TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የትምህርት_ፍኖተ_ካርታ ሰነድ⬆️

አንድ የቻናላች ወዳጅ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መምህር #ዳንኤል_መኮንን በትምህርት ፎኖተ ካርታው ላይ ያወጣውን መረጃ ተመልከተው በሚል ልኮልኛል። እኔም መምህሩን በቻናሉ ስም በማመስገን መረጃውን እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ።

የትምህርት ፍኖተ ካርታ በጥቂቱ⬇️

◾️የዩኒቨርስቲ ቆይታ #ሶስት አመት የነበረው ወደ 4 አመት ከፍ ያለ ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች በመጀመሪያ አመት ተማሪ ሲሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ሳይንስ ኮርሶች ማለትም እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሶሎጂ፣ስነ ምግባር የመሳሰሉ ኮርሶችን በመውሰድ ማህበረሰባቸውን እንዲያውቁ ይደረጋል። የመጨረሻ አመት ተማሪ ሲሆኑም ከ4 ወር እስከ 8 ወር ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ አገልግሎት ይሰጣሉ (ኢንተርንሺፕ)።

◾️የመምህራን ጥቅማ ጥቅም በተገቢው መልኩ ይከበራል።

◾️አጠቃላይ ፈተና በ6ኛ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ይሰጣል።

◾️ፍኖተ ካርታው ለ12 አመት ያገለግላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢቦላ⬆️

በኮንጎ #የኢቦላ በሽታ እንደገና በማገረሸቱ የተነሳ ወላጆች በፍርሃት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት #እያስቀሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በኢቦላ ቫይረስ በሽታ ምክንያት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #የትምህርት ተሳትፎ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ወረርሽኙ በነሐሴ ወር ከተከሰተ ወዲህ በኢቦላ #የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል፡፡

ይሄን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረትም በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው መላክ መጀመሩን አልጀዝራ በዘገባው አመልክቷል።

@tsegawolde @tikvahethiopia
Forwarded from Tikvah-University
#የትምህርት_ምዘናና_ፈተናዎች_አገልግሎት_ሹመት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሹሞለታል።

እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ከሰኔ 02/2014 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ሰኔ 08/2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን ተከትሎ ተቋሙ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ሲመራ ቆይቷል።

የቀድሞ መጠሪያው ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የነበረው አገልግሎቱ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠረቅና ውጤት ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሱበት መቆየቱ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
#የትምህርት_እድል

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል።

የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 78 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ09/12/14 - 13/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• የመመዝገቢያ ብር 400
• አንድ ክላሰር ይዛችሁ ተገኙ

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ተብሏል።

ት/ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች በማፍራት በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎችም እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈራ ት/ቤት ነው።

ለአብነት በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና 78 ተማሪዎችን አስፈትኖ 42 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት የመጣውም 659 ከዚሁ ሲሆን በት/ቤቱ ዝቅተኛ ውጤት የነበረው 529 ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ። በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል። በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው #የትምህርት_ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia