TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ... በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል። በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ? አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦ " የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ…
#Update

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር " መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር " መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ውይይቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባላቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን አግኝቶ ማነጋገር #ግድ እና #ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ዘንድሮ የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአዲስ አበባ ከተማ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎች ሰልፍ እንዳያደርግ በመከልከሉ ጥያቄዎቹን ሳያቀርብ እንደቀረ ይታወሳል።

በኃላ ሊያነሳቸው የነበረውን ጥያቄዎችን በማካተት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ እሳቸውን ማነጋገር ለሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት እንደሚረዳ ገልጾ ነበር።

በወቅቱ በፃፈው ደብዳቤ በየጊዜው እያሻቀበ በመጣው የኑሮ ውድነት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ገልጾ ለዚህ ብቸኛው መፍትሄው ጠቅላይ ሚኒስትሩን  አግኝቶ ማነጋገር እንደሆነ ገልጿል።

ኢሠማኮ የሠራተኞች አንገብጋቢ የሚባሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ሊያገኝ እንዳልቻለ በዛው ደብዳቤ ተመላክቷል።

ከዚህ ቀደም የሠራተኞች ጥያቄ የቀረበላቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄውን ወደ ጎን የመግፋት አዝማሚያ እያሳዩ በመምጣታቸው፣ የኢሠማኮ አመራር " ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአነጋግሩን " ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን በወቅቱ በፃፈላቸው ደብዳቤው አስረድቶ ነበር።

#ማስታወሻ

ከዚህ ቀደም ኢሠማኮ ከሰራተኛው ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንዳያደርግ በተከለከለው ሰልፍ ሊጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች ምን ነበሩ ?

1. በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው እየተቸገረ ነው፣ በተለይ ደግሞ ደሞዝ ተከፋዩ። መንግስት መፍትሄ ይስጠን። አብዛኛው ሰራተኛ በቀን አንዴም ለመብላት እየተቸገረ ነዉ።

2. የስራ ግብር ይቀነስልን።

3. የዛሬ አራት አመት ወጥቶ የነበረው የዝቅተኛ ደሞዝ ማስተካከያ አዋጅ እስካሁን ደንብ ሳይወጣለት ቆይቷል። ይህም ትኩረት ይሰጠው፣ በ600 ብር እየኖረ ያለ ሰው አለ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ደሞዝ በአማካኝ ከ800 - 1,200 ብር ነው።

4. የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ከደምበኛቸው ከሚቀበሉት ክፍያ ለሰራተኛው 80 ፐርሰንት ከፍለዉ ቀሪውን 20 ፐርሰንት እንዲወስዱ በሚል የወጣዉ መመሪያ አለመከበር በኤጀንሲ በተቀጠሩ  ሰራተኞች ላይ ተመልካች ያጣ የጉልበት ብዝበዛ እየተካሄደ ነው፣ መንግስት ትኩረት ያርግበት የሚል ነው።

@tikvahethiopia