TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WolaitaSodo

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ያለው ጌታቸውን ምክትል ከንተባ ሆነው እንዲሰሩ ሾመ። ምክር ቤቱ ሹሙቱን የሰጠው ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ ዙር ሰባተኛ የስራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው። በተጨማሪም የከተማ የፋይናንስና ኢኮኖሚ እንዲሁም እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈቶች ኃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል። ተሿሚዎች በምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolaitaSodo

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የወላይታ ህዝብ የድጋፍ ስልፍ አካሄደ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰላም የኖቬል ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ የወላይታ ህዝብ በሶዶ ከተማ የድጋፍ ስልፍ አካሂዷል፡፡ የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በህገመንግስትና በሰላማዊ መንገድ እንዲመለስ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት ለሀገራችን የኩራት ምንጭ መሆኑን የጠቀሱት ሰልፈኞቹ በዚህም የወላይታ ህዝብ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ይህ እድልም ከአድዋ ድል ያልተናነሰና ሀገራቱን ወደ ከፍታ ማማ የሚያሸጋግር ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም የወላይታ ህዝብ የጠየቀው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዳር ለማድስ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉም ጠቁመዋል፡፡

በእለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩቤ ሽልማቱ ሀገራችንን የመልካም ዝና ባለቤት ያደረገ ነው ብለው ለቀጣይ ትግል ስንቅ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ምላሽ ለማግኘት ያሳየውን ትዕግስት አድንቀው ጥያቄው እንዳይቀለበስ በተለይ ወጣቱ በስከነ መንገድ መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል፡፡

(SRTA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WolaitaSodo

በወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ዛሬ ታህሣስ 10/4/2012 ዓም ዓመት መሙላቱን ምክንያት በማድረግ ሁሉም የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር ሸማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ነጋዴዎች መንግስት ሰራተኞች በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው ጉተራ አዳራሽ ወይይት አድርገዋል። የዕለቱ ተሳታፊዎች የህዝብ ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ ብቻ መቀጠል አለበት ብለዋል።

(ወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር)
@tikvahethioia @tikvahethiopiaBOT
#WolaitaSodo

በወላይታ ሶዶ ከተማ "መርካቶ ገበያ" ዛሬ መንስኤ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የወ/ሶዶ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን የበኩሉን ጥረት እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም ካለው ከባድ ነፋስ የተነሳ እዘሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመት በመሆኑ ተጨማሪ ኃይል እንደሚያስፈልግ የከተማዋ ነዋሪዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

Via Wolaita Zone Communication
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WolaitaSodo

ዛሬ ጥዋት በወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆች እና ተቋሟት ላይ ውድመት አስከትሏል።

ጥዋት የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የከተማው አስተዳደር ያሳወቀው ከ6:20 በኃላ ነው።

እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት የወላይታ ሶዶ ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋውን አቅርቧል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራው ይገኛል።

Via Wolaita Sodo Administration
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#WolaitaSodo ዛሬ ጥዋት በወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆች እና ተቋሟት ላይ ውድመት አስከትሏል። ጥዋት የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የከተማው አስተዳደር ያሳወቀው ከ6:20 በኃላ ነው። እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት የወላይታ ሶዶ ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ…
#WolaitaSodo

ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል።

በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል ፤ ከነገ ጀምሮ ወደ ሥራ ይገባል።

የመርካቶ ገበያ መቃጠል የንግዱ ማህበረሰብን ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የሶዶ ከተማ ገቢ የሚመነጨው ከገበያ ማዕከሉ በመሆኑ በከተማይቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የትላንቱ የእሳት አደጋ ከባድ በመሆኑ ወደተለያዩ የከተማው ክፍሎች እና አካባቢዎች እንዳይዛመት ፦

- የሐዋሳ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ማጥፊያ ቡድን፣
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ማጥፊያ ቡድን፣
- የሲዳማ ክልል መንግስት ፣
- የፀጥታ አካላት፣
- የግል ባለሀብቶች እና መላው የወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና ቀርቧል።

ዛሬ የክልል ፣ የዞን እና የወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በመርካቶ ገበያ የእሳት አደጋው ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

ወላይታ ሶዶ ከዚህ በፊት አራት ጊዜ እንዲህ አይነት ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አስተናግዳለች። የትላንቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተከሰተ አደጋ ነው።

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል ዝግጅት !

#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል ካለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የሚመለከታቸው አካላትን ያሳተፈ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው።

ግብረ ሀይሉ የጸጥታ ሃይሎች ፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የእምነት አባቶችን ያካተተ ነው።

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ከተማዋን የማጽዳትና የማስዋብ ሥራ በወጣቶች እየተካሄደ መሆኑንም ተገልጿል።

የከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ፥ "በየክ/ከተማ ከሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች በአሉ በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ ሀይሉ ጋር እየሰሩ ነው” ብሏል።

በሐዋሳ ከተማ እንግዶች ካለምንም የፀጥታ ስጋት ከተማዋን ጎብኝተው እንዲወጡ የተቀናጀ የጸጥታ የማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቋል።

#WolaitaSodo

የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቋል።

ከከተራ ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ የፀጥታ አካላት ጋር በመወያየት በየአካባቢው ምደባ መደረጉ ተገልጿል።

#DireDawa

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡና ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያይቶ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ እና ደህንነት ችግር በድምቀት እንዲከበር ለማድረግ ዝግጅት እንዳጠናቀቀ አሳውቋል።

የጸጥታ ማስከበር ስራው በድሬደዋ ፖሊስና በፌደራል ፖሊስ ቅንጅት የሚከናወን ነው ተብሏል።

በጸጥታ ማስከበር ስራው በየቀበሌው እና በየአካባቢው የተደራጁ ወጣቶችም ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል። ~ ENA

PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WolaitaSodo : የዎላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዎላይታ ጉታራ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም አድስ መንግስት ምሥረታ በዞኑ የሚካሄድ ሲሆን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የሌሎች የመንግሰት ኃላፊነት ሹመት ይፀድቃል።

@tikvahethiopia
#WolaitaSodo

ከጥቂት ቀናቶች በፊት በአርባምንጭ ከተማ የምስረታ ጉባኤውን ያደረገው የ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  መንግስት " ዛሬ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ያካሂዳል።

የፌዴሬሽኑ 12ኛው ክልል የስራ ማስጀመሪያውን መርሀግብር የሚያከናውነው በዛሬው ዕለት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ነው።

ከተማዋም ባለፉት ሳምንታት አዲሱን የክልሉን አመራር አቀባበል ለማድረግ ዝግጅቷን ስታካሂድ ነበር።

ዛሬ ለሚካሄደው የስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር የፌዴራልና የአዲሱ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ ከተማው ገብተዋል።

በአዲሱ አደረጃጀት የተቋማት ክፍፍል መሰረት " ዎላይታ ሶዶ " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዋና መቀመጫ እንዲሁም የክልሉ ዋና የፖለቲካ ማዕከል ናት።

ፎቶ፦ የዎላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#WolaitaSodo

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የከተማው ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  አረጋግጧል። 

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ምስጋናው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራበት ኪዳነ ምህረት ቀጠና ላይ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ አደጋ ተከስቷል። በዚህ አደጋ የ2 ሰዎች (ወንድና ሴት) ሕይወት ሲያልፍ ችሏል" ብለዋል።

" ሌሎቹ 17 የሚሆኑ ወንዶች፣ 6 ሴቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያሉ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያና ኦቶና ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ፣ "አንደኛዋ ሟች ከሹፌሩ ጋር የነቀረች ሴት ናት። አንደኛው ደግሞ ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪ ነበር" ነው ያሉት።

አደጋው የተከሰተውም በሕዝብ ማመላለሻ፣ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ)፣ በባለ ሁለት እግር ሞተር፣ በአንድ የቤት መኪና መካከል መሆኑን ገልጸው፣ "ሁሉም ላይ ጉዳት ደርሷል" ብለዋል።

" የአደጋው መንስኤ፣ ጥፋት የማነው? የሚለውን በሂደት ላይ ነን፣ ሹፌርም ተጎድቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በበኩሉ፣ " የአፈር ማዳበሪያ የጫነው የጭነት መኪና ፍሬን በመበጠስ ምክንያት ከባድ የመኪና አደጋ ተከስቷል " ብሎ በዚህም 2 ሰዎች ሞተዋል ፤ 24 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አሳውቋል።

በአደጋው ፦
- አንድ ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና
- ሁለት ቶዮታ ቪትዝ
- ሶስት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

More - https://t.iss.one/ThiqaMediaEth/301

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia