TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬዞን " ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት #መንታ ልጆቿን አጥታለች " - ነዋሪዎች " እኛ አካባቢ ትንንሽ ነገሮችን አጋኖ እና ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ " - አቶ ታደለ አሸናፊ በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች የታሰሩ ባለስልጣናት ጭምር ከእስር አለመፈታታቸው እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ክፍተት…
“ አዲሱን ሹፌር ሊገድሉት ሲያሳድዱት ሴቶች ቀሚስ አልብሰው ነው የሸኙት ሌሊት ” - የኮሬ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን “ በተደጋጋሚ እየፈጸመ ያለውን መዋቀር ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በቡኒቲ ክላስተር የወላድ እናቶች ስቃይ ዛሬም ቀጥሏል ” ሲሉ አንድ ነዋሪና የመንግስት ሠራተኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የጉዳዩን አሳሳቢነት አስመልክተው ሰሞኑን ስለተመለከቱት ጉዳይ ሲገልጹም፣ “ ከአልፋጮ ቀበሌ ወ/ሮ ነፃነት ቦጋለ የተባሉ ወላድ እናት ምጥ ተይዘው በአንቡላስ እጦት ምክንያት ወደ ሆስፒታል መድረስ አልቻሉም፡፡ ከብዙ እንግልት በኋላ ወደ ሰገን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል (ጉማይዴ) ቢደርሱም አልተሳካላትም ” ብለዋል።
“ የሆስፒታሉ ጤና ባለሙዎች የእናት እና የጨቅላውን ሕይወት ለማትረፍ ርብርብ ቢደረግም ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ በህዝብ ማመላለሻ መኪና 4,000 ብር ከፍለው ወደ ካራት ሆስፒታል ተልከዋል ” ብለው፣ እናትየዋ በሰላም ቢገላገሉም በአንቡላንስ እጥረት ከፍተኛ እንግልትና ከእጥፍ በላይ ለሆነ የትራንስፖርት ወጪ መዳረጋቸውን አስረድተዋል።
“በቅርቡ ከአልፋጮ ቀበሌ አንዲት እናት አምቡላንስ ባለመኖሩ መንታ ልጆቿን ማጣቷ የሚታወስ ነው” ያሉት መረጃ አቀባዩ፣ “እናቶችን እና ጨቅላ ሕፃናትን ከሞት ለመታደግ መንግስት ፖሊሲ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ትኩረት በመነፈጉ የእናቶች ስቃይ እየተባባሰ ቀጥሏል” ነው ያሉት።
አክለውም፣ “የኮሬ ዞን የመንግሥት አካላትም ከማሾፍ እና ከማፌዝ በተጨማሪ አምቡላንሶችን የካድሬ ማመላለሻ በማድረግ በሰው ልጅ ህይወት መቀለዳቸውን ተያይዘዋል” ሲሉ ተችተዋል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ ምን ምላሽ ሰጠ ?
ጉዳዩን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ ስሜ ባይጠቀስ ያሉ የኮሬ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ባለሥልጣን ፥ ለአካባቢው ነዋሪዎች አምቡላንስ ተሰጥቷቸው እንደነበርና የአጠቃቀም ችግር እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ “አምቡላንሱን ቀምተውናል። የቀሙን ደግሞ ‘ለምን የክላስተር ጥያቄ አነሳችሁ’ ብለው ነው” ሲሉ ላቀረቡት ወቀሳም፣ “የአንቡላንስ መወሰድ ሌላ፣ የመዋቅር ጥያቄ ሌላ። አይገናኝም” ብለዋል ባለሥልጣኑ።
“3 ቀበሌዎች ትንሽ ከዋና ከተማው ይርቃሉ፣ ለማዘዝም አይመችም በሚል። ተወዳድሮ አንድ ልጅ (የአምቡላንስ ሹፌር) ሲያልፍ፣ ‘አይደለም ማለፍ ያለበት የእኛ ልጅ ነው’ ብለው ፈርመው አመጡ። በ3ኛው ወር ላይ 5 ክላሽ (ሕገወጥ መሣሪያ) በአምቡላንስ ላይ ጭኖ ኮንሶ ላይ ተያዘ። ልጁ በዚሁ ምክንያት ከሥራ ተባረረ” ብለዋል።
አምቡላንሱን ኮንሶ ዞን አልመልስም ቢልም ተከራክረው እንዳስመለሱ፣ አምቡላንሱ ከተመለሰ በኋላም ሌላ ሹፌር ቀጥረው አምቡላንሱን ወደ ቡኒት ክላስተር እንደላኩ፣ይሁን እንጂ ከላኩ በኋላም፣ ወጣቶቹ “አዲሱን ሹፌር ሊገድሉት ሲያሳድዱት ሴቶች ቀሚስ አልብሰው ነው የሸኙት ሌሊት” ሲሉ ከሰዋል።
“ሹፌሩ ቀሚስ ለብሶ ከወጣ በኋላ ቁልፉን ወሰዱና ባለ 5 ክላሽ ጭኖ ለተገኘው ሹፌር ሰጡ። ይሄ ነው ያለው ችግር እንጂ እነርሱን አምቡላንስ የከለከለ የለም” ብለው፣ 2 አምቡላንሶች እንደተመደቡላቸው፣ እዚያ ለማሳደር ዋስትና እንደሌላቸው አስረድተዋል።
ችግሩ እንዲቀረፍ ለምን አታወያዩአቸውም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም፣ ሰሞኑንም ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ክልሉ ጤና እና ጸጥታ ቢሮ የተደረገው ሙከራ ባለሥልጣናቱ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን አልተሳካም።
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

#Update " ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት…
" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራ አቋሙን ያሳወቀን” ብሏል።
ተማሪዎቹን ወክሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጠ ሌለኛው ተማሪ ፤ “ እኛ የ2016 ዓ/ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደብን Freshman እና Remedial ተማሪዎች ነን። ነገር ግን አስካሁን ከሌሎች የአማራ ክልል በተለዬ የእኛ ካምፓስ ለተማሪዎቹ ጥሪ አላደረገም ” ሲሉ አማሯል።
ዩኒቨርሲቲው ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጥሪ አድርጎላቸው እንደነበር ያስታወሰው የሁሉንም ተማሪዎች ቅሬታ አቅራቢው፣ “ ባልታወቀ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ከተነገረን ወር ሊሞላን ነው ” ብሏል።
በመሆኑም፣ መጥራት የሚችሉ ከሆነ ጥሪ እንዲያደርጉ፣ መጥራት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ተማሪዎቹ በመጠበቅ ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ እንዲያሳውቁ፣ እንዲሁም በቅርቡ መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ እንዳደረገው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸው ጠይቋል።
“ ከእነዚህ አማራጮች ውጪ ግን ‘ተማሪዎች ጠብቁ’ የሚል መልስ መስጠት እንደማይቻል ይታወቅልን። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ትዕግስት ሊኖረን ስለሚይችል። በዕድሜያችንና በሞራላችን እየተቀለደ ነው ያለው ” ሲልም የተማሪዎቹ ተወካይ አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል በሰጡት ቃል፣ “ ዩኒቨርስቲው አሁን አልጠራም ማለትም አይችልም (ምክንያቱም አልጠራም ቢል ከትምህርት ሚኒስቴር ግዳጅ አለበት)። ጠርቶ እንዳያስገባ ደግሞ አካባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች እያደረጉ ያሉትን ነገር በዓይናችን እያዬን ነው ” ሲሉ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ይታገሱ እንዲላቸው ሳይሆን ቁርጡን እንዲያሳውቃቸው ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ዩኒቨርሲቲው የማይጠራበት ምክንያት፣ አሁን አካባቢው ላይ ያለው ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው። በጸጥታ ችግር ከጤና እና ከአግሪካልቸር ግቢዎች ለቀው ወደ ፔዳና ፖሊ ካምፓሶች የተደረቡ ተማሪዎች Still ትምህርት አልጀመሩም። አሁን አዲስ ተማሪዎችን ቢጠራ የት ላይ ነው የሚያደርጋቸው? ” ሲሉም ጠይቀዋል።
“ ማስተባበሪያ ክላስ ራሱ ጠቦን እየተቸገርን ነው። የዶርም እጥረት አለ። ተማሪዎቹ ወደዬ ግቢያቸው እስካልተመለሱ ድረስ” ያሉት እኚሁ አካል ፣ “አሁንም ፔዳ (Main campus) ያለው ሁኔታ አስጊ ነው። ‘እስከ ነገ ሐሙስ ‘ለቃችሁ ውጡ’ የሚል ወሬ ስለመጣ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ተማሪዎችን መጥራት አይችልም። የመጡት እየተሰቃዩ ነው። እነዚህም መጥተው ከሚሰቃዩ ቢረጋጉ ነው የሚሻላቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን…
#BDU
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ እስካሁን ጥሪ ባልተደረገላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ተጨማሪ ምላሽ አግኝቷል።
በዚህም ተቋሙ ፤ " ተማሪዎቹን ለመጥራት አስቻይ ሁኔታዎች እየተጠበቀ ነው። " ብሏል።
" አሁን ያለው ሁኔታ ተማሪዎቹን ለመጥራት እየተገመገመ ነው። ተማሪዎቹ በትዕግስት ይጠብቁ። " ሲል አሳውቋል።
ተጨማሪ ዝርዝር የምናጋራችሉ ይሆናል።
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት። 70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ…
#Update
" ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ብሎ ተሸንፏል " የተባለው ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበል ለ70 የጤና ባለሙያዎች በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል #ተገዶ ከፈለ።
በገባው ቃል መሠረት የኮቪድ ወቅት ልዩ አበል ባለመክፈሉ ከ60 በላይ በሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክስ ተመስርቶበት፣ " ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ቢልም ተሸንፏል " ፣ " የፍርድ ቤት ውሳኔንም በተደጋጋሚ ሲጥስ ነበር " የተባለው ጤና ሚኒስቴር በመጨረሻ ገንዘቡን ለከሳሾቹ በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል ተገዶ መከፈሉን የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የጤና ባለሙያዎቹን ወክለው ጉዳዩን በጥልቀት ሲከታተሉት የነበሩ ተወካይ የፍርድ ቤት ሂደቱና ጤና ሚኒስቴር ስንት ጊዜ ይግባኝ እንደጠየቀ ሲያስረዱ፣ " ከዋናው መዝገብ እስከ አፈፃፀሙ ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ብለው አሸንፈናል። ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው አስገድዶ የተቆረጠበት " ብለዋል።
ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበል ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል በመቁረጥ እንዲፍላቸው ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የጤና ባለሙያዎችን ብዛትና የልዩ አበሉን መጠን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪም፣ " 70 ናቸው። አጠቃላይ የገንዘብ መጠን በግልፅ አልተቀመጠም ነበር። በግምት ግን ከነታክሱ ከ33 ሚሊዮን በላይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤት ልዩ አበሉን እንዲከፍል ለመስሪያ ቤቱ ውሳኔ ቢያሳልፍም በተደጋጋሚ ፈቃደኛ ሳይሆን የክሱ ሂደት ብዙ ጊዜ በመውሰዱ የኮቪድ ልዩ አበሉ መጠን አልጨመረም ወይ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ፣ " ወለድና ሌላ ነገር ሳይሆን የዋናው መዝገብ ክርክር የክስ ሂደቱ ጊዜ ስለረዘመ ጨምሯል " ነው ያሉት።
ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበሉን በመጨረሻ በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል ተገዶ ከሳሿቹ ፍትህ ያገኙት ከሁለት ዓመታት ተኩል በላይ እንደሆነ የገለጹት ታማኝ ምንጭ፣ " ገንዘባችን እንዲከፈል ከማድረጉ ባሻገር ምንም አይነት ካሳም ወይም ቅጣት አልከፈለም " ብለዋል።
ሌላኛው ሁነቱን ሲከታተሉ የነበሩ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው፣ የፍትህ ስርዓቱ ተጽዕኖ ቢበዛበትም የጤና ባለሙያዎቹ ታግሰውና እውነትን ብቻ ይዘው ችሎቱን ተደጋጋሚ እንዳሸነፉ፣ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው ተቋም (ጤና ሚኒስቴር) የፍርድ ውሳኔውን ለመፈጸም ፌቃደኛ ባለመሆን ተደጋጋሚ ይግባይኝ እንደጠየቀ ገልጸው፣ " የመጨረሻ የፍርድ ቤት ውሳኔዉ ተፈጻሚ ሆኗል " ብለዋል።
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ ፦
- የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን 1,050 ብር፣
- ለየመጀመሪያ ድግሪ ባለሙያዎች 900 ብር የኮቪድ ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ቢወሰንም፣ ተቋሙ የሰሩበትን የተወሰኑ ወራት አበል ከፍሎ ሙሉውን ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ክስ እንደመሰረቱ፣ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት ልዩ አበሉን እንዲከፍል ቢወስንም ጤና ሚኒስቴር ውሳኔውን እየጣሰ መቆየቱን መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

አጋፋሪ - ምዕራፍ 2 በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466
በጉማ የፊልም ሽልማት ፕሮግራም ላይ በምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ ዋና የወንድ ተዋናይ በመሆን አለማየሁ ታደሰ ያሽነፈበት በይዘቱ ለየት ያለ ተከታታይ ድራማ … አጋፋሪ ሁለተኛው ምዕራፍ … በዲኤስቲቪ!
አጋፋሪ ምዕራፍ አንድን በETV መዝናኛ ተከታትላችሁ ተደሰታችሁ አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ምዕራፍ በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466 በ290 ብር ብቻ እየተከታተሉ ዘና ይበሉ!
ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466
ዲኤስቲቪ-ሁሉም ያለው እኛ ጋር ነው!
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #አቦልቲቪ #DStvSelfService #Agafari #StepUp

#Amhara
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ አይሱዚ በተባለው የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ሰኞ ዕለት ተፈፅሟል በተባለ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜን አትጥቀሱብኝ ያሉ በርካታ ሟቾች ዘመዶቼ ናቸው ያሉ ነዋሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፤ በጭነት ተሽከርካሪ ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ቤተክርስቲያንን ልጅ ክርስትና አስነስተው ወደ መኖሪያ ቤት እየተመለሱ የነበሩ ናቸው ብለዋል።
እኚሁ ነዋሪ ምን አሉ ?
- ጥቃቱ ከደረሰባቸው ውስጥ የኔ ዘመዶች ይገኙበታል። ሳሲት ከተማ ክርስትና ላይ ውለው ሲመለሱ ነበር።
- ከሰላ ድንጋይ ወደ ሳሲት ጦርነት እየቀረበ ሲመጣ ሙሉ ቤተሰብ የነበራቸውን የራሳቸውን ተሽከርካሪ ተጠቅመው ወደ ትውልድ ቄያቸው ሲጓዙ ነው ጥቃት የተፈፀመው።
- ከ40 በላይ ሰዎች ነበሩ ነው የተባለው ፤ መኪናው በአካባቢው የነበረውን ጦርነት በመሸሽ ላይ የነበሩ ሰዎችንም ጭምር እያሳፈረ ነው የሄደው።
- የእኔ ቤተሰቦች፦ የአክስቴ ልጆች እህትና ወንድም የነበሩ፣ በወንድምየው ወገን 7 ልጆች ነበሩ አንድ ላይ (እስከነ ሚስቱ) አቶ ምሳው ይባላል፣ እህቱ ሸዋለፋ ትባላለች እሷ እስከነልጇ ነበረች አጠቃላይ 6 ቤተሰብ ነው ያለቀው። በሌላ በኩል፤ የአባቴ ወገን፣ ዘመዶች፣ አክስቶቼ ነበሩ ፤ ቄስ ንጉሴ እስከነባለቤታቸው አጠቃላይ 8 ቤተሰብ፣ ክርስትና አንሺ የነበረው የባልየው ወንድም ዘየደ እስከነ ሹፌሩ፣ ጎረቤታቸው አቶ ማመዬ አጠቃላይ የአጎቴና የአክስቶቼ ልጆች የስጋ ዘመዶቼ አልቀዋል።
- በጥቃቱ አስከፊነት ምክንያት ማንነታቸው ሳይለዩ የተቀበሩ አሉ። ወደ ጤና ተቋማት ሄደው የሞቱም አሉ።
- ጥቃቱ በይበልጥ በግራ በኩል ነው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው።
- ክርስትና የተነሳው ህፃን በአያቱ እቅፍ ውስጥ የነበረ ሲሆን ከአያቱ ጋር በህይወት መትረፍ ችሏል። ወላጆቹ ግን ህይወታቸው አልፈዋል።
- ቦታው ከጦርነት ቀጠና 15 ኪ/ሜ ይርቃል። ማንም እዛ ጥቃት ይፈፀማል ብሎ አልገመተም።
- ጥቃቱ ማህበረሰቡን ያስደነገጠ ነው። ከዚህ ቀደም በአካባቢው እንደዚህ አይነት ነገር ስላልነበር።
- ስትጓዙ ተጠንቀቁ። አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ላይ አትጓዙ። ትራንስፖርት መጠቀም ከባድ ሆኗል።
- መንግሥት ህዝብን ለማስተዳደር እስከተመረጠ ድረስ የመረጠው ህዝብ ላይ እንዲህ ያለው ጥቃት ማድረስ የማይጠበቅ ነው። ተዋጊና ተዋጊ ምንም አይነት ጉዳት ቢደርስ ሁለቱም አስቦበት ነው። ሰላማዊ ሰዎች ላይ እንዲህ ያለው ጥቃት ሲደርስ መንግሥት ኃላፊነቱን ቢወስድ።
- መንግሥት ጉዳዩን በቅርበት አይቶ የተፈፀመውን ጥቃት ቢመረምርልን የሚል መልዕክት አለኝ።
ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በመከላከያ እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል " ሰላድንጋይ " ላይ ግጭት እንደነበር አሁን ላይ ግን እንደሌለ መከላከያም በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስፍራው ገብቶ አካባቢውን እንደተቆጠር ተነግሯል።
ይህን የሰሜን ሸዋ ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን በመንግሥት በኩል የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። መገናኛ ብዙሃን ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ አሳውቀዋል።
ነገር ግን ከወራት በፊት መንግሥት ፦
- ድሮን የታጠቀው አለኝ ለማለት ሳይሆን ልክ እንደሌለው ማሳሪያ ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሆነ ፣
- የፀጥታ ኃይሉ ድሮ በንፁሃን ላይ እንደማይጠቀም ፤
- ድሮ ጥቅም ላይ የሚውለው ለስብስብ ኢላማ እንደሆነ በዚህም ከመንግሥት ጋር የገጠመው የታጣቂው ስብስብ ዒላማ ሲገኝ እንደሚመታ
- ህዝብ ላይ ድሮን እንደማይጣል ፣ መንደር ላይ እንደማይተኮስ ፣
- የታጣቂ ኃይሎች ምርጥ ኢላማ ሲገኝ እንደሚተኮስ
- ድሮን ጥቅም ላይ ሲውል ለህዝብ ጥንቃቄ እንደሚደረግ አሳውቆ ነበር።

#Amhara በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ አይሱዚ በተባለው የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ሰኞ ዕለት ተፈፅሟል በተባለ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል። ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜን አትጥቀሱብኝ ያሉ በርካታ ሟቾች ዘመዶቼ ናቸው ያሉ ነዋሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፤ በጭነት ተሽከርካሪ ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ቤተክርስቲያንን ልጅ ክርስትና አስነስተው ወደ መኖሪያ ቤት…
"መረጃዎችን እያሰባሰብን ነው " - ኢሰመኮ
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ ተፈጸመ የተባለውን ግድያ በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያጣራው ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ " ገና አዲስ ስለሆነ እዚህ ላይ አስተያዬት መስጠት ያስቸግራል። እንደሚታወቀው የእኛ ምርመራ ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ መረጃው እንደደረሳቸው ሲያስረዱም " አይተነዋል፣ ሚዲያ ላይ Circulate ሲያደርግ ስለነበረ " ነው ያሉት።
ምርመራ ጀምራችኋል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ምክትል ኮሚሽነሯ፣ " መረጃዎችን እያሰባሰብን ነው። ቦታው ላይ ግን ገና መድረስ አልቻልንም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢሰመኮም ይሁን በመንግሥት በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትሎ ያሳውቃል።

" 4 አባቶች ተገድለዋል " - ቤተክርስቲያኗ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም " እራሱን ' ኦነግ ሸኔ ' ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ 4 አባቶችን ገድሏል " ሲል አሳወቀ።
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ 3 አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ ፦
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ገልጸዋል።
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሙ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያዎች በቡድኑ በመወረሳቸው ምክንያት ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያኑ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህ መረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያና የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው።

" 4 አባቶች ተገድለዋል " - ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም " እራሱን ' ኦነግ ሸኔ ' ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ 4 አባቶችን ገድሏል " ሲል አሳወቀ። ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ 3 አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ…
" የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ እናሳስባለን " - ቤተክርስቲያኗ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጥንታዊው እና ታሪካዊት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም መሆኑን ገልጻለች።
በተለያዩ ጊዜያትም በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑንም አስታውሳለች።
አሁን ደግሞ 4 አባቶች በታጣቂ ቡድኖች ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ መሆኑን አመልክታለች።
አንድ አባት ደግሞ ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ይፋ አድርጋለች።
በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ ቤተክርስቲያኗ አሳስባለች።

የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት አሳወቀ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ ም/ቤት አባል የነበሩት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
አቶ ዮሐንስ ከወራት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
የቀድሞው የአማራ ክልል ባለልስጣን ለረጅም ጊዜ በተለያየ የስልጣን እርከን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በኃላ ላይ ከመንግሥት ጋር መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር።
ከወራት በፊትም በአማራ ክልል ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ለእስር መዳረጋቸው መነገሩ ይታወሳል።

#Infinix_Hot40
ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ አዲሱ (Hot 40 pro) የተሰኘ ሞዴሉን በአትሞስፌር በደማቅ ሁኔታ አስተዋወቀ!
ይህ ሞዴል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ይዞ ብቅ ያለ ሲሆን 108 ሜጋ ፒክስል ኤ.አይ ካሜራ ከ32ሜጋ ፒክስል የፊት ካሜራ በማካተተ ቀርቧል። 256ጂቢ ሚሞሪ ከ16 ጂቢ ኤክስቴንድድ ራም ጋር ያጣመረው ይህ ስልክ የፈለጉትን ጌም በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት መጫወት እንዲችሉ ያስችሎታል ።
#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries