መታየታቸው ከተገለጹት መካከል አብዛኞቹ ክስተቶች ከምድር ላይ የተነሱ የተለመዱ ነገሮች ናቸው።
➡ የተደረገው ምርመራ ውጤት በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ዩፎዎችን በተመለከተ ያለውን እምነት በቀላሉ የሚለውጠው አይደለም።
➡ የዩፎዎችን መኖር በተመለከተ በሕዝቡ ውስጥ ጠንካራ እምነት አለ እና ለዚህም ፊልሞች፣ መጻሕፍት፣ ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ያለውን አመለካከት በቀላሉ መለወጥ አዳጋች ነው።
➡ አስካሁን የተደረጉት ሁሉም ምርመራዎች እና ዝርዝር መረጃዎች በአብዛኛው እንግዳ ፍጡራን ወደ ምድር ስለመምጣታቸው የሚያመለክቱ ምንም ማስረጃዎች የሉም።
➡ ታዩ የተባሉት ነገሮች የተለመዱ ነገሮች እና በተሳሳተ መንገድ ከመረዳት የመነጩ ናቸው።
➡ ዩፎዎችን በተመለከተ የተደረገው ምርመራው ከ1945 (እአአ) ጀምሮ ያሉ መዛግብትን እና ምሥጢራዊ ሰነዶችን ጨምሮ በመንግሥት የተደረጉ ይፋዊ ምርመራዎችን ያከተተ ነው።
➡ በርካቶች ዩፎዎች ናቸው ያሏቸው ነገሮች ክብ በራሪ ነገሮችን ሲሆኑ፣ እነዚህ ግን በዚያ ዓይነት ቅርጽ ተሠርተው ሙከራ ሲደረግባቸው የነበሩ አውሮፕላኖች ናቸው። በካናዳ የተሠራውን ተመሳሳይ ቦምብ ጣይ አውሮፕላንም አንዱ ማሳያ ነው።
ለረጅም ዓመታት የአሜሪካ መንግሥት እነዚህን ምንነታቸው ያልታወቀ በራሪ አካላትን በተመለከተ በርካታ የምርምር ፕሮግራሞችን አካሂዷል፤ ነገር ግን አብዛኞቹ በእንግዳ ፍጡራን ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች #በምሥጢር ተይዘው ቆይተዋል።
አሁንም ድረስ በርካቶች እንግዳ ፍጡራን እንዳሉ የሚያምኑ ሲሆን፣ በአንድ ወር ውስጥ ከ50 አስከ 100 የሚደርሱ ዩፎዎችን መታየታቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች ይቀርባሉ።
መንግሥት እነዚህን ክስተቶች ይደብቃል የሚለው ግምትም አሁንም መቀጠሉን የፔንታጎን ሪፖርት አመልክቷል።
ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ የስለላ መኮንን ዴቪድ ግሩሽ በአሜሪካ ምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ቀርቦ የአሜሪካ መንግሥት የእንግዳ ፍጡራን አካላትን እና በራሪ ነገሮችን ይዞ እንደሚገኝ እንደሚያምን መስክሯል።
ግለሰቡ ይህ እምነቱ እና ለም/ቤቱ የሰጠው ቃል በሰነዶች ላይ ያሉ መረጃዎችን፣ የድምጽ ቅጂዎችን እና ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ያደረገውን ውይይቶችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግሮ ነበር።
Via BBC
@tikvahethiopia