TIKVAH-ETHIOPIA
“ በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም ” - የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን አልታወቀም ስለተባሉት ወጣቶች ሁኔታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ…
" በፈንጂ እና በድማሚት ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም " - የከበሩ ማዕድናት አምራች ማህበር
ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል።
ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ፈንጂ ቢጠቀምም፤ ሙከራው እንዳልተሳካ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳደር ገልጿል።
የመከላከያ ሠራዊት መሀንዲሶች በአካባቢው ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፤ ዋሻው የሚገኝበትን ቦታ ተመልክተው " ፈንጂ እና ድማሚት " በመጠቀም የዋሻው የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካም ተብሏል።
የተንጠለጠውን ገደል ለመናድ አልተቻለም።
ይህ ሙከራ ከከሸፈ በኋላ እንዲወገድ የሚፈለገውን የዋሻ ክፍል " በታንክ የመምታት " ሀሳብ ከመሀንዲሶቹ በኩል መቅረቡን የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ገልጿል።
ያቺ ቦታ ብትመታ እና ብትናድ ሰዎቹን ቆፍሮ የማውጣት እድል እንደሚኖር ማህበሩ ገልጿል።
ይሁንና " በታንክ መምታት " የሚለው ሀሳብን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ተነግሯል።
የመከላከያ ሠራዊት አባላት መውጫ ያጡትን የማዕድን ቆፋሪዎች ለማውጣት አሁንም በአካባቢው እንደሚገኙ ተገልጿል።
በዋሻው ውስጥ መውጫ ካጡ 12 ቀናት ያስቆጠሩት የማዕድን አውጪዎች ያለ ምግብ " እስካሁን መቆየት ይችላሉ ? " ለሚለው ጥያቄ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር አሁንም ተስፋ እንዳለ አመልክቷል።
" ይኖራሉ። እስከ 15 ቀን ድረስ የመቆየት እድል አላቸው። ዋሻው ውስጥ ውሃ ስላለ፤ አፈር በሉ ምንም አሉ ዞሮ ዞሮ የመቆየት እድላቸው አለ " በማለት ግለሰቦቹ በህይወት ይገኛሉ የሚል ተስፋ እንዳለው ማህበሩ ገልጿል።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።
ፎቶ፦ የደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia

Addis Ababa University- Cisco Networking Academy,
@CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com
Online Live class - Cisco CCNA Professional Networking Course Training & Certification Preparation.
Registration Date: Feb.12 to March 8, 2024
Class start date: March 9, 2024.
Course Recognitions: CCNA trainees will receive 3 Certificate of Completion, 3 Letter of Merit, 3 Digital Badge that recognized and accepted in USA, Canada, and Europe, and you will award 58% CCNA certification exam discount voucher.
Mobile #: 0902-340070/0935-602563/ 0945-039478/
Office : 011-1-260194
Follow our telegram channel: @CiscoExams

#Amhara
በአማራ ክልል በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ በመቀነሱ መነኮሳት ለመፈናቀል መገደዳቸውንና ገዳሙ የሀይቅ ውሃ ሙላት ሥጋት ላይ በመሆኑ ተጀምሮ የነበረውን ግንባታ ማስኬድ አለመቻሉን በባሕር ዳር ጣና ሀይቅ የሚገኘው የመስቀል ክብራ አንጦንስ አንድነት ገዳም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የገዳሙ እመምኔት እማሆይ ወለተ ሥላሴ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
ምን አሉ ?
➡ መነኮሳት እየተፈናቀሉ ነው። የምንተዳደው በቱሪስት ገቢ ነበር በጸጥታው ችግር ቆሟል።
➡ በወቅታዊ ችግር ምክንያት ቱሪስት የሚባል ነገር የለም። ፍሰቱ ቁሟል። የእርሻ ቦታም የለንም። ገቢ የምናገኘው ሁሌም የቱሪስት እጅ ጠብቀን ነው።
➡ የዕደ ጥበብ ሥራዎቻችንን ሰዎች ለበረከት እያሉ ይገዙ ነበር ይሁን እንጂ ላለፉት 6 ወራት በከፋ ችግር ውስጥ ነን።
➡ ቀና ብንል ሰማይ ነው፣ ዝቅ ብንል ምድር ነው። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።
➡ በገዳሙ 40 መነኮሳት ነበሩ ፤ ነገር ግን 5 መነኮሳት በመፈናቀላቸው በገዳሙ የቀሩት 35 መነኮሳት ብቻ ናቸው። አሁንም ያሉት መነኮሳት ይሰደዳሉ የሚል ሥጋት አለኝ።
➡ አጣዳፊ ችግራችን / የሚያስፈልገን የዕለት ቀለብ / የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ ነው። ከዚህ አልፎ የዕደ ጥበብ ውጤቶቻችን ገበያ ላይ ለማዋል ቢችሉ ከድጋፍ ጠባቂነት እንወጣለን።
በሌላ በኩል ፤ ገዳሙ በጣና ውሃ ሙላት በተለይ በክረምት ወቅት ትልቅ ስጋት ስለሚጋርጥበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና በባህልና ቱሪዝም በኩል Proposal ተሰርቶ ዙሪያውን ግንባታ ተጀምሮ እንደነበር፣ ነገር ግን ግንባታ ከሚያስፈልገው 300 ሜትር የተገነባው 65 ሜትር ብቻ መሆኑን፣ በአጠቃላይ ለግንባታው ወጪ ከ12 ሚሊዮን በላይ እንደሚያስፈልግ፣ በዚህም ሁሉም ሰው ርብርብ እንዲያደርግ ተጠይቋል።
የመስቀል ክብራ አንድነት ገዳም በ1314 በፃድቁ አቡነ ዘዮሐንስ የተመሰረተና አቡኑ ለ35 ዓመታት ሲያገለግሉበት የቆዩ ገዳም መሆኑ ተነግሯል።
መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#ጉጂ
ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለአዲሱ አባገዳ የ " ባሊ " ስልጣን የማስረከብ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በአሁኑ ወቅት በርካታ ህዝብ በአዶላ ከተማ አቅራቢያ " ሜኤ ቦኮ አርዳ ጂላ " በተሰኘው ስፍራ በባህላዊ ትውፊት መሰረት የሚከናወነውን 75ኛውን የስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር ለመታደም ተሰባስቧል።
የአበገዳ ስልጣን ርክክብና ተተኪ አበገዳ የመመረጡ ሂደት እጅግ ሚስጥራዊ ከሚባሉት ክንውኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ተተኪውን አባገዳ የሚታወቀው በመጨረሻው የዕለቱ መርሐ ግብር መቋጫ ላይ ብቻ ነው። #ኢፕድ

Photo
#ኢትዮጵያ
እናት ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ ፈራሚ የሆነችበትን የሳሞአ ስምምነት አሁን ባለበት ሁኔታ እንዳያፀድቅ ጥሪ አቀረቡ።
" ግብረሰዶም ከባህላዊና ሃይማኖታዊ እይታ ባሻገር በኢትዮጵያ የወንጀል ህግም በወንጀልነት የተቀመጠ ነዉ " ያሉት ፓርቲዎች ከዚህ አኳያ ግብረሰዶምን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያበረታታ ፣ የሚደግፍ ማንኛዉም ተግባር ወይንም ስምምነት ከአገራችን ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖት በተቃራኒ ከመሆኑም ባሻገር የወንጀል ተግባርን ማበረታታትና መደገፍም ጭምር ነዉ ብለዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ራሳቸውን ቋሚ ተመጽዋች እና እርዳታ ለማኝ ላደረጉ አገራት የሳሞአ አይነት ድብቅ ተልዕኮ ያላቸው ስምምነቶችን መቃወም ማለት ምን ማለትና የሚያስከትለዉም መዘዝ የት ሊደርስ እንደሚቻል እንረዳለን ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም ሆኖ እንደ ሕዝብ ባህላችን፣ እሴታችንና ወጋችንን ጠብቀን በምንከተላቸዉም እምነቶች ከፈጣሪ ትእዛዝ በተቃራኒዉ ባለመቆም ሊከተል የሚችለዉን መዘዝ መጋፈጥ እንደ አገር የምንፈተንበት ትልቅ ፈተና ነው ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ፤ " ይህ ፈተና ዛሬ በዚህ መልክ አገራችንን የገጠማት ቢሆንም አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ የላቀ ብዙ ፈተናዎችን በድል አልፋና እዚህ የደረሰች በመሆኗ ዛሬም ሸብረክ ልትል እንደማይገባ አጽንኦት ሰጥተን ልናሳስብ እንወዳለን " ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዉስጡ ትዉልድ አምካኝና አገርና ማንነትን አጥፊ የሆነ ይዘት ያለውን ስምምነት ከተቻለ በዚህ ረገድ የሚነሱ አንቀጾች እንዲወገዱ ወይንም እንዲታረሙ ይህን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስምምነቱን እንዳያጸድቅ አሳስበዋል።
(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#GetachewKassa
በይበልጥ " ሀገሬን አትንኳት " ፣ " ውብ አዲስ አበባ " ፣ " የከረመ ፍቅር " በተሰኙት ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ስራዎች የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምፃዊ ጌታቸው ባደረበት ህመም የካቲት 12 ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሀገሬን አትንኳት ...
" የብዙሃን እናት መጠጊያ የምንላት
እማማ ናትና ሀገሬን አትንኳት።
በዓድዋ በማይጨው ጀግኖች የሞቱላት
ህፃን ሽማግሌ የተሰየፈላት
ደመ መራራና ቁጡነት ያለባት
ጎጆዬ ናትና #ኢትዮጵያን ❤ አትንኳት !
ዘርዓይ ደረስ ወንዱ በሮሞ የቆመላት
ጀግኖች በጦር ሜዳ ወጥተው የቀሩላት
እኔም በተጠንቀቅ አለሁሽ የምላት
ጥቁሯን አፍሪካዬን ኢትዮጵያን አትንኳት። "
NB. አንፋጋው ድምፃዊ ጌታቸው የተጫወተው ' ሀገሬን አትንኳት ' የተሰኘው ዘመን አይሽሬ ስራ በአንጋፋው ደራሲና ገጣሚ ጋሽ አበራ ለማ የተፃፈ ነው።

#ጉጂ ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለአዲሱ አባገዳ የ " ባሊ " ስልጣን የማስረከብ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። በአሁኑ ወቅት በርካታ ህዝብ በአዶላ ከተማ አቅራቢያ " ሜኤ ቦኮ አርዳ ጂላ " በተሰኘው ስፍራ በባህላዊ ትውፊት መሰረት የሚከናወነውን 75ኛውን የስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር ለመታደም ተሰባስቧል። የአበገዳ ስልጣን ርክክብና ተተኪ አበገዳ…
#Update
አባገዳ ጃርሶ ዱጎ 75ኛው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ በመሆን ስልጣን (ባሊ) ተረከቡ።
ዛሬ በተካሔደው 75ኛው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ ስልጣን ርክክብ መርሀ ግብር አባገዳ ጂሎ ማንዶ ስልጣናቸውን (ባሊ) ለአባገዳ ጃርሶ ዱጎ አስረክበዋል፡፡
በየስምንት አመቱ በሚካሄደው የስልጣን (ባሊ) ርክክብ መርሀ ግብር መሰረት ከገዳ ሀርሙፋ ወደ ገዳ ሮበሌ ሽግግር መደረጉን ኦቢኤን ዘግቧል።

በቅርብ ቀን https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk አሳታፊ በሆኑ አዝናኝ የሽልማት ዝግጅቶች ይጠብቁን፡፡
የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE

እንኳን ደስ አላችሁ!
የተረክ በM-PESA 4ተኛ ዙር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተረክበዋል!
የአዲስ አበባ ልጆች መኪና እና ባጃጁን እጃቸው አስገብተዋል፤
የድሬ ፣የጅግጅጋ እና የካራሚሌዎቹም ሽልማታቸውን ተረክ አድርገዋል!
ሳንሸልማችሁማ አንላቀቃትም!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ @SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA