TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amahra #Oromia ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ወደቄያቸው ለመመለስ ከሰሞኑን በክልሎቹ መካከል የተደረሰበትን የመግባባት ስምምነት በተመለከተ ለሁለቱም ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ተከታዮችን ጥያቄዎች አቅርቧል። 👉 ከሞት ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመመልስ ፈቃደኛ ናቸው ? ይህንን ማወቅ ተችሏል ወይ ? 👉 በመንግሥት…
#Update

በጸጥታ ችግር ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደዬ ቄያቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ እንደነበር የኦሮሚያና አማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው አይዘነጋም።

የክልሎቹ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ከሁለት ወራት በፊት ሲገልጹ የነበረው፣ የጸጥታ ችግር የነበራቸውን የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በቅድሚያ ሰላምን መስፈኑን በማረጋገጥ ተፈናቃዮቹ እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እንደሚከናውን ነበር።

ይህን ተከትሎም ከተፈናቃዮቹ መካከል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች አንዳንዶቹ “ ተገደን ” ነው፣ ሌላኛዎቹ ደግሞ “ በፈቃዳችን ” ነው ባሉት ንግግር ወደ ወለጋ እየተመለሱ መሆኑን ሰሞኑን ሲገልጹ ተስተውለዋል።

ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው መለሰ፣ “ ከኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል የመመለስ ስለሆነ ፕሮግራሙን የያዘው፣ አመራርም መድቦ ሲያወያይ የቆዩት የፌደራልና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት ናቸው ” ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ “ አጠቃላይ መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ ሁለቱ ክልሎች በቅርቡ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣሉ ” ሲሉ አጭር የፅሑፍ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) እና ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ለገሰ ተደጋጋሚ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ተፈናቃዮች ከፊሎቹ " ተገደን ነው እየተመለስን ያለነው "፣ ከፊሎቹ ደግሞ " በፈቃዳችን ነው እየተመለስን ያለነው " የሚሉ ሀሳቦች ማቅረባቸውን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተላከላቸው የፅሑፍ መልዕክትም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በተጨማሪ ስለ ተፈናቃዮቹ ቅሬታ ምላሽ መስጠት ይችሉ እንደሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ በበኩላቸው፣ “ ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች፣ ከሱዳንም፣ ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየተፈናቀሉ በመጠለያ እንዲሁም Host community ሆነውም የሚኖሩ አሉ ” ብለዋል።

“ ይሄን ደግሞ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው” ያሉት ኃላፊዋ፣ “እናም ይሄ ከብዙ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ጉዳይ፣ በከፌተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተይዞ እየተከናወነ ያለ ጉዳይ ስለሆነ፣ እኛ በቂ ክልትትል ስሌለን፣ አሁንም ደግሞ ይሄ ነው ብለን ለሕዝብ የምንነግረው ያን ያክል ዝርዝር መረጃ ለእናንተ የምናደርሰው በአሁኑ ሰዓት አይኖረንም” ነው ያሉት ኃላፊዋ።

መረጃውን ያዘጋጀው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ባይቶና በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው  "ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የተባለ የፓለቲካ ድርጅት ሙሉ እውቅና ማግኘቱ አስታውቋል። በእነ ዶ/ር ፀጋዛኣብ ካሕሱ ከሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ደርጅት ተነጥሎ የወጣው ባይቶና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና ማግኘቱን ገልጿል። በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው …
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የፓለቲካ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና አገኘ።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ዓብለሎም መለስ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ "ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አግኝቷል " ብለዋል።

ፓርቲው የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያመሰገኑት ከፍተኛ አመራሩ ፣ ፓርቲው ለሚያካሂደው ፓለቲካዊ ትግል እውቅናው ምቹነት ይፈጥርለታል ብለዋል። 

ብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ ( ባይቶና ) የተባለ የትግራይ ተፎካካሪ ፓርቲ ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
                
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ ነበር " -  መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ ዓሥራት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ግድያ ዙሪያ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

- ከጥቃቱ በፊትም በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ ነበር።

" ሁል ጊዜ ዛቻው ልቀቁልን ነው፤ ልቀቁልን ነው የሚሉን። ገዳሙን መነኮሳቱ ለቀው እነሱ ገብተው ሊቀድሱበት ይሁን ፣ሊያስተምሩበት ይሁን ፣ ሊያቆርቡበት ይሁን ምንም አይገባኝም "

- ከዚህ ግድያ ክስተት ቀደም ብሎ የገዳሙ መጠበቂያ መሣሪያና የመናንያኑ እህል በኃይል ተወስዷል። ገዳሙም እንዲራቆት ተደርጓል። የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ካልሰጠ ወደ ፊትም ከዚህ ያልተናነሰ ወንጀል በገዳሙ ሊፈጸም የማይችልበት ምክንያት አይኖርም።

- ምንም እንኳ ለቤተክርስቲያን አባቶች መደብደብ መሰደድና መገደል የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው።

- ገዳማትን መጠበቅ የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ኃላፊነት ነው መንግሥት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የጸጥታ መዋቅሮቹ  ገዳማትን እንደማንኛውም ተቋም ሊጠብቅ ይገባል።

- በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ ምእመናን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መናንያን በገዳሙ ሕጋዊ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000011282222 (የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም)  ድጋፍ እናድርግ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የተ.ሚ.ማ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
ጠንካራ ሴት ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ በደንብ እንረዳለን፣  ህልምዎና ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባችን ያግዝዎታል! ባንካችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ያዘጋጀውን አደይ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመክፈት የልዩ አገልግሎቶቹና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ።

#BankofAbyssina #WomenSavingAccount #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ፎቶ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለ2 ቀናት መንግሥታዊ ጉብኝት ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸው ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በመቀጠል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትር አስጎብኝተዋል።

መረጃው የጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።…
#Update

የጨረታ መክፈቻው ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ ከሕብረተሰቡ መጣልኝ ባለው ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ አሳውቋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
በማንኛውም ቦታ ሆነው በግሎባል ሞባይል ተመዝግበው አካውንትዎን ማንቀሳቀስ፣ ክፍያ መፈፀምና ማስተዳደር ይችላሉ፡፡

ግሎባል ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ለማውረድ ሊንኩን ጠቀሙ  
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ofss.dgbb

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #GBE #SharedSuccess