TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ከተማ እየተረጋጋ ቢሆንም፤ የሸቀጣ ሸቀጥና የእህል አቅርቦት ማነስ በአፋጣኝ እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ካማሽ ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሰላምና #መረጋጋት እየተመለሰች መሆኗንም መስክረዋል። በመንገድ እጦት በአሶሳ ከተማ የተከማቸው ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር፣ ዘይት፣ ዱቄትና ሌሎችም ሸቀጣሸቀጦች ሰሞኑን ወደ ካማሽ ዞን እንደሚጓጓዙ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል #መረጋጋት በሚታይባቸው አካባቢዎች ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ በላይ መሰብሰቡን እንዲሁም ግጭት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የታቀደውን ያህል ገቢ መሰብሰብ #አለመቻሉን የክልሉ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ...

•በተረጋጉ አካባቢዎች ካቀደው እስከ 163 በመቶ
•ባልተረጋጉ ስፍራዎች ካቀደው እስከ 43 በመቶ ገቢ ሰብስቧል

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ #ሰላምና #መረጋጋት ለማምጣት የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ እየተወጡ #አለመሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሀና እንዳሉት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ለውጥ ለማምጣት ህዝቡ ተቃውሞዎች ሲያደርግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተሳታፊዎች ነበሩ፤ ለውጡ ከመጣ በኋላም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መንግሥትና የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሁከቶቹ ተበራክተዋል ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩትን የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጠና ቡድን ማዋቀሩን በመጥቀስ፤ በቀጣይ ለሚሠራቸው ሥራዎች አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡንም ገልጸዋል፡፡ ሰላም ከሌለ ልማትና የመኖር ነፃነት ስለማይኖር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️

በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።

ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።

"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።

በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።

በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።

ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።

ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።

ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።

ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።

በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።

በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።

አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ #ጀምሯል። ጨፌው ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም እንደሚገመግም ይጠበቃል። እንዲሁም በክልሉ ያለው #ሰላም#መረጋጋት እና የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚመክርም ተገልጿል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል...

ትናንት ተዘግቶ የዋለው የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ ዛሬ ተከፍቷል። በአካባቢው #መረጋጋት የሚታይ ሲሆን፣ በታጣቂዎች ቁልፍ የተነጠቁ ተሽከርካሪዎች አልፎ አልፎ መንገድ ዘግተው/ቁመው ይታያሉ።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
(ትኩረት‼️)

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየተዘረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ በጫኝና አውራጆች መካከል በተነሳ ግጭት የተጀመረው አለመረጋጋት ወደተለያዩ አካባቢዎች #መስፋፋቱን ነው ነዋሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አስተያዬታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹እረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ከብቶቻችንም እየተነዱ እየተወሰዱ ነው፡፡ ትናንት ገበያ መውጣት አልቻልንም፤ ዛሬም #በዓሉን ለማክበር ተቸግረን ፍርሃት ውስጥ ነን›› ብለዋል፡፡

ማምቡክ መንደር 49 አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ገበያ ነበር፤ ገና ከመቆሙ በጠዋቱ ተበትኗል፡፡ በጫካው ውስጥ ተኩስና ቀስት ማስወንጨፍ አለ፡፡ ከዳንጉር አካባቢ ነው የግጭቱ መሠረት ያለው፤ መንግሥት በፍጥነት ሊደርስልን ይገባል፡፡ ሰዎች በየጫካው እየሞቱ ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በበኩሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር አንጻራዊ #መረጋጋት ላይ መሆኑን ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በአሽከርካሪ እና ጫኝና አውራጅ ሥራ በተሠማሩ ወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ላይ ችግሩን የፈጠሩ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን እና ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት #እንዳይጠፋ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የሚመሩት ልዑክ ካርቱም ገብቷል፡፡ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስነበበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ወደ ሱዳን ያቀናው በሱዳን የሽግግር መንግሥትን በይፋ ለመመሥረት በሚከናወነው ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ነው፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ኦማር አልበሽር መንግሥት የሦስት አስርት ዓመታት ቆይታው በሕዝባዊ ተቃውሞ ተናግቶ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሲመሠረት ሱዳን ወደ ቀውስ እንደምትገባ ብዙዎች ገምተው ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ባደረጉት ተከታታይ ጥረት ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና ሲቪል የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በዚህም #ሱዳን ወደ #መረጋጋት እንደምትገባ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የሽግግር መንግሥቱ ምሥረታ ላይ ለመገኘትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ጠዋት ካርቱም ገብቷል፤ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎለታል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia