TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #ኦዲት

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት እያቀረበ ይገኛል።

በዚህም ወቅት ተከታዩን ሰምተናል ፦

በ2014 የበጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች በተከናወነው የኦዲት ሪፖርት መሰረት እርምጃ የተወሰደ እንደሆነ ማጣራት ተደርጎ ነበር።

በ92 መስሪያ ቤቶች ተመላሽ እንዲደረግ ተብሎ አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊዮን ብር እና በዶላር 23,230 ከ43 ውስጥ ተመላሽ የተደረገው 48.2 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ ታውቋል፤ ይህም ተመላሽ ሊደረግ ከሚገባው ጋር ሲነጻጸር 11 በመቶ ብቻ ነው።

ቀሪው 394.8 ሚሊዮን እና 23,230 ከ43 ተገቢው እርምጃ ያልተወሰደበት እና ተመላሽ አልተደረገም።

በተጨማሪ በ2014 #የተሟላ_የማስረጃ_ሰነድ ካልቀረበበት 5 ቢሊዮን 61 ሚሊዮን ማስረጃ የቀረበበት 508. 1 ሚሊዮን ብቻ ሲሆን በመቶኛ 10% ብቻ ማስረጃው ቀርቦ ትክክለኝነቱ ተረጋግጧል።

የተመለሰው ትንሽ ቢሆንም አሰተያየት ተቀብለው ተመላሽ ካደረጉት ተቋማት ውስጥ ፦
የኢንፎርሜሽን ደህንነት መረብ አስተዳደር 5.9 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 5.8 መልሷል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4.1 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 3.5 ሚሊዮን መልሷል።
የስፔስ እና ጂኦስፔሻል ስልጠና ኢንስቲትዩት ተመላሽ እንዲያደርግ ከተባለው 5.6 ሚሊዮን ውስጥ 4.4 ሚሊዮን መልሷል።

የሰነድ ማስረጃ አቅርቡ ከተባሉት ውስጥ ፦
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 124.25 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 150.2 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከ3.9 ሚሊዮን 2.2 ሚሊዮን መልሷል።

ሰነዶቹም ትክክለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia