#ETHIOPIA
በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል።
በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል።
#ለማስታወሻ - የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፦
- ከኢንተርናሽናል እና የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ውጭ ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይተገበራል።
- ግብረ ገብ ፣ አገር በቀል ዕውቀት ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናት እና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው ይሰጣሉ።
- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት ይሰጣል።
- ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይሰጡ የነበሩት ኬሚስትሪ ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ " ጄኔራል ሳይንስ " ተብለው ይሰጣሉ። ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል።
- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤ ከ7ኛ ክፍል -12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል።
- ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ።
- 3ኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን #ተጨማሪ_ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል።
- አጠቃላይ ፈተና በክልል ደረጃ 6ኛ ክፍል ላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል።
- የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች " ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን " የተባለ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው ይሰጣቸዋል።
- 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ቢዝነስ ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከእነዚህ የሙያ ትምህርቶች ውስጥ የመረጡትን ይወስዳሉ።
- የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍልን እንዲሁም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ 5 የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል ፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ / ኢፕድ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia