#ዓድዋ #ፒያሳ
የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ እንደ ከዚህ ቀደሙ በ " ምኒሊክ አደባባይ " በዓሉን ማክበር የሚፈልግ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ተሰብስቦ እንዲያከብር አልተደረገም የሚል ቅሬታ ያደረባቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አንድ በጥዋት በዓሉን አከብራለሁ ብሎ ወደ ፒያሳ " ምኒሊክ አደባባይ " ያቀና የአዲስ አበባ ነዋሪ ፥ ምኒሊክ አደባባይ በከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ ስር እንደነበር ፣ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ብቻ ማለፍ እንደሚቻል፣ ጥብቅ የሆነ ፍተሻም እንደነበር ገልጿል።
በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያም ፍቃድ ከተሰጠው ውጭ መግባት እንደማይቻል በዚህም በዓሉም ለማክበር እንዳልቻለ ጠቁሟል።
ይህ የህዝብ በዓል በመሆኑ ህዝብ በመረጠው መንገድ ወይም ተካፋይ በሆነበት መንገድ ሊከበር ይገባ ነበር ሲል ያደረበትን ቅሬታ አጋርቷል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፤ " ዛሬ ከባለፈው ዓመት በበለጠ የዓድዋ በዓልን ለማክብር የመጣ ሰው ከቴዎድሮስ አደባባይ ጀምሮ መግባት ባለመቻሉ ሲመለስ ነበር። ፈረስ እና የተለያዩ የዓድዋ አልባሳትን የለበሱ ሰዎችም ሲመለሱ ነበር " ብሏል።
" በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያ እየገቡ የነበሩትም በቀበሌ ይመስለኛል ባጅ የተሰጣቸው ብቻ ናቸው " ያለው ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ በዓሉ ሁሉም ለማክበር ባለመቻሉ እንዳደበዘዘው ጠቁሟል።
ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ " ካለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ ዓድዋን ከፒያሳ ምኒሊክ አደባባይ ለማላቀቅ ስራዎች የተሰሩ ይመስለኛል " ሲል ገልጾ " የኔ ጥያቄ የተገነባው ዓድዋ መታሰቢያ ከዚህ በኃላ ባለስልጣናት እና የሚፈልጉት ሰው ብቻ በብቸኝነት ለማክብረ ነው ? ወይስ በዓሉን ማክበር የሚፈልግ ህዝብ ተሰብስቦ እንዲከበርበት ነው ? " ብሏል።
መንግሥት የ128ኛው ዓድዋ ድል በዓል ከከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ ክብሩን በጠበቀ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን እየገለፀ ይገኛል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓድዋ128 #ዓድዋ ፕሬዝዳንት ሥህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ ለሚከበረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት ትግራይ ክልል ገብተዋል። ፕሬዝዳንቷ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከመቐለ በሄልኮፕተር ወደ ዓድዋ በመጓዝ ላይ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የዓድዋ በዓል የፌደራል መንግስት ባካተተ መልኩ መከበር የቆመው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ነበር።…
#ዓድዋ
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለልስጣናት ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በዓሉን ለማታደም በስፍራው ተገኝተዋል። መኮንኖቹ በበዓሉ ስፍራ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የታደመበት መሆኑን አመልክቷል።
ፎቶ፦ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል እና ትግራይ ቴሌቪዥን

Photo
#Update
በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ባንዴራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ፣ የትግራይ ክልል ፣ የአፍሪካ ህብረት ባንዴራ በፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተወካይ በሆኑት ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራድያ ተሰቅሏል።
የባንዲራ መስቀል ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር ታጅቦ መከናወኑን በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

#ዓድዋ " ኢትዮጵያ ምን ጊዜም አሸናፊ ናት " - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ በተመረቀው " የዓድዋ ድል መታሰቢያ " እየተከበረ ይገኛል። በዚሁ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መሪዎች፣ የተለያዩ ባለልስጣናት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሏል። በዓሉ በሀገር መከላከያ ወታደራዊ ትርኢት እና በሌሎችም ዝግጅቶች…
ፎቶ፦ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ፒያሳ በሚገኘው የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " እየተከበረ በሚገኘው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ትርኢት አቅርቧል።
Photo Credit - Leuel Masrsha (WMCC)
@tikvahethiopia
Photo Credit - Leuel Masrsha (WMCC)
@tikvahethiopia