TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETRSS01

ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ነገ አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ ለማምጠቅ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS01

ነገ 21 ጊዜ መድፍ ስለሚተኮስ እንዳትደናገጡ!

በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችው ETRSS- 01 የተሰኘችው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሠዓት ላይ ወደ ጠፈር የምትመጥቅ ሲሆን ይህን ታሪካዊ ቀን በማስመልከት 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር በግልባጭ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል። በመሆኑም በሚተኮሰው መድፍ ድምፅ ህብረተሰቡ እንዳይደናገጥ ኮሚሽኑ ያስታውቃል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FAKE_PHOTO #ERSS01

ይሄ ዛሬ ማምሻውን 'ይህችናት ሳተላይቷ' ነገ ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት (#ERSS01) ይህቺ ናት እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። ፎቶው 2013 ላይ የተነሳ ነው። በሚግርም ሁኔታ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ሳይቀሩ ፎቶውን ሳያጣሩ ሳያረጋግጡ ሲቀባበሉት ነበር።

ማስታወሻ #ETRSS01 -- ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ነገ አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ የምታመጥቅ ይሆናል። የቲክቫህ ቤተሰቦች ከወዲሁ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS01

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ኢትየጵያ ለመጀመርያ ግዜ የምታመጥቃት #ETRSS01 ሳተላይት ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡

ከደቂቃዎች በኃላ ወደህዋ የምትመጥቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ETRSS-01፦

• የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10 ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡

• ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡

• በኢትዮጵያና ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።

• ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት ነው፡፡

• የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሰራ ሲሆን ከማምጠቅ ስራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን ይከናወናል።

• እንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና የምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግትት ተዘጋጅቷል፡፡

• ጣቢያው የሳተላይቷን ደህንነት ክትትል የሚደረግበትና ከሳተላይቷ የሚገኙ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት ነው፡፡

(A/A City Press Secretariat Office)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia