TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት⬇️

ጥቂት የሠራዊት አባላት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሊያነጋግሩን ይገባል በሚል ወደ ቤተ መንግስት የሄዱበት መንገድ ለሠራዊቱ የተሰጡ ክልከላዎችን የተላለፈ መሆኑ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ፣ የምዕራብ ዕዝ፣ የሰሜን ዕዝ፣ የደቡብ ምስራቅ ዕዝ እና የማዕከል ግብረሀይል ጠቅላይ መምሪያዎች ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ለኢቲቪ ዜና ልከዋል፡፡

በመግለጫቸው እንዳሉትም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአገራችን ህዝባች በልማትና በዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት በሚያደርጉት ርብርብ ውስጥ የህዝባችን ሰላም የሚያውክና የአገራችንን ሉዓላዊነት የሚደፍር አደጋ ሲያጋጥም በፈፀምነው ጅግንነት እና ህዝባዊነት መንግስትና
ህዝብ የሰጡንን የአገርና የህዝብ ደህንነት የመጠበቅ ግዳጃችንን በአግባቡ ስንወጣ ቆይተናል፡፡

የአገራችንና የህዝባችንን ክብር በጐረቤት አገሮች በአህጉር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንዲል ያደረገና የተደነቀ፣ አካባቢያዊና አለምአቀፉዊ ግዳጃችንን በብቃት መወጣት ችለናል፡፡

ሠራዊታችንን ህገ መንግስቱን በማክበርና በማስከበር በህግ የበላይነት ማመንና በህግ ማዕቀፍ ብቻ መስራት፣ የሲቪል ባለስልጣናትን ማክበር፣ህዝብን ማስከበር እና በአጠቃላይ ኘሮፎሽናሊዝም፣ ህዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ውጤታማነት የሠራዊታችን ልዩ መገለጫዎች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

በመሆኑም ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጥቂት የሠራዊት አባላት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሊያነጋግሩን ይገባል በሚል ወደ ቤተ መንግስት የሄዱበት መንገድ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት ለሠራዊቱ የተሰጡ ክልከላዎችን የተላለፈ በመሆኑ ፍፁም ኢ-ህገመንግስታዊ ስለሆነ በፅኑ #እናወግዘዋለን፡፡

ድርጊቱም የሠራዊታችንን ባህሪ እና የተቋሙን አሠራር ያልተከተለና የማይገልፅ የጥቂት አባላት የተሳሳተ እንቅስቃሴ እንጂ እኛን #የማይወክል መሆኑኑ እንገፃለን፡፡

አሁንም ህገ መንግስቱን በማክበርና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የውጭና የውስጥ ሃይልን በመመከት የአገራችንን እና የህዝባችን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ግዳጃችን ላይ ፍፁም የማንዘናጋ መሆኑንም እንገፃለን፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት #መስጊዶች #ተቃጥለዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ጥር 26/ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን ለአብመድ እንደተናገሩት ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች #ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች #የማይወክል መሆኑን አሥረድተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ethiopia #Somalia

" የፕሮግራሙ ይዘት የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ #የማይወክል ነው " - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ትላንት በኢትዮጵያ ብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ (Etv World) በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰራጨ ፕሮግራም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ፕሮግራሙን ተመልክተው ቅሬታቸውን የገለፁ በርካቶች ሲሆኑ ፤ ፕሮግራሙን በተመለከተ የሶማሊያ ሚዲያዎች ሲቀባበሉት ውለዋል።

በEtv የእንግሊዝኛው የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ አሁን ድረስ ያለው ይኸው ፕሮግራም ስለ ሱማሊያ የተለያዩ የሚያነሳ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ አዲሱን ፕሬዜዳንት እና መንግስታቸውን የሚመለከት ነው።

ይህንን ፕሮግራም በተመለከተ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አጭር መግለጫን አውጥታለች።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት በ “Etv WORLD” ፕሮግራም ስለ ሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በሚመለከት በቀረበው ፕሮግራም ላይ ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ መመልከቱን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ የፕሮግራሙ ይዘት የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ የማይወክል እና ከሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጋር የማይጣጣም ነው ብሎታል።

@tikvahethiopia