TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Facebook

• " ፌስቡክ በገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ አለ " - ግሎባል ዊትነስ

• " የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች ተላልፈዋል። ችግሩ የተፈጠረው የምንጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው " - ፌስቡክ

በጎረቤት ኬንያ በነሐሴ ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን ከገፁ ላይ እንዲያጠፋ የኬንያ ባለስልጣናት ጠይቀዋል።

ፌስቡክ ማስተካከያ ካላደረገ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ግሎባል ዊትነስ የተባለ የመብት ቡድን ባወጣው ሪፖርት ፌስቡክ የዘር ግጭት የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮች ያሉባቸው ማስታወቂያዎችን ማፅደቁን ይፋ አድርጓል።

ግሎባል ዊትነስ በጥናቱ ሂደቱ 10 በእንግሊዘኛ እና 10 በስዋሂሊ ቋንቋ የተሰሩ የጥላቻ ንግግር ያዘሉ ማስታወቂያዎችን ለፌስቡክ ያስተላለፈ ሲሆን ሁሉም ማስታወቂያዎች መፅደቃቸውን የተቋሙ ዋና አማካሪ ጆን ሎይድ ተናግረዋል።

በኬንያ ፌስቡክ #ከ10_ሚሊየን_በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በነሐሴ ወር የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በማህበራዊ ድህረገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ መኖሩን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ፌስቡክ ትላንት ባወጣው መግለጫ የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች በገፁ መተላለፉን አምኖ ችግሩ የተፈጠረው ድህረገፁ የሚጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው ብሏል።

አክሎም፣ በተለይ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ቴክኖሎጂዎች ጎጂ መረጃዎችን በማስወገድ እንዲያግዙት እና ምርጫው ሰላማዊ እና ስጋት የሌለበት እንዲሆን በሰዎች ላይ እና ቴክኖሎጂዎች ላይ እንዲሰራ መጠየቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia