TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ...ነገ ሀገር #ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት #ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
.
.
ዛሬማ ሰላም ነው #ፎክር እንጂ...የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ህፃናት #ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ...የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።

.
.
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር...አቅራራ...ህዝብ ቀስቅስ...ተነሳ በለው፣ ግደለው በል!
.
.
የለኮስከው #እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን #ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ!

#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ🔝

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተነሳው #እሳት ጉዳት ሳያደርስ #ጠፍቷል፡፡ ደብረ ብርሐን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ ቃጠሎው የተነሳው በግቢው ውስጥ ከተከማቸ ቆሻሻ ላይ መሆኑን አብመድ ዘገቧል። ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባደረጉት ጥረትም ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

ስብስቤ ዋሻ-#ባሌ_ዲንሾ_ፓርክ አቅራቢያ ወይም ወደ ዲንሾ በሚወስደው መንገድ ከፍታ ቦታ ላይ #እሳት እንድተነሳ ጥቆማ ደርሶናል። የሚመለከተው አካል ጉዳዩን ይመልከተው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀግሽ መካኒሳ #ቆሬ የሚገኘው ካምፕ ውስጥ #እሳት_አደጋ ተነስቷለል!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የእሳት_አደጋ_በጅግጅጋ

በጅግጅጋ ከተማ በ ቀበሌ 02 በልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ትላንት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

መነሻ መንስዔው ያልታወቀው እሳቱ የተነሳው ከአንድ ሱቅ መሆኑ ተገልጿል።

በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የተገለፀ ሲሆን እሳቱ በፍጥነት በመዛመቱ 7 የንግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ አድረሷል።

ድምሩ ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ነው።

#እሳት_አደጋ_በመቅደላ_ወረዳ

ትላንት ምሽት በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳት አደጋው መነሀሪያ ሸድ ላይ የተከሰተ ነበር።

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን እና ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ዘይቤ ድረገፅ፣ የመቅደላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia