TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል። ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር። በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን…
#CBE

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ #የራሳቸውን_ያልሆነውን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ (በከፊል የመለሱ) 5166 ግለሰቦች የሚቀረውን ብር እንዲመልሱ የሰጠው የመጨረሻ ቀነ ገደብ ዛሬ ቅዳሜ 11:00 ላይ ያበቃል።

ባንኩ ፤ ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦
- ሙሉ ስማቸው
- ፎቷቸው
- በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት እንዲሁም ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አሳስቦ ነበር።

ባንኩ ከቀናት በፊት ፤ ገንዘብ ወስደው ጭራሽ ያልመለሱ 565 ደንበኞቹንና በከፊል መልሰው የሚቀር ገንዘብ ያልመለሱ 5166 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይወሳል።

በሌላ በኩል ፤ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሰዱትን እና ወደ ግል ባንኮች ያዘዋወሩትን ገንዘብ በዲጂታል መንገድ ወደ ንግድ ባንክ ቢመልሱም ገንዘብ ካልመለሱት ጋር ስማቸው መውጣቱን በመግለፅ ንግድ ባንክ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ንግድ ባንክ ዓርብ በመጋቢት 6 / 2016 ለሊት በ25,761 ደንበኞች ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ እንደተወሰደበት ከዛ ውስጥ 622 ሚሊዮን ያህሉን ማስመለሱን ከ4 ቀን በፊት መግለጹ ይወቃል።

@tikvahethiopia