TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል " - ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

እያንዳንዳቸው 4 ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ስምንት ሚሊዮን ብር ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሽ መደረጉን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

ተቋሙ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል ፤ እነዚህ ሁለት ዕጣዎች ብሔራዊ ሎተሪ ከሚያሳትማቸው ከፍተኛ ዕጣ የሆነው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬቶች ናቸው ብሏል።

በእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከቀረቡት 5 ቲኬቶች ሶስቱ ቀርበው 12 ሚሊዮን ብር ሁለት አሸናፊዎች ቢረከቡም የቀሪዎቹ ሁለት ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ሲል አሳውቋል።

ጳጉሜ 2015 ዓ.ም የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የሁለቱ ቲኬቶች ወይም የ8 ሚሊዮን ብር አሸናፊ በቀን ስራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ ሲሆን ዕጣው ከወጣ ከ3 ወር በኋላም ወስዷል።

ሌላኛው አሸናፊ የቀን ሰራተኛው የሚሰራበት መኪና አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ሲሆን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ መጥቶ የ4 ሚሊዮን ብር ሽልማቱን መውሰዱን ቢቢሲ አማርኛው ክፍል የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውና የተለያዩ ውድድሮችን ያካተተው 3ኛው ዙር “እችላለሁ”ዘመቻ በይፋ ተጀምረ!

ባንካችን አቢሲንያ የሴቶችን የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለመወጣት ለሴቶች የተሻለ ጥቅም የሚያስገኙ አደይና ዛሃራ የተሰኙ የሴቶች የቁጠባ ሂሳቦችን ማቅረቡ ይታውቃል፡፡

አገልግሎቱን መሰረት በማድረግ በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) አስመልክቶ ለሶስትኛ ጊዜ እችላለው በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ውድድር ይፋ አድርጓል።

ውድድሩ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም.  ድረስ በሶስት የተለያዩ የውድድር ዘርፎች የሚካሂድ መሆኑን አስታውቋል። #ICAN
OMEGA COMPUTER TRADING

ሁሉንም አይነት ላፕቶፖች ያገኛሉ !!!

ከ4ተኛ አስከ 13ተኛ Generation ከ core i3  አስከ core i9 ከ 2GB አስከ 16GB Dedicated Graphics card ያላቸው
👉 አዳዲስ ጌሚንግ ላፕቶፖች
👉 ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች
ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች በ ጥራት እና በ ብዛት ላፕቶፖችን አና ዴስክቶፖችን ከ እኛ ጋር ያገኛሉ
👉 እንገዛለን እንሸጣለን ይዘው ይምጡ ይዘው ይሒዱ
👉ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር

የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓችን ለማየትና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ - Telegram-  👉 https://t.iss.one/Omegacom21

አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ህንፃ ግራውንድ
Inbox me - @Yime29
ስልክ - 0974060288
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀዋሳ " ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች " ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ…
#ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ የህዝብ ትንራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲ) የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ፤ " የነዳጅ ጉዳይ ስቃያችንን አበላን ፤ የመፍትሄ ያለህ !! " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ፤ "ሰርተን ከምንገባበት ለነዳጅ ሰልፍ ቆመን የምንውለበት እየበለጠ ነው " ብለዋል።

የነዳጅ ችግሩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑም በመግለፅ "
ካልሰራን ልጆቻን ምን ይብሉ ? ፤ እኛስ ምን በልተን እንደር ? ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት በዚሁ በሀዋሳ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች ፤ " በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " በሚል ምሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተው ነበር።

አሽከርካሪዎች ፤ ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ገልጸው ነበር።

በወቅቱ እየተነሳ ላለው ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ፤ ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ችግሩም " #ወደፊት_ይቀረፋል " የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ማመልከታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
ልዩ ትኩረት የሚሻው የጎርፍ አደጋ !

በሶማሌ ክልል ከተከሰተ ከወራት በላይ ያቆጠረው የጎርፍ አደጋ አሁንም የክረምት ወቅት ከመድረሱ በፊት ልዩ ትኩረት አንደሚሻ ተፈናቃዮችና ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አንድ ተፈናቃይ በሰጡት ቃል ፦

" አሁን ከከፈልነው የስቃይ ዋጋ በላይ ሕይወታችንን እንዳናጣ አሁንም ቢሆን ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል።

የክረምት ወቅት እየመጣ የጎርፉ መጠን መጨመረ የሚታወቅ ነው፡፡ ሁሉም ከፍተኛ ስጋት አለው፡፡ ሁሉም የገፈቱ ቀማሽ መንግስት ወደ ሌላ ቦታ ሰፈራ ሊሰጠን ይገባል የሚል ፍላጎት ነው ያለው " ብለዋል፡፡

ለሌላኛው ተፈናቃይ ፦

" 30 ከብቶች በጎርፉ ተወስደዋል፡፡ ቤቴ ሰጥሞ ወድሟል፡፡ አሁንም ችግሩ እንዳይደገም ምንም ዋስትና የለም፡፡ እንዲህ አይነት ችግር ነው ያለው " ሲሉ አማረዋል፡፡

ከክልል አደጋ መካላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ያነጋጋርናቸው አንድ ሠራተኛ ፦

" ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እየተሞከረ ነው። ሆኖም ለዘላቂ መፍትሄ የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።

ለተፈናቃዮች ለአሁንም በቋሚነትም የሚቋቋሙበት ድጋፍ ያስፈልጋል። በተለይም እናቶች፤ አረጋዊያንን፤ ሕጻናት የክረምቱ ወቅት ሲመጣ በድጋሚ ለችግሩ ሰለባ ይሆናሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለን " ብለዋል።

ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-08-2
#ETHIOPIA

ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ።

ተሽከርካሪዎቹ እና እቃዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የተፈቀደው በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የሚቀርቡ ሠነዶች አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው ነው ተብሏል።

ይህም የሚሆነው ለመጨረሻ ጊዜ  መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሸን ከፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን በመጥቀስ በሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) የተፃፈ ደብዳቤን  ለጉምሩክ ኮሚሽን ተልኳል።

ተሽከርካሪን ጨምሮ 28 ምርቶች ከጥቅምት 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደይፈቀድላቸው መወሰኑ ይታወሳል።

የውጭ ምንዛሬ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች ጋር ተያይዞ በአፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ማስተካከያ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በጥቅምት ወር በወጣው እና የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው 38 ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱ ምርቶች የሆኑ ግን ደግሞ ምርቶቹ እና ተሽከርካሪዎቹ በሕግ በተደነገገ ፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ከሆነ  በተደረገው ማስተካከያ ክልከላው አይመለከታቸውም ተብሏል ።

ተሽከርካሪዎች ጎረቤት አገር ወደብ ወይም ጉምሩክ ጣቢያ በደረሱበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ (ማሻሻያ) ቁጥር 1287/2015 አንቀጽ 2(24) ለአዲስ ተሽከርካሪ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሟሉ ሆነው ነገር ግን ይህን ውሳኔ ሲጠብቁ የተሽከርካሪው እድሜ ያገለገለ ምድብ ውስጥ የገባባቸው ከሆነ በክልከላው ምክንያት በጎረቤት አገር ወደብ ወይም በጉምሩክ ጣቢያ የቆዩበት ጊዜ ሳይታሰብ እድሜው ጎረቤት አገር ወደብ ወይም የጉምሩካ ጣቢያ እስከደረሰበት ያለውን ጊዜ ድረስ ብቻ በማስላት እንዲስተናገዱ ማስተካከያ መደረጉ ተነግሯል።

የቀረጥ ነፃ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪ ክልከላው እንደማይመለከታቸው ማስተካከያውን የሚያስረዳው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የውጪ ምንዛሬ ክልካላው በተመለከተ በጥቅምት ወር 2015 ዓ/ም የተጻፈው ደብዳቤ እና በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ማብራሪያዎች መሻራቸውንና በማስተካከያው መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆን መወሰኑን ከደብዳቤው ላይ ተመልክተናል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን  በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው  ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia
ሊቨርፑል ወይስ ማንችስተር ሲቲ (#ይገምቱ!) https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk  

ለ3 የቴሌግራም ተከታዮቻችንን ለእያንዳንዳቸው የ400 ብር ካርድ የሚያሸልም!

💥💥 የውድድሩ ሕግጋቶች 💥💥

1. ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk ይቀላቀሉ,
2. ግምትዎን በሃሳብ መስጫው (#COMMENT) ላይ ያስቀምጡ,
3. ውጤት ማስተካከል እና ከላይ የተጠቀሱትን ህግጋቶች የማያከብሩ ከውድድሩ #ውጭ ይሆናሉ,
4. ከ 3 በላይ ትክክለኛ መላሾች የሚለዩት #በዕጣ ይሆናል።

መልካም ዕድል!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #LIVMANCITY #EPL #liverpoo.l #ManCITY
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር " ታይተዋል " ስለተባሉ #ዩፎዎች ምንነት ባወጣው ሪፖርት ምን አለ ?

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር /ፔንታጎን/ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (#ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

በሪፖርቱ ፦

 በአውሮፓውያኑ የ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ #የስለላ_አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው።

የአሜሪካ መንግሥት ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ ምንም ዓይነት ” ማስረጃ የለውም።

ዩፎ ተብለው መታየታቸው ከተገለጹት መካከል አብዛኞቹ ክስተቶች ከምድር ላይ የተነሱ የተለመዱ ነገሮች ናቸው።

የተደረገው ምርመራ ውጤት በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ዩፎዎችን በተመለከተ ያለውን እምነት በቀላሉ የሚለውጠው አይደለም።

የዩፎዎችን መኖር በተመለከተ በሕዝቡ ውስጥ ጠንካራ እምነት አለ እና ለዚህም ፊልሞች፣ መጻሕፍት፣ ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ያለውን አመለካከት በቀላሉ መለወጥ አዳጋች ነው።

አስካሁን የተደረጉት ሁሉም ምርመራዎች እና ዝርዝር መረጃዎች በአብዛኛው እንግዳ ፍጡራን ወደ ምድር ስለመምጣታቸው የሚያመለክቱ ምንም ማስረጃዎች የሉም።

ታዩ የተባሉት ነገሮች የተለመዱ ነገሮች እና በተሳሳተ መንገድ ከመረዳት የመነጩ ናቸው።

ዩፎዎችን በተመለከተ የተደረገው ምርመራው ከ1945 (እአአ) ጀምሮ ያሉ መዛግብትን እና ምሥጢራዊ ሰነዶችን ጨምሮ በመንግሥት የተደረጉ ይፋዊ ምርመራዎችን ያከተተ ነው።

በርካቶች ዩፎዎች ናቸው ያሏቸው ነገሮች ክብ በራሪ ነገሮችን ሲሆኑ፣ እነዚህ ግን በዚያ ዓይነት ቅርጽ ተሠርተው ሙከራ ሲደረግባቸው የነበሩ አውሮፕላኖች ናቸው። በካናዳ የተሠራውን ተመሳሳይ ቦምብ ጣይ አውሮፕላንም አንዱ ማሳያ ነው።

ለረጅም ዓመታት የአሜሪካ መንግሥት እነዚህን ምንነታቸው ያልታወቀ በራሪ አካላትን በተመለከተ በርካታ የምርምር ፕሮግራሞችን አካሂዷል፤ ነገር ግን አብዛኞቹ በእንግዳ ፍጡራን ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች #በምሥጢር ተይዘው ቆይተዋል።

አሁንም ድረስ በርካቶች እንግዳ ፍጡራን እንዳሉ የሚያምኑ ሲሆን፣ በአንድ ወር ውስጥ ከ50 አስከ 100 የሚደርሱ ዩፎዎችን መታየታቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች ይቀርባሉ።

መንግሥት እነዚህን ክስተቶች ይደብቃል የሚለው ግምትም አሁንም መቀጠሉን የፔንታጎን ሪፖርት አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ የስለላ መኮንን ዴቪድ ግሩሽ በአሜሪካ ምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ቀርቦ የአሜሪካ መንግሥት የእንግዳ ፍጡራን አካላትን እና በራሪ ነገሮችን ይዞ እንደሚገኝ እንደሚያምን መስክሯል።

ግለሰቡ ይህ እምነቱ እና ለም/ቤቱ የሰጠው ቃል በሰነዶች ላይ ያሉ መረጃዎችን፣ የድምጽ ቅጂዎችን እና ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ያደረገውን ውይይቶችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግሮ ነበር።

Via BBC

@tikvahethiopia