#እንድታውቁት
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።
በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።
በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦
- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ #ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።
👉 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።
- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) #አገልግሎት ይሰጣል።
በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።
ቅዳሜ ደግሞ ግማሽ ቀን ነበር የሚሰራው።
ከዛሬ በኃላ በአ/አ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋት 2:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ በሁሉም ቅርንጫፍ ከጥዋት እስከ 11:30 አገልግሎት ይሰጣል።
ዛሬ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የስራ ሰዓት ማሻሻያ ባደረገበት ስነስርዓት ላይ የተገኘው ፍትህ ሚኒስቴር ፤ ይህ አሰራር የተገልጋዮችን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ በመሆኑ ሌሎችም ተቋማት መሰል አሰራር ቢከተሉና ወስራ ቢያስገቡ ሲል ጠይቋል።
@tikvahethiopia

25 ዓመታት በሕብረት
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank

#EMA
ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ።
የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ ጉባዔ ያካሂዷል።
በዚሁ መሠረት ዘንድሮ 60ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ከየካቲት 29 እስከ 30/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ለማካሄድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።
በዓመታዊ የሕክምና ኮንፈረንሱ (AMC፣ በውስጥ እና ውጭ ሀገራት የሚኖሩ እውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን፣ የሕክምና ልምዶችን ለመለዋወጥ የሚረዳ መድረክ መሆኑንም አመላክቷል።
በጉባዔው የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ፣ CEU የሚያስገኙ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ እንዲሁም የሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀርቡበት ክፍለጊዜም እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል።
በማህበሩ 60ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ፦
* ከ600 በላይ የተከበሩ የሕክምና ባለሙያዎች
* ከሁሉም ክልል የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፣
* ከተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ማኀበራት፣
* ከስፔሻሊስቶች ማኀበራት የተውጣጡ ተወካዮች፣
* የሕክምና ኮሌጅ ኃላፊዎች
* የመንግሥት አካላት
* የጤና አውደ ርዕይ ከ100 በላይ ድርጅቶች
* ከ2,000 በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በየዓመቱ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር የሽልማት መርሀ ግብር ግብርም በ2016 ዓ/ም በአራት ዘርፍ ማለትም ፦
• “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የአመቱ ምርጥ የህክምና ተማሪዎች
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የሕይወት ዘመን
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ምርጥ ወጣት ሀኪም
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የ2016 የዓመቱ ምርጥ ተቋም ሽልማት የሚሰጥ ይሆናል” ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ከተመሰረተ 1954 ዓ/ም ጀምሮ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ በታካሚዎች ደኀንነት እና በአጠቃላይ በሕክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫዎት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማኀበር ነው፡፡
#AddisAbabaTikvahFamily

#Tigray #Meklle
የኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ በዘላቂነት " / PEACE BUILDING IN ETHIOPIA AND BEYOND / " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሰላም ኮንፈረስ እየተካሄደ ነው።
በመቐለ ዩኒቨርስቲና ተባባሪ አካላት በተዘጋጀው የሰላም ኮንፈረንስ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ተሳታፊ ናቸው።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው የሰላም ኮንፈረንስ በሰላም ግንባታና ትርፋቶቹ ያተኮሩ ሶስት ሙሁራዊና ጥናታዊ ፅሁፎች በአገር ውስጥና የውጭ ሙሁራን ቀርበው ወይይት ይካሄድባቸዋል።
ከዓለም አቀፍ ኮንፈረንሱ በተጨማሪ በመቐለ ከተማ በሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችና የተፈናቃይ መጠለያ ጣብያዎች ጉብኝት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
በመቐለ ከተማ በመካሄድ በሚገኘው አለም አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ የጊዚያዎ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
ተጨማሪ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-10

#WolaitaSodo
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የከተማው ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ምስጋናው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራበት ኪዳነ ምህረት ቀጠና ላይ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ አደጋ ተከስቷል። በዚህ አደጋ የ2 ሰዎች (ወንድና ሴት) ሕይወት ሲያልፍ ችሏል" ብለዋል።
" ሌሎቹ 17 የሚሆኑ ወንዶች፣ 6 ሴቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያሉ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያና ኦቶና ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ዋና ኢንስፔክተሩ፣ "አንደኛዋ ሟች ከሹፌሩ ጋር የነቀረች ሴት ናት። አንደኛው ደግሞ ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪ ነበር" ነው ያሉት።
አደጋው የተከሰተውም በሕዝብ ማመላለሻ፣ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ)፣ በባለ ሁለት እግር ሞተር፣ በአንድ የቤት መኪና መካከል መሆኑን ገልጸው፣ "ሁሉም ላይ ጉዳት ደርሷል" ብለዋል።
" የአደጋው መንስኤ፣ ጥፋት የማነው? የሚለውን በሂደት ላይ ነን፣ ሹፌርም ተጎድቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የወላይታ ሶዶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በበኩሉ፣ " የአፈር ማዳበሪያ የጫነው የጭነት መኪና ፍሬን በመበጠስ ምክንያት ከባድ የመኪና አደጋ ተከስቷል " ብሎ በዚህም 2 ሰዎች ሞተዋል ፤ 24 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አሳውቋል።
በአደጋው ፦
- አንድ ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና
- ሁለት ቶዮታ ቪትዝ
- ሶስት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
More - https://t.iss.one/ThiqaMediaEth/301
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን

4ኛ ዙር የተረክ በM-PESA ዕጣ አሸናፊዎች ታውቀዋል!
መኪና እንደሚያስፈልገው ያሰበው የአዲስ ወጣት በምኞት ብቻ አላስቀረውም፤ በተረክ በM-PESA ግቢው አስገብቷታል!
ቀጣይ ተረኞች እናንተ ናችሁ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#furtheraheadtogether

የዋንጫውን አሸናፊ በመገመት ሽልማት ይውሰዱ!
- ሽልማቱን የምናበረክተው የቴሌግራም ገፃችንን https://t.iss.one/GlobalBankEth ለተቀላቀሉ ብቻ ይሆናል፡፡
- ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ለሽልማት ብቁ አያደርግም፣ ትክክለኛ 5 አሸናፊዎችን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #nigcam #nigeria #ivorycoast #afcon #winner

#ማዳጋስካር
ማዳጋስካር ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶችን ብልት እንዲቆረጥ የሚያዝ ህግ ማዘጋጀቷ ተሰምቷል።
በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ የምትገኘው ማዳጋስካር ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶችን ብልት እንዲቆረጥ የሚያስገድድ ህግ አውጥታለች፡፡
ሀገሪቱ ህጻናቶቿን ከመደፈር አደጋ ለመጠበቅ ጥብቅ ረቂቅ ህግ ያዘጋጀች ሲሆን በዚህ ህግ መሰረት ደፋሪዎች ብልታቸው እንዲቆረጥ ይደረጋሉ ተብሏል።
ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን የደፈሩ ወንዶች ብልታቸው በቀዶ ጥገና ሐኪም ተቆርጦ እንዲጣል ይደረጋል የተባለ ሲሆን ከ13 እስከ 18 ዓመት የሆናቸው ህጻናትን የደፈሩ ሰዎች ደግሞ በኬሚካል አማካኝነት ብልታቸው እንዲጎዳ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የማዳጋስካር ፍትህ ሚኒስትር ላንዲ በጉዳዩ ዙሪያ ለኤፍፒ በሰጡት ማብራሪያ ፤ በሀገሪቱ የሚደፈሩ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ይህንንም ለመከላከል የግድ ጠንካራ ህግ ማዘጋጀት አስፈልጎናል ብለዋል፡፡
" በ2023 ብቻ 600 ህጻናት ተደፍረዋል " ያሉት ሚኒስትሯ ላንዲ ጥፋተኛ የሆኑ ተከሳሾች በትንሹ ከ5 ዓመት ጀምሮ እስር እየተላለፈባቸው ቢሆንም ለውጥ አለመምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ድርጊቱ ጭካኔ እንጂ ጥፋተኞችን አያስተምርም ሲል አዲሱን የማዳጋስካር ህግ ተችቷል፡፡
" ህጻናት ከጥቃት መጠበቅ አለባቸው፣ ደፋሪዎችም በህግ መጠየቅ አለባቸው " ያለው አምንስቲ ኢንተርናሽናል ነገር ግን እርምጃው በሰዎች ላይ መገለልን እና የባሰ ጨካኝ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ብሏል፡፡
ድርጅቱ ፤ ወንጀሉን ሳይፈጽሙ ነገር ግን በብዙ ምክንያቶች ጥፋተኛ የሚባሉ ሰዎች ይኖራሉ በዚህ ጊዜ ህጉ ተግባራዊ ከተደረገ ሊቀለበስ የማይችል ጉዳት በሰዎች ላይ ሊደርስም ይችላል ሲል አሳስቧል፡፡
ይህ አከራካሪ ህግ አስገዳጅ ህግ ለመሆን ከግማሽ በላይ ያሉ ሂደቶችን አልፏል የተባለ ሲሆን የላይኛው ምክር ቤት ውሳኔ እና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፊርማ ይቀረዋል ተብሏል፡፡
መረጃውን ኤኤፍፒን ዋቢ በማድረግ ያስነበበው አል አይን ኒውስ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አልነጃሺ
በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ ጥገና ባለመደረጉ የሶሀባዎች መቃብር በዝናብ እና በፀሀይ እየተደበደበ መሆኑ ተገለፀ።
ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አልፎም የዓለም ሙስሊሞች ታሪክ የሆነው ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በውስጡ የነበሩ ቅርሶችም ተዘርፈው መወሰዳቸውን የአል ነጃሺ መስጅድ ኢማም እና አስጎብኚ ተናግረዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የንጉስ አል ነጃሺን ጨምሮ የ8 ሶኻባዎች የመቃብር ስፍራ ያለበት ቦታ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ በዝናብ እና ፀሀይ እየተደበደበ ከመሆኑም ባሻገር የመፍረስ አዳጋ እንደተጋረጠበት ኢማሙ ተናግረዋል።
በተጨማሪ የአል ነጃሺ መስጂድ ሚናራ በመሳሪያ የተመታ በመሆኑ በዝናብ ፍሳሽ እንደተቸገሩ ገልጸዋል።
ከቅርብ ሳምንታት በፊት በመንግሥት በኩል " የአል ነጃሺ መስጅድ በቱርክ መንግስት እድሳት እንደሚደረግ ቢገለፅም እስካሁን የመጣ አካል የለም " ሲሉ ኢማሙ ተናግረዋል።
በሌላ ዜና ፤ ሼህ ሙሀመድ አልሀሙዲን ለታሪካዊው የአልነጃሺ መስጂድ ትራንስፎርመር በመቃጠሉ የተቋረጠውን የውሀ እና መብራት አግልግሎት ለማስቀጠል ጥገና ለማድረግ በሚድሮክ ኩባኒያ በኩል ቃል መግባታቸው በመጅሊስ ልዑካን ቡድኑ መስማታቸው እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የነጃሺ አካባቢ ነዋሪዎች ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ቶሎ ተፈፃሚ እንዲሆን ጠይቀዋል።
መረጃው የሀሩን ሚዲያ ነው።