#Infinix_Hot40
አዲሱ ኢንፊኒክስ 'Hot 40 pro' ስልክ ያለ ሃሳብ የፈለጉትን መተግበሪያ ለመጠቀም የሚያስችል ‘ Ultra speed helio G99’ የተሰኘ ፕሮሰሰር የተገጠመለት በመሆኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል!
#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries

ፍትህ ሚኒስቴር ፤ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በዚሁ መግለጫ ፤ የሽግግር ፍትህ የባለሞያዎች ቡድን የተሰጠውን ኃላፊነት በወቅቱ ማጠናቀቁን ገልጿል።
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው የመጨረሻ ረቂቅ ስራ እንዳለቀ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በመንግስት እንደሚፀድቅ ተመላክቷል።
(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Ethiopia
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች በቀጣይ ሳምንታት ከአደራዳሪዎች ጋር ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል " - የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት
የትግራይ ክልል የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የካቲት 19/2016 ዓ.ም ምሽት ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ውል ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ ምክንያት የህዝብ ስቃይና ሞት መቆም አልቻለም ፤ ስለሆነም ውሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተከታታይ ውይይቶች በማካሄድ ላይ ናቸው ብለዋል።
" ሰላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊና ፓለቲካዊ መንገድ በመጠቀም የትግራይ ህዝብ ጥያቁዎች እንዲመለሱ መስራት ተመራጭ አማራጭ ነው " ያሉት አቶ ረዳኢ ይህንን ታሳቢ በማድግ በሚቀጥሉት ሳምንታት የፕሪቶሪያ የሰላም ውል ፈራሚዎች ከአደራዳሪዎች ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል ብለዋል።
በትግራይ የተከሰተው ደርቅ ወለድ ረሃብና ሞት አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት የነበሩ ልዩነቶች ወደ አንድ ማምጣት እንደተቻለ የገለፁት አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፤ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት በጋራ እየተሰራ መሆኑ አብራርተዋል።
ሃላፊው አያይዘው እንደገለጹት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 18 ና 19 /2016 ዓ.ም ለ2 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል።
ካቢኔው የኢንቨስትመንትና የኤክስፓርት መመሪያ እንዲሁም የአርበኞች ኮሚሽን አሁናዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተሻሽሎ እንዲተገበርና እንዲቋቋም ወስኗል።
የትግራይ ህዝብ በከባድ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ውስጥ እያለ ፤ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በፀጥታ ሃይል አዛዦች ላይ እየተደረገ ያለው የተቀናጀና የተናበበ የማጥላላት ዘመቻ ያወገዘው ካቢኔው ፤ የትግራይ ህዝብና አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መንፈስ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት እንዲረባረቡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
መረጃውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዋቢ በማድረግ አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 ከእድሳትና የማስፋፋት ሥራ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር አሳውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት በረራዎች በተርሚናል 1 ይደረጋሉ። በሌላ በኩል…
#እንድታውቁት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የሀገር ውስጥ በረራ የሚያደርጉ መንገደኞች ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።
አየር መንገዱ ፤ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።
በዚህም የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የሚመጡ መንገደኞች በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንዲገቡ ብሏል።

#አሰቦት
" የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ጠብቁ " - አባ ገ/ሚካኤል
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት የተነሳ ሲሆን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ግን ወደ ገዳሙ በከፍተኛ ሁኔታ #እየተጠጋ እንደሆነና እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።
አባ ገ/ሚካኤል የተባሉ የገዳሙ አገልጋይ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በሰጡት ቃል ፤ የእሳት ቃጠሎ መነሻው በሥርዓት ያልታወቀና የሰደድ እሳት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከ3 ዓመታት በፊት ከፍተኛ እሳት ተከስቶ ለዘመናት የኖሩ የገዳሙን ብርቅዬ አራዊትና ደን ማውደሙን አስታውሰዋል።
በአሁኑ ሰዓት እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ፤ የእሳቱ አደጋ የሚከፋ ከሆነና መቆጣጠር ካልተቻለ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።
#Update
እሳቱ ለገዳሙ እንደማያሰጋ ተገልጿል።
#ተሚማ

Photo
#Ethiopia #Kenya
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እያደረጉት በሚገኘው ይፋዊ ጉብኝት በፕሬዝዳነት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፤ " የአቀባበል ስነስርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደርጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ ነው። " ብሏል።
ሁለቱ መሪዎች በድይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር አንስተው ይኽንኑ በቁርጠኝነት ማጠናከር እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተነግሯል።
" ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወሳኝ አጋጣሚ ሆኖ የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የበለጠ ለማዳበር ብሩህ መፃዒ ጊዜን ያመላከተ ሆኗል " ሲል የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኬንያ መግባታቸውና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንደተቀበሏቸው ይታወሳል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ኬንያ፣ ናይሮቢ ገቡ።
ፕሬዝዳንቱ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ኤርፖርት ሲደርሱ የኬንያ ምክትል ፕሬዜዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ተቀብለዋቸዋል።
ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ኬንያ የገቡት በኬንያ በሚካሄድ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ (UNEA-6) ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነው።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ኬንያ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በቅርቡ ከኢትዮ-ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገቡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው ይወያዩ እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።
ኬንያ ሁለቱን መሪዎች ለማቀራረብ ጥረት እያደረገች እንደሆነም የሚታወቅ ነገር የለም።

If you missed our first in-person information session in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹, we have another opportunity for you to meet our programs team and hear directly from Jasiri Community Fellows who have completed the program.
Register via https://bit.ly/49MPjIv
See you there.
Register via https://bit.ly/49MPjIv
See you there.
በሳፋሪኮም ያልተገደበ ኢንተርኔት የምንወደውን ሙዚቃ ያለምንም መቆራረጥ እናጣጥም! በ60 ብር ብቻ ያልተገደበ ዕለታዊ የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ!
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC https://t.iss.one/SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare 24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA

በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
928.6 KB
#ጋምቤላ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፦
" ግንቦት 13/2015 ዓ.ም. በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኝ ፒኝዋ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አንድ ግለሰብ መጥፋታቸውን ተከትሎ፣ በፒኝዋ ቀበሌ እና አጎራባች በሆነው በሌር ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በወቅቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የግለሰቦች እና የተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት እና ዘረፋ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚሁ ግጭት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በጎግ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም. በተለያዩ ወቅቶች በሰዎች ሕይወት እና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።
ኢሰመኮ ማረጋገጥ በቻለው መረጃዎች እና ማስረጃዎች መሠረት ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት አልፏል ፣ 113 ሰዎች ላይ አካል ጉዳት ደርሷል ፤ በግለሰቦች እና ተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። "
(ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የተከሰቱ ግጭቶችና የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ያስከተሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የላከልን ባለ 15 ገፅ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

በጋምቤላ ብቻ እንዲህ ሆኖ ነበር ....
ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦
➡ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው እና ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት ነገር ግን ሰዓቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ አንድ ሰው ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል።
➡ ግንቦት 14/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ወንዝ አካባቢ 2 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሞተዋል።
➡ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ተራራ አካባቢ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ 7 ሰዎች በጥይት ተገድለዋል።
➡ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በአካባቢው ማኅበረሰብ #የአእምሮ_ሕመም እንዳለበት የተገለጸ ሰው 04 ቀበሌ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ #በቡድን በተሰባሰቡ ወጣቶች ጥቃት #በስለት_ተወግቶ ተገድሏል።
➡ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገደማ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ፦
* የቀድሞውን የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፤
* የጋምቤላ ክልል መደበኛ ፖሊስ
* የጋምቤላ ክልል ሚሊሻ መለዮ ልብሶችን የለበሱ እና ሌሎች የታጠቁ ሰዎች በ3 የተለያየ አቅጣጫ በመግባት በቦታው የነበሩ 9 ሰዎችን በጥይት ገድለዋል፤ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
➡ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ 04 ቀበሌ፣ ቄራ ሰፈር አጉኛ አካባቢ የታጠቁ ሰዎች ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በመግባት ተኩስ ከፍተው፤ አንድ ሰው ሲገድሉ በሌላ አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡
የኢሰመኮ ባለ15 ገፅ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/85541

#Ethiopia #Kenya ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እያደረጉት በሚገኘው ይፋዊ ጉብኝት በፕሬዝዳነት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፤ " የአቀባበል ስነስርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደርጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ ነው። " ብሏል። ሁለቱ መሪዎች በድይይታቸው…
#Update
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የጋራ መግለጫ ምን ይላል ?
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኬንያ ያስራ ጉብኝትን እና ከፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉትን ምክክር ተከትሎ የኬንያ " ስቴት ሀውስ " የጋራ ነው ያለውን መግለጫ ዛሬ ምሽት አውጥቷል።
በዚህም መግለጫ ፤ ፕሬዚዳንት ሩቶ እና ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ከአፍሪቃ ቀንድ ደህንነት ጋር በተያያዘ ፤ በአህጉሪቱ ውስጥ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ማስጠበቅ ለኢኮኖሚ እድገትና ልማት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸው ተገልጿል።
በዚህም መሠረት ፤ ለሀገራት ግዛቶች ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እውቅና መስጠት ሉዓላዊነታቸውን ማክበርና ማስከበር እንደሚገባ አረጋግጠዋል።
ሕገ መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦችን እንዲሁም በአፍሪካ አገሮች የውስጥ ፖለቲካ የውጭ ጣልቃ መግባት እንደማይቀበሉት አስረግጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪ መሪዎቹ ፤ ሁለቱ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ አሳ ሀብት፣ ትራንስፖርት፣ አይሲቲ፣ ቱሪዝም፣ ጤና፣ ባህል እና ደን ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።
(ከስቴት ሀውስ የወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)