TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰኔ15 #ባህርዳር

በእነየማነ ታደሠ መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ ቀዳሚ ምርመራ ለመስማት ለነሐሴ 9/2011 ተቀጠረ። በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው ‘መፈንቅለ መንግሥት’ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የ47ቱ ጉዳይ ዛሬ በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታይቷል። ችሎቱ ቀዳሚ ምርመራን ለመስማት ቢሰየምም ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ለማቆም በቂ ጊዜ አልነበረንም፤ የክስ ወረቀትም አልደረሰንም በሚል ጉዳያቸው ሌላ ቀን እንዲታይ ጠይቀዋል።

ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ለማዘጋጀት ከአርብ ጀምሮ ጊዜ ነበራቸው፤ የክስ ወረቀትም ያልደረሳቸው ምስክሮች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል መሆኑን ጠቅሶ ለቀዳሚ ምርመራው የመንግሥት ጠበቃም ቢሆን ቆሞላቸው ችሎቱ ይቀጥል ብሏል።

ግራ ቀኙን ያደመጠው ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎች የክስ ወረቀት ሊደርሳቸው ይገባል፤ ጠበቃ ማቆም የሚችሉ ከሆነ የመንግሥት ጠበቃ የሚያስቀርብ አይደለም በሚል ቀዳሚ ምርመራውን ለመስማት ለሐሙስ ቀጥሯል።

Via #BBCAMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባሕር ዳር አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ የአሲድ ጥቃት ተፈጸመባቸው!

ለበቀል የተነሳች ሴት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር ላይ የአሲድ ጥቃት መፈጸሟ ታውቋል፡፡

ግለሰቧ የስራ ሀላፊው ላይ የአሲድ ጥቃት የፈጸመችው ነሐሴ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ነው ተብሏል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ የሥራ ሂደት አባል የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ይስማው ታሪኩ ተጠርጣሪዋ ጥቃቱን ለመፈጸም አሲድ ገዝታ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ላይ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ እንደሄደች ነገር ግን ስብስባ ላይ ናቸው ተብላ እንደተመለሰች፤

ከሰዓት በኋላ ስትመለስ ግን የስራ ሀላፊው ቢሯቸው ውስጥ በሥራ ላይ እንዳሉ እንዳገኝቻቸውና በጆግ ይዛው የመጣችውን አሲድ ከቅርብ እርቀት ላይ ሆና እንደደፋችባቸው ከዚያም ምን እንደተከሰተ መለስ ብላ ሳታይ እሩጣ እንደወጣች ቃሏን ለፖሊስ ሰጥታለች ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዋ ድርጊቱን ፈጽማ ለማምለጥ ብትሞክርም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ትብብር በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የስራ ሀላፊም ወዲያውኑ ወደ ሐኪም ቤት ተወስደው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል።

የክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ ደመላሽ ስንሻው በተፈጸመባቸው የአሲድ ጥቃጥ በሁለት እጆቻቸው እና ሆዳቸው አካባቢ የመጥቆርና የማበጥ እንዲሁም ፊታቸው ላይ አልፎ አልፎ የመቃጠል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ ተጠርጣሪዋ ጥቃቱን ለመፈጸም የተጠቀመችበትን አሲድ ለመኪና ባትሪ በሚል እንደገዛችው ለፖሊስ የተናገረች ሲሆን ፖሊስም የአሲዱን ምንጭ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል።

#BBCAmharic

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-3
የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወይም ነገ ጠዋት ይፋ ይደረጋል!

በእርማት ወቅት ስህተት አጋጥሞ በተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ላይ ቅሬታ ፈጥሮ የነበረው የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤት ዛሬ አርብ አልያም ነገ ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ። የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሔር ለቢቢሲ እንደገለጹት የፈተናው እርማት ላይ የተፈጠረውን ስህተት በማስተካከል በድጋሚ እርማቱ አካሂዶ በማጠናቀቅ ውጤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወይም ነገ ጠዋት ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል። ማክሰኞ ዕለት ይፋ የተደረገውን የሃገር አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን ተከትሎ በተለይ የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት ውጤት ላይ በበርካታ ተማሪዎች ቅሬታ መቅረቡ ይታወሳል። የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲም ቅሬታውን ተቀብሎ በተጠቀሰው የፈተና ውጤት ላይ ምርመራ በማድረግ በእርማቱ ወቅት ችግር እንደነበረ በመግለጽ የተፈጠረውን ስህተት ለማረም እየሰራ እንደሆነ ገልጾ ነበር።

Via #BBCAmharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የማቋቋም ጥያቄ የቤተ ክርስቲያኗ የዶግማና የቀኖና ትውፊት ለውጥ ሳይኖር አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅር የማበጀት ጥያቄ ነው" የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ

#ቢቢሲአማርኛ #BBCAMHARIC

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቃቸው ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ክልላዊ ፅህፈት ቤቱን ጥያቄ የሚቀበለው ከሆነ የሰው ኃይል አመዳደቡም ሆነ አፈፃፀሙ ይህ አደራጅ ኮሚቴና ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጋራ የሚወስኑት እንደሚሆን ተገልጿል።

በተጠየቀው መሰረት አስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የምዕመኑን ጥያቄ ለመመለስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚቴው አስጠንቅቋል። እርምጃው ምን እንደሆነ በዚህ ወቅት ግልፅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት በራሳቸው ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እናቋቁማለን ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሏቸው ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ…
#AmharaRegion

ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ተገደሉ።

የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

ወ/ሮ ሚሊሹ በዛሬው እለት ነው የተገደሉት።

እንደ ወረዳው መረጃ ፥ የመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ውለው ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የተገደሉት።

ግድያ የተፈጸመባቸው አመራሯ በእናትነት ላይ ነፍሰ ጡርነትን ይዘው እንደነበር ተገልጿል።

የወረዳው አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ " ግድያው የተፈጸመው በጽንፈኛ አካላት #በተተኮሰ ጥይት ነው "  ብሏል።

ከቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ አልብስ አደፍራሽ #በታጣቂዎች_መገደላቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ #የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ ነው የተሰማው።

ጥቃቱ አነጣጥሮባቸው ነበር ከተባሉት ውስጥ፦

➡️ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ

➡️ የወልዲያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ይገኙበታል።

መኖሪያ ቤታቸው ላይ ነበር ጥቃት የተፈጸመው።

ከዚህም ባለፈ የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

" #ባልታወቁ_አካላት " ተፈጽሟል በተባሉት ጥቃቶች በባለስልጣናቱ ላይ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጉባ ላፍቶ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ተነግሯል።

ባለፈው #ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia
#BBCAmharic

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz ° “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው” - የወምበራ ወረዳ ነዋሪዎች ° “ ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን ” - የደብረ ዘይት ማዕከል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ወምበራ ወረዳ ደብረ ዘይት ከተማ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጨለማ ውስጥ ለመኖር መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ…
#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አሶሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ 2 ሳምንት አልፏል።

የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አገልግሎት ሊቆም እንደሚችል አሳውቋል።

ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ400 እስከ 500 ከዞን ፣ ከወረዳ፣ ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ታካሚዎችን ያስተናግዳል።

ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር 24 ሰዓት ሙሉ የማይቋረጥ ኃይል ማግኘት ያለበር ቢሆንም ባለፉት ሳምንታት የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።

ኃይል ከተቋረጠበት ቀን አንስቶ ለጄኔሬተር በየቀኑ ከ180 እስከ 200 ሊትር ነዳጅ እየተጠቀመ ነው።

ሁለት ጄኔሬተሮች ያሉ ቢሆንም ሙሉ ሆስፒታሉን ኃይል እንዲያገኝ የሚያስችሉ አይደሉም።

ያለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ለማቆየት የሚሆኑ ማሽኖችን ማስነሳትም ከባድ ሆኗል።

በዚህ ማሽን ውስጥ የሚቆዩ ሕጻናት ያልተቋረጠ ኦክስጅን ማግኘት ስላለባቸው ኃይል መቋረጥ ካጋጠመ በሕጻናቱ ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል።

ሆስፒታሉ የተወሰኑ የሥራ ክፍሎችን የኃይል አቅርቦት እያጠፋ ነው ጄኔሬተሩ ሲነሳ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ወደ ጨቅላ ሕጻናት ማቆያ ማሽኑ የሚቀይረው። ሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ኃይሉ ሲፈለግ ደግሞ ማሽኑን ለማቋረጥ ይገደዳል።

ቀድሞም የበጀት እጥረት የሚፈተነው ሆስፒታሉ ለጄኔሬተሩ የሚውለው ነዳጅ ወጪ ከአቅም በላይ እንደሆነ የነዳጅ ማከማቻም አለመኖር ፈተና እንደሆነ ገልጿል።

ሆስፒታሉ ነዳጅ ከተለያዩ መ/ቤቶች እና ባለሃብቶች በልመና ነው ማታ ማታ እየዞረ የሚያመጣው።

ሁኔታው በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ጭምር ሊቋረጥ የሚችልበት አዝማሚያ እንዳለ አሳውቋል።

የአሶሳ ዞን ፥ በአሶሳ ከተማ እና በአካባቢው የኃይል መቋረጥ የተከሰተው በአጎራባች የኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ " በታጣቂዎች " በደረሰ ጉዳት እንደሆነ አሳውቋል።

#BBCAMHARIC

@tikvahethiopia