TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦ " ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በኋላ እንዲሁም ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋናነት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች " የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሣሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሣሪያ አውጡ " በሚል ምክንያት ሴቶችና የአእምሮ ሕመምተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሲቪል ሰዎች በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን፣…
#Gambella

ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ተሰምቷል።

ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ 12 ተከሳሾች ግን የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ብይኑን የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ-መንግሥት እና በሕገ-መንግሥት ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። 

ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት እነማን ናቸው ?

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
የቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር፣
የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬ እና የተለያዩ የፀጥታ አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ 15 ተከሳሾች ናቸው።

ተከሳሾቹን ላይ የቀረበው ክስ ምንድነው ?

ሰኔ 7/2014 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ መንግሥት በአሸባሪ ቡድንነት የፈረጀው " ሸኔ " እና የጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር (ጋነግ) በጋራ ሆነው ቀበሌ 03 በፌደራል ፖሊስ ካንፕ እና በክልሉ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሌሎች ፀጥታ አካላት ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው ነበር።

በኃላም ጥቃት አድራሾቹም በፀጥታ ኃይሎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ማንነታቸው የተለዩ 35 ሰዎች እና ማንነታቸው ያልተለዩ ሌሎች ንፁሃንን " #መረጃ_ሰጥታችኋል " በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ  ትዛዝ ሰጥተዋል ፤ በግድያው ላይ የተሳተፉም አሉ የሚል ነው።

የክስ መዝገቡ የተከሳሾች የተሳትፎ ደረጃቸውን በዝርዝር አስቀምጧል።

ፍርድ ቤት ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

ከ15ኛው ተከሳሽ ውጭ ሌሎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ግለሰቦቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን አሰምቷል። ማስረጃዎቹን አቅርቧል።

ፍርድ ቤት ፦
° የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
° ቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬን ጨምሮ 13 ተሳሾች በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ዛሬ በዋለው ችሎት 12 ተከሳሾች የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በበቂ ሁኔታ መከላከል አለመቻላቸው ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከላቸው ተጠቅሶ ነጻ ተብለዋል።

ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾችንና የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከዚህ ቀደም የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አባል ኮ/ል አቶሬ ጉር እና የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ አባል ረ/ሳጅን ቾድ ቤንግን በተመለከተ ፍ/ቤቱ በቀረበባቸው ክስ ላይ በቂ ማስረጃ አለመሰማቱን ተገልጾ በነጻ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤፍቢሲ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia