TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሙስና📈 " ዛሬ እኮ አገልግሎት ተፈልጎ ክፍለ ከተማ ቢኬድ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ፣ ተደብቆ ነው ሲሰጥ የነበረው " በኢትዮጵያ ውስጥ #ሙስና ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ፣ የሚፈፀምበትም መንገድ እየተራቀቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ ...…
የሙስናው መባባስ . . .

የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ፦

" ሙሰኞች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ጠንካራ ስላልሆነ ሙስና ከመቀነስ ይልቅ እንዲጨምር ሆኗል።

የፖለቲካ መዋቅሩ በራሱ አጥፊዎች እንዳይጠየቁ እድል የሚሰጥ ነው።

ሰዎች ሙስና ሰርተው ሲያጠፉ በግልፅ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጥፋተኛ መሆን ሲገባቸው እንደውም ከለላና ሽፋን ሲያገኙ ፣ ከበሉበት ቦታ ወደሌላ ቦታ ዘወር ሲሉ ፣ ሃብትና ንብረት እንዲያገኙ ሲመቻችላቸው ይታያል።

ይሄ ሁሉ የፖለቲካ ስሪቱ ነው። የፖለቲካ ስሪቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑነው። ይሄ ብሄርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት በሙስና ላይ የሰላ ትግል እንዳይደረግና ተጠያቂነት እንዳይመጣ ያደርጋል።

የፖለቲካ ስርዓቱ #ብሄር እና #ትውውቅን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአጥፊውና በጠያቂው መካከል ልዩነት እንዳይኖር ሆኗል።

መፍትሄው ሙስና የሚፈፅሙ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህጉን ጠንካራ ማድረግ ብቻ ነው። "

@tikvahethiopia