ወደ ሐዋሳ እያመራ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ።
በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ ማምሻውን አስከፊ የትራፊክ አደጋ ደርሷል።
በዚህም አደጋ የ8 ሰው ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል።
አደጋው የደረሰው በዛሬው ዕለት ምሽት 12:30 ገደማ መነሻውን ከአርባምንጭ ከተማ አደርጎ ወደ ሐዋሳ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3 A 01784 " ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው።
በመኪናው ውስጡ የነበሩት የጤና ቡድን #ስፖርተኞች (ከተለያዩ ከመንግሥት ሠራተኞች እና ከባለሀብት የተወጣጡ) ሲሆኑ ከመካከላቸው የ8 ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 13 ከባድእና በ6ቱ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በዎላይታ ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ከፋንጎ ሁምቦ ቀበሌ እስከ ድምቱ እንዲሁም ከኤቱና ዳገት እስከ ቀርጨጬ ከተማ ድረስ ያለውን ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ መንገድን በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ነው ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዎላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia