TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#በኢትዮጵያ_ኮቪድ19_እየተባባሰ_ነው😷

የጤና ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተባባሰ መምጣቱን #ለቪኦኤ ተናገሩ።

ዶ/ር ተገኔ ሰው ‘አስገዳጅ መመሪያ ተነስቷል ፤ ኮሮና ቫይረስ የለም’ በሚሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እየተመራ እራሱን ለበሽታው እያጋለጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አስገዳጅ መመሪያውም አለመነሳቱን፣ የቫይረሱ ሥርጭትም እየተባባሰ መሆኑን ዶክተር ተገኔ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
5 ዓመት የቱርክ መፈንቅለ መንግስት ከከሸፈ ...

እአአ ጁላይ 15/2016 ተሞክሮ የከሸፈው የቱርክ መፈንቅለ መንግስት ትላንት 5 ዓመት ደፍኗል። በወቅቱ የቱርክ ህዝብ ታንክን ጨምሮ ከባባድ መሳሪያዎችን በባዶ እጁ ፊት ለፊት በመጋፈጥ እጅግ በተጠና ሁኔታ የተደራጀውን ሙከራ ያከሸፈው።

ተሞክሮ በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ወቅት ለሀገራቸው ዘብ ቆመው ህወታቸውን ያጡ የቱርክ ዜጎች ትላንት በመላው ቱርክ ታስበዋል።

ከቱርክ ውጭ በሚገኙም የቱርክ ኤምባሲዎችም ዕለቱ ታስቦ ውሏል።

#በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ አባላት ዕለቱን (ጁላይ 15) እና በዕለቱ ህይወታቸው ያለፈውን 251 ዜጎች በማስታወስ 15 ችግኞችን በአዲስ አበባ ተክለዋል።

የሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስት ላይ በ2016 በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ወቅት 251 ዜጎች ሲሞቱ 2,200 ሰዎች መጎዳታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በ #ኢትዮጵያ ጉዳይ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት (UNSC) በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ ትላንት ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለ ገልጸዋል።

ከወራት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አሁን ላይ እየተስፋፋ መሆኑን እና በርካታ ሰብአዊ ኪሳራዎች እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ሳቢያ፦
- የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እያሻቀበ መሆኑን
- ከ2 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ግጭቱን ተከትሎ መፈናቀላቸውን
- ከትግራይ ክልል በተጨማሪም ወደ አማራ እና አፋር ክልል በተስፋፋው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን፤
- ከሰብአዊ ቀውስ በተጨማሪም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየተጎዳ መሆኑን
- የበሀገሪቱ የብድር ጣራ እየጨመረ መሆኑን
- ሀገሪቱ እዳ የመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን፣
- የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያሸቀበ መምጣቱን ገልፀዋል።

ገተሬስ ፥ የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው መረጋጋት ወሰሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁን ላለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ሲሉ ተናረዋል።

በጦርነቱ የተካፈሉ አካት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲያድርጉ፣ የውጭ ሀገራት ሀይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ፣ ለሰብአዊ ድጋች መተላለፊያ መንገዶች እንዲከፈቱ እና ችግሩን ለመቅረፍ #በኢትዮጵያ_የሚመራና ሁሉንም አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

#Al_AIN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Afar #Amhara " ለሰላም ተስፋ አለ " የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ዛሬ ስለኢትዮጵያ ጉብኝታቸው መግለጫ ሰጥተዋል። በጦርነቱ የተጎዱትን ትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን " በእርግጥ የሚስተዋለው ከጥቂት ወራት በፊት ከነበሩ ግጭቶች ያነሰ ነው " ብለዋል። ከትግራይ ክልል አመራሮች፣…
#USA , #NewYork📍

" በሰማሁት ታሪክ እንባዬን መቆጣጠር አቅቶኛል " - አሚና መሀመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ሃላፊ አሚና መሃመድ የኢትዮጵያ ግጭት በሴቶች ላይ ባደረሰው ከባድ ጉዳት እጅጉን መደንገጣቸውን ገለጹ፡፡

ምክትል ዋና ጸሃፊዋ ይህንን ያሉት ለ5 ቀናት #በኢትዮጵያ
- በትግራይ ክልል
- አማራ ክልል
- አፋር ክልል
- ሶማሌ ክልል ያደረጉትን ጉብኝት በማስመለክት ትላንት በ #ኒውዮርክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

አሚና የትግራይ ክልል ግጭት ባስከተለውን አስከፊ መዘዝ የተጎዱቱን የኢትዮጵያ ሴቶች አግኝተው ማነጋገረቻውን እና በሰሙትም ታሪክ እንባቸው መቆጣጠር እንዳቃታቸው ገልጸዋል፡፡

አሚና ግጭት ባለባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉት ሴቶች " ሊታሰብ የማይቻል አሰቃቂ አደጋ አጋጥሞቸዋል " ብለዋል።

በተለይ በጦርነቱ ወቅት አስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸውን ታሪክ ማድመጥ ኩፉኛ የሚያምና የሚያስለቅስ ጉዳት መሆኑን ገልፀዋል። " ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሊታሰብ በማይቻል መልኩ ተጎድተዋል " ብለዋል አሚና መሐመድ።

በልጆቻቸው ፊት ከተደረፈሩት ባሻገር የደረሰባቸውን ጉዳት የማያስታውሱ ሴቶችን ጭምር ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሚና መሀመድ ፤ በትግራይ አንዲት በተደጋጋሚ በቡድን የተደፈረች፣ በዚህም ወንድ ልጅ የወለደችና አሁን ላይ የቤተሰቦቿንና ማህበረሰቡ አይን ማየት ተስኗት ራሷን አግላ የምትገኝ እንስት አግኝተው አሳዛኝ ታሪክ መስማታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የአብሮነት ጉዞ ነበር ያሉት አሚና " ተመድ በተለይ ለሴቶች እና ህጻናት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማገገም አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ቅድሚያ መስጠቱን ይቀጥላል " ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

በጦርነቱ ከተጎዱት ሴቶች ባሻገርም የኢትዮጵያን ጦርነት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ፕሬዝዳንት እንዲሁም ደግሞ ከትግራይ ክልል መሪዎች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ተናግረዋል።

" ለተፈጸመው ግፍ ሁሉም ተጠያቂ ነው " ያሉት አሚና " አንድ አካል በሌላው ላይ እንዲህ ማድረጉ ፍጹም ተቀባይነት የለውም " ሲሉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ ለተፈጸመው ሁሉ " ያለ ጥርጥር ፍትህ እና ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ሳይታረቁና ተጠያቂ ካልሆኑ ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንደማይችል አስረግጠው ተናግረዋል።

(አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia
#EFN

Ethio Fitness & Nutrition በውጤታማነታቸውና በፈጣን የሰውነት ለውጣቸዉ ተመራጭ የሆኑትን ኦርጅናሉን 100% ክሬቲን አቅርቧል።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.iss.one/ethiofitnessnutrition

አድራሻ ፦ መገናኛ ከዘፍመሽ 200 ሜትር ወረድ ብሎ ግሬስ ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ

አገልግሎቱን ከመጠቀሞ በፊት በድርጅቱ የጥሪ ማእከል #የባለሞያ_ምክርን ያግኙ ፤ 9369

NB : ምርቱ ህጋዊ የሆነ ፍቃድ ያለው #በኢትዮጵያ_ምግብና_መድኃኒት_ባለስልጣን ተመዝግቦ አስፈላጊውን ፍቃድ ያገኘ አስፈላጊውን ፍተሻ ያለፈ ነው።
#ኔዘርላንድ #አቶእሸቱ_ዓለሙ #ደርግ

በኔዘርላንድ የሚገኝ የይግባኝ ፍ/ቤት እ.አ.አ በ2017 ዓ.ም በጦር ወንጀለኝነት ጥፋተኛ የተባሉትን አቶ እሸቱ ዓለሙን የዕድሜ ልክ እስራት ባሳለፍነው ረቡዕ አጽንቷል።

የ67 ዓመቱ ተከሳሽ #በኢትዮጵያ በ1960 ዎቹ እና በ1970ዎቹ በነበረው ጨካኝ ኮሚኒስት ሥርዓት ወቅት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በደች የሚገኝ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ብይን ከ5 አመታት በፊት ሰጥቶ ነበር።

አቶ እሸቱ ዓለሙ የ2017 ፍርድ እንዲቀለበስላቸው ይግባኝ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም በሄግ የሚገኘው የይግባኝ ፍርድ ቤት ግን በ1960ዎቹ መጨረሻ እና በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ በኮ/ሌ መንግሥቱ ኃ/ማሪያም አመራር በተፈጸመው የቀይ ሽብር ዘመቻ ተሳታፊ ነበሩ ሲል ውሳኔውን አጽንቷል።

አቶ እሸቱ በመታመማቸው ምክንያት በይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ አልተገኙም ነበር።

የጉዳዩ ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ ወደ 150,000 የሚጠጉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ምሑራንና የፖለቲካ ሰዎች በወቅቱ የነበረው ስርዓት ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት ባደረገው ዘመቻ በጭካኔ ተገድልዋል።

አቶ ዓለሙ እአአ በ1978 በጎጃም ክፍለ ሀገር የደርግ ተወካይ የነበሩ ሲሆን በወቅቱ ደርግ በክፍለ ሀገሩ ከተቃዋሚዎቹ አንዱ ከነበረው ከኢህአፓ ጋር ሲፋለም ነበር።

ፍርድ ቤቱ እንዳለው " በተከሳሹ እውቅናና ተሳትፎ " የጦር ወንጀል በክፍለ ሃገሩ ይፈጸም ነበር።

በመቶዎች የሚቆጠሩና አብዛኞቹ ወጣት ተማሪዎች የሆኑት ሰለባዎች ካለ በቂ ምክንያት ተይዘው ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የታሰሩ ነበር።

አንዳንዶች በከፋ ሁኔታ ሲደበደቡ አብዛኞቹ ደግሞ ካለ ፍርድ ሂደት ወደ እስር ቤት ይጋዙ ነበር። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰለባዎች ደግሞ በሞት ተቀጥተዋል።

" የሞት ቅጣቱ በተከሳሹ አመራር ሰጪነት በጭካኔ ይፈጸም ነበር " ብሏል ፍ/ቤቱ።

አቶ ዓለሙ በ2017 የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት የፍርድ ሂደቱ መጀመሪያ ላይ በስሜት ተሞልተው ባደረጉት ንግግር በደርግ ላይ የቀረበውን ውንጀላ ተቀብለው ነገር ግን እርሳቸው በግላቸድ የፈፀሟቸው አለመሆናቸውን ለዳኞች ገልፀው ነበር።

አቶ ዓለሙ በደች ፍ/ቤት ጉዳያቸው ሊታይ የቻለው ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጀምሮ ኔዘርላንድ ውስጥ መኖር በመጀመራቸውና በ1998 የሀገሪቱን ዜግነት በመቀበላቸው ነው።

#ASSOCIATED_PRESS | #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ስለ #ኢትዮጵያ እና ታላላቅ ሀይቆች ቀጠና ምን አሉ ? ዛሬ ቃለ መሀላ የፈፀሙት የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚያከናውኑትን ተግባር እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ሩቶ ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት…
#KENYA

አሜሪካ ያሰራጨችው ፅሁፍ ?

ከቀናት በፊት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለመሀላ በፈፀሙ ወቅት ባሰሙት ንግግር የቀድሞ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ #በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር ማከናወናቸውን ገልፀው እሳቸውም የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳውቀው ነበር።

ሩቶ ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል መስማማታቸውን እና የኬንያ ሕዝብን በመወከል የሰላም ንግግሮችን ለመምራት መስማማታቸውንም በዕለቱ ገልፀው ነበር።

ትላንት የአሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባሰራጨው መልዕክት ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላለው ግጭት የሰላም ልዩ ልዑክ ሆነው መሾማቸውን በደስታ እንደምትቀበለው ገልፃለች።

አሁሩ በሰላም ልዩ ልዑክነት የተሾሙበት ወቅት ለሁለቱም ግጭቶች ወሳኝ በሆነ ጊዜ መሆኑን እና ስራቸውም ወሳኝ እንደሚሆን አሳውቃለች።

አሜሪካ ትላንት ባሰራጨችው መልዕክት ኡሁሩ ኬንያታን ማን እንደሾማቸው በግልፅ አለመፃፏን ተከትሎ በርካቶች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል፤ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ምትክ የተሾሙ የመሰላቸውም አልጠፉም።

ግርታው አሜሪካ ያሰራጨችው መልዕክት ሙሉ ባለመሆኑ የተፈጠረ ሲሆን ኡሁሩ ኬንያታ የተሾሙት በሀገራቸው ኬንያ ፤ የኬንያን ህዝብ እና መንግስት ወክለው የተጀመሩ ሰላም ንግግሮችን እንዲቀጥሉ ነው እንጂ በአፍሪካ ህብረት ስር አይደለም።

የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ አሁንም ስራ ላይ ናቸው፤ ከጥቂት ቀናት በፊት የኃላፊነት ጊዜያቸው እንደተራዘመላቸው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ የወጣው የጋራ መግለጫ 12 ነጥብ የያዘ ነው። ከዚህም ስምምነት መካከል ፦ - የህወሓት ቡድን #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል። - የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል። …
#ETHIOPIA🇪🇹

#በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ የቀደመው ሁኔታ እንዲፈጠር  ሁሉም አካል ዛሬ ወደ ተደረሰው " የሰላም ስምምነት " #ተፈፃሚነት እና #ተግባራዊነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ህብረት ፤ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት በስኬት እንዲጓዝ እና ሰላም እንዲሰፍን  የስምምነቱ ትግበራ " ወሳኝ ይሆናል " ሲሉ ነው ያስገነዘቡት።

በዚሁ አጋጣሚ ለሰላም መስፈን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከሚጫወቱት ሚና ባለፈ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥላቻ እና እርስ በእርስ መራራቅን ከሚሰብኩ ንግግሮች በመቆጠብ በሰላም ማስፈኑ የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው።

@tikvahethiopia
የካንሰር ህክምና . . . #በኢትዮጵያ

#ጥቁር_አንበሳ

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ መኖራቸውን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ክፍል ኃላፊ ኤዶም ሰይፉ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" የተለያዩ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ከ2013 መጨረሻ፣ 2014 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ወረፋ ያልደረሳቸው አሉ፡፡

ይሁን እንጂ በየዕለቱ የሚመጡ ድንገተኛ የካንሰር ታካሚዎች በመኖራቸው በቅድሚያ ለእነዚህ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።

በሆስፒታሉ ቆይተው መታከም ይችላሉ ተብለው የተለዩት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ነው።

ለዚህ ወረፋ መብዛት ዋነኛ ምክንያት ብለው ያቀረቡት በሆስፒታሉ የሚገኘው መሣሪያ #አንድ ብቻ መሆኑን ነው።

በዚህ ዓመት ብቻ በተደረገው ማጣራት የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠበባቁ 5,000 ታካሚዎች ሲኖሩ፣ በማዕከሉ በቀን በአማካይ ከ300 በላይ ታካሚዎች ይስተናገዳሉ።

ከእነዚህ የካንሰር ታካሚዎች መካከል 70 በመቶ የጨረር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ ኬሞ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው የታካሚዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ።

በማዕከሉ አገልግሎት ለማግኘት የ2014 ዓ.ም. እና በ2015 ዓ.ም. ሕክምና ለማግኘት የተመዘገቡ ደግሞ ከ10,000 በላይ ናቸው። "

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ስፔሻላይዝድ_ሆስፒታል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክሊኒካል ኢንኮሎጂስት ዶ/ር አማረ የሺጥላ ምን አሉ ?

"  በሆስፒታሉ የሚሰጠው የካንሰር ሕክምና ኬሞ ቴራፒና ቀዶ ጥገና ነው።

የጨረር ሕክምና ለመጀመር የማሽን ተከላ ላይ እንገኛለን። 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ታካሚ እስኪጠናቀቅ እየተጠባበቁ ነው።

በሆስፒታሉ ካንሰር ሕሙማን ሕክምና አንዱ የሆነው ኬሞ ቴራፒ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ በዛ ከተባለ ከሳምንት አይበልጥም።

ይሁን እንጂ ለካንሰር ሕሙማን የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመጠባበቅ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ያስፈልጋል። "

#በሐሮሚያ_ዩኒቨርሲቲ_ሕይወት_ፋና_ሆስፒታል

በሐሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሻውል (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን እየተሰጠ ነው።

የጨረር ሕክምና ከተጀመረ ስድስት ወራት አስቆጥሯል ፤ የታካሚዎች መጠነ መጠበቅ ከሦስት ወራት አይበልጥም።

በሆስፒታሉ በዓመት እስከ 6000 የካንሰር ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። በተለይ ደግሞ ጨረር ሕክምና ከተጀመረ በኋላ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ በምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜያት ብቸኛው የካንሰር ሕክምና መስጫ በመሆኑ ከሶማሌላንድና ከሌሎች አገሮች እየመጡ አገልግሎት የሚያገኙ ነበሩ። "

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ ላይ ሳለ #መስኮቱ_መገንጠሉን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከበረራ አግዶታል።

የአሜሪካው አላስካ አየር መንገድ በቁጥር 65 የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖቹን አግዷል።

እገዳው በበረራ ወቅት የአንደኛው አውሮፕላን መስኮት ተገንጥሎ አውሮፕላኑ በአስቸኳይ ለማረፍ ከተገደደ በኋላ ነው።

አርብ ዕለት በኦሬጎን ግዛት ከፖርትላንድ ከተማ ተነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የገጠመውን አደጋ ተከትሎ ከ35 ደቂቃዎች በረራ በኋላ በመነሻው ለማረፍ ተገዷል።

አየር መንገዱ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩት 177 ተሳፋሪዎች እና ሠራተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው አውሮፕላኑ #በሰላም አርፏል ብሏል።

የአደጋው መንስዔ እስኪጣራ ድረስ ሁሉንም 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከበረራ እንዳገደ አየር መንገዱ አስታውቋል።

ይህ ቦይንግ ሰራሹ አውሮፕላን ባለፉት ዓመታት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ከአምስት ዓመት በፊት #በኢትዮጵያ እና #ኢንዶኔዢያ ባጋጠመ አደጋ ምክንያት ከበረራ ታግዶ የነበረው ይህ ማክስ 737 ዝርያ መሆኑ ይታወቃል። #BBC

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

“ የካንሰር ሕመም እየጨመረ ነው ” - ዶክተር አስቻለው ወርቁ

በኢትዮጵያ የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን፣ በተለይም ማኀበረሰቡ ትንቦሆ፣  አልኮል ነክ ነገሮችን ከመጠቀም እንዲታቀብ ጥሪ ቀረበ።

ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በተለይ በኢትዮጵያ በኩል የፋይናንስ እጥረት ችግር እንደፈተነው ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተቋሙ የ20ኛ ዓመት ምስረታውን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካንሰር #በኢትዮጵያ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? በበሽታው የተጠቂ ሰዎች ቁጥር ቀነሰ ወይስ ጨመረ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

የተቋሙ የቦርድ አባልና የውስጥ ደዌ ባለሙያው ዶክተር አስቻለው ወርቁ ምን አሉ ?

“ በጣም እየጨመረ ነው ያለው። ለመጨመሩ የተለያዩ ምክንያቶች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች እየጨመሩ ነው። የካንሰር ህመምም እየጨመረ ነው።

ለምሳሌ፦ የሳንባ ካንሰርን ብናዬው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ነው ያለው። የምንመረምረው ጥቂት ሰዎችን ስለሆነ በዚያችው ዳታ ተመርኩዘን ነው የምንገልጸው። ማኀበረሰቡን ያማከለ የዳሰሳ ጥናት ካልሰራን ቁጥሩን በትክክል መግለጽ ከባድ ነው።

10 ሰዎችን መርምሮ 5 ሕሙማን ቢገኝ 50 በመቶ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ያልተመረመሩ ብዙ ስለሚኖሩ። እንደ አጠቃላይ ካየነው ግን ፦
- የሳንባ፣
- የአንጀት፣
- የጉበት፣
- የማህፀን፣
- የደም ሴል ካንሰር ታማሚሞች ቁጥራቸው እጅግ ባጣም እየጨመረ ነው ያለው። ” ብለዋል።

ካንሰር ዋነኛ የሞት እና የስቃይ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ቁጥሮች እንደሚያመላክቱ ተገልጿል።

ለአብነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሞቱ ሰዎች ካንሰር የመገኘት እድሉ ከፍ ብሏል። ምክንያቱም የሳንባ ካንሰር ካሉት የካንሰር ዝርዝሮች ወደ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው ተብሏል።

የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ምን አሉ ?

“ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትንባሆ መሸጥም መግዛትም እንዳይችል የሚነገርበት ጊዜ መቼ ነው ?

ትንባሆ ነክ ነገሮች፣ አልኮል በሽታውን እያስፋፉት ነው።
 
ከ3,000 በላይ የካንሰር ሕሙማንና ቤተሰባቸውን እረድተናል። በአሁኑ ወቅት 175 ለካንሰር ሕሙማንና ለቤተሰባቦቸው፦

° ከአገራቸው የሚመጡበት ሙሉ የትራንስፖርት፣
° ከውጪ የሚገዙ መድኃኒቶች፣ 
° በሆስፒታል ውጪ በግል ተቋማት ለሚሰሩ የላብራቶሪ ምርመራ፣ 
° ሆስፒታል ለተኙት ሕሙማን ለአንዳንድ ነገር መሸፈኛ በወር 1,000 ብር፣
° እየታከሙ ለሚማሩ ተማሪዎች በወር 1,000 ብር፣
° 24 አልጋ ባለው የካንሰር ሕክምና ማዕከል በየዕለቱ ለቁርስ፣ ምሳ፣ በክሰስና እራት ወጪዎችን እየሸፈንን ነው። ”

NB. ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ የአቶ ወንዱ በቀለ የ4 ዓመት ጨቅላ ልጃቸው በካንሰር በሽታ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን “ ማቲዎስ ቢሞትም ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን ” በሚል መልካም አስተሳሰብ በመቀየር በ15 መስራች አባሎች ሚያዚያ 9 ቀን 1996 ዓ/ም የተመሠረተ ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia