TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሹመት !

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ አብርሃም አለኸኝን በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋቸዋል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
👍2
#Update

ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
2. ጀነራል አበባው ታደሰ
3. ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሌ/ጀ አለምሸት ደግፌ

የአደዋ ድል ጀግና ከፍተኛ ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ጀነራል ጌታቸው ጉዲና
2. ሌ/ጀነራል በላይ ስዩም
3. ሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ
4. ሌ/ጀነራል መሰለ መሠረት
5. ሌ/ጀነራል ሹማ አብደታ
6. ሌ/ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል
7. ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ
8. ሌ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የመዘከሪያና የመከላከያ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት የማስመረቅ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

#PMOEthiopia #FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
👎920👍86548🎉36😁33🔥19🤩18
#PMOEthiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
👎264👍19111
#NewsAlert

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት፥

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር

2. አቶ ካሊድ አብዱራህማን - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል

3. አቶ ወንድሙ ሴታ - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

4. አቶ ሄኖስ ወርቁ - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ሸመቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፦

1. ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር

2. አቶ አበራ ታደሰ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
👍2👎2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

በአሁን ሰዓት በፀጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ነው። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ መከታተል ይቻላል።

ዋና ዋና ነጥቦችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

እስካሁን ድረስ ያነሷቸው ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸው (ከፀጥታ ጉዳዮች ውጭ) በዚህ ተያይዟል : https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
👍5😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። በአሁን ሰዓት በፀጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ነው። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ መከታተል ይቻላል። ዋና ዋና ነጥቦችን ተከታትለን እናሳውቃለን። እስካሁን ድረስ ያነሷቸው ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸው (ከፀጥታ ጉዳዮች…
#ድርድር

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል።

" ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። " ብለዋል።

" ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን ነገር የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፦
- በፀጥታ ተቋማት ዝግጅት፣
- በህግ ማስከበር፣
- በ ' ተረኝነት ' ጉዳይ ፣
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳይ ፣
- ሌብነትን በተመለከተ፣
- የብሄራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሽ እና ማብራሪያዎች በዚህ ታገኛላችሁ https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14-2 (#PMOEthiopia)

@tikvahethiopia
👍6
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚኒስትሮቹ ወዴት ነው የተሸኙት ? ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦ - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ - የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ - የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፤ - የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት መሸኛታቸውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።…
#ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች በመስጠት የህ/ተ/ም/ቤት ሹመቱን እንዲያፀድቅላቸው ጠይቀዋል።

በዚህም መሰረት፦

1.  ዶክተር ዓለሙ ስሜ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር፣

2.  ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር፣

3.  ዶክተር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትር

እንዲሁም ከጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ፦

1.  አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣

2.  ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣

3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር፣

4.  አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር እና

5.  አቶ መለሰ አለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት  ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል፡፡

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
👍801👎280🤔2621😱17🙏11🕊11🥰8
#PMOEthiopia

ዛሬ ማክሰኞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ም/ቤቱ ከተወያየባቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተፈቀደ እና የተከፈለ ካፒታል በማሻሻል የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲችል በተለይ ፦

- በግንባታ ላይ ያሉ የባቡር መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ የተጠናቀቁትም ወደ ስራ እንዲገቡ፤

- በቀጣይ ለሚገነቡ የባቡር መሠረተ- ልማቶች የተሻለ አቅም እንዲኖረው የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 221 ቢሊዮን ከፍ እንዲል በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ብር 120 ቢሊዮን እንዲሆን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጿል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

(ተጨማሪ የዛሬ የምክር ቤቱን ወሳኔዎች ከላይ ያገኛሉ)

@tikvahethiopia
👎626👍34949🕊12🤔10😱10🙏8🥰4😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#DrAbiyAhmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ምን መለሱ ?

" የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡

በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡

በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፡፡

ምርታማነትን ማሻሻልም ሌላኛው ስራ ነው፡፡

በዘንድሮው ዓመት ከዓለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፡፡

ይህ ሁሉ የሚከናወነው የኑሮ ውድነቱ ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል ነው፡፡ በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ ተችሏል፡፡ "

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
😡2.29K290😭150🤔82👏45😱33🕊27🙏24😢16🥰8
#Ethiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን አድርጎ ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በማጽደቅ ለሕ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል።

ምክር ቤቱ ምን አለ  ?

- የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ነው። ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው፡፡

- የፋይናንስ ድጋፉ ፦
° የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም
° ለሥራ ፈጠራ፣
° የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣
° የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣
° የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2ዐ17 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

- ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው። ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣምም ነው።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
😡441110😭40👏30🤔12😢8🙏8😱6
#መሶብ

12 የፌዴራል ተቋማት በአንድ ቦታ የተሰባሰቡበት የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፓይለት ፕሮግራም ሥራ መጀመሩ ተነገረ።

" መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት " በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው ተብሏል።

የአሰራር ስረአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተመላክቷል።

ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር እንደሆነ ተገልጿል።

አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት 12  የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን 41 የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችን እንዳቀረቡ ይፋ ተደርጓል።

አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባና ሌሎችንም አካትተዋል።

በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ የሚገኙት 12 ተቋማት ፦

1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው።

ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ገልጿል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
551👏213🙏31🤔30😡27🕊11😭11🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #France የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አውሮፓ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ፈረንሳይ የገቡ ሲሆን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል። ውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቶች እና ትብብሮች በሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደሆነና ፍሬያማ እንደነበር ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከውይይቱ በኃላ ገልጸዋል።…
#Ethiopia #Italy

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአውሮፓ የሥራ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ።

ከቀናት በፊት በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ጣልያን፣ ሮም ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጣልያን ሮም ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒን በሮም ፓላዞ ቺጊ ጋር ውይይት እንዳካሄዱ ገልጸዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል የሁለትዮሽ ትስስር በማጠናከር ለአዲስ ኢንቬስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር እድሎችን መፍጠር ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሮም ከብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሊዮ አስራ አራተኛ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " በውይይቱ ለዓለም ሰላም ያለንን የጋራ አቋምም ተወያይተናል።  የትምህርት ተደራሽነትን የማስፋት አስፈላጊነትን በተመለከተም የጋራ ስምምነት ይዘናል " ብለዋል።

በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር ተገናኝተው እየተሳተፉባቸው ባሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ እንደተወያዩ ገልጸዋል።

" በጥቂት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እንዲሁም በኮይሻ ግድብ ፈጣን አፈፃፀም እንደታየው ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት ረገድ ከWebuild Group ጋር ያለን ትብብር ወሳኝ ነው " ብለዋል።

በውይይቱ፥ በመሠራት ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ በፍጥነት በታገዘ ውጤታማነት ላይ ፈጠራን እና ዘላቂነትን የሥራዎቻችን ማዕከል አድርገን መያዝ እንደሚገባ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
😡1.08K298👏41🤔32😢19🕊17😭16🙏12💔11🥰6😱6