TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ #ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

👉 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) #አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።

ቅዳሜ ደግሞ ግማሽ ቀን ነበር የሚሰራው።

ከዛሬ በኃላ በአ/አ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋት 2:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ በሁሉም ቅርንጫፍ ከጥዋት እስከ 11:30 አገልግሎት ይሰጣል።

ዛሬ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የስራ ሰዓት ማሻሻያ ባደረገበት ስነስርዓት ላይ የተገኘው ፍትህ ሚኒስቴር ፤ ይህ አሰራር የተገልጋዮችን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ በመሆኑ ሌሎችም ተቋማት መሰል አሰራር ቢከተሉና ወስራ ቢያስገቡ ሲል ጠይቋል።

@tikvahethiopia