TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የRSF መሪ የሆኑት ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር አዛዥ የሆኑትን አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንን " ወንጀለኛ " ናቸው ብለዋቸዋል። የመሩትን ጦርም በመፈንቅለ መንግስት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። ሄሜቲ ወታደሮቻቸው ወደ ግጭት ተገደው መግባታቸውን አመልክተዋል። የሱዳን ጦር አዛዥ ሀገሪቱን እንዳወደመ የገለፁት ዳጋሎ ጦራቸውን እያሸነፈ መሆኑንና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍኑ ፤ ያለው ሁኔታም በቅርቡ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ ደራሽ) በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ " የተማረኩ " ናቸው ያላቸውን #የግብፅ_ወታደሮችን የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል።
የግብፅ ወታደሮች በ " ሜሮዌ " ስለነበሩበት ሁኔታ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ባይኖርም የግብፅ እና የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ዉጥረት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አልፎ አልፎ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያካሂዱ ቆይተዋል ተብሏል።
RSF ያጋራው አጭር ቪዲዮ በርካታ ድካም የተጫጫናቸው የግብፅ ሰራዊት አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች መሬት ላይ ቁጭ ብለው የRSF ዩኒፎርም የለበሱ አባላት በግብፅ አረብኛ ዘዬ ወታደሮቹን ሲያናግሩ ያሳያል።
ሮይተርስ ቪድዮውን ወዲያውኑ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል። የግብፅ ባለስልጣናትም በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ወዲያውኑ አልሰጡም።
@tikvahethiopia